#ብልጽግና 50+ አግኝቶ ያሸንፋል። ስለሆነም #ብልፄው የስጋት ድግስን #የምርጫ መሳሪያው ሊያደርግ ፈጽሞ አይገባም።

 

#ብልጽግና 50+ አግኝቶ ያሸንፋል። ስለሆነም #ብልፄው የስጋት ድግስን #የምርጫ መሳሪያው ሊያደርግ ፈጽሞ አይገባም።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 May be an image of one or more people, people smiling, scarf and text
 
ብልፅግና የ2018ትን ፯ኛ አገራዊ ምርጫን 50+ አምጥቶ ምርጫውን #ደልደል ብሎ ማሸነፍ ይችላል። ግን ነገር ግን የስጋት፤ የጭንቀት፤ የፍርሃትን መሳሪያነት ግን ሊተው ይገባል። ስጋት፤ ጭንቀት፤ ፍርሃት መፍጠር የብልጽግና ቋሚ ዘዴው ነው።
 
የ2013 ዓም ምርጫ ከመድረሱ በፊት ሙሉ ኦሮምያ፤ ስሜን ሽዋ ነደዋል። ያ …… ጭንቀት፤ ያ ……… ፍርሃት፤ ያ ……… "መጡባችሁ" አቅም ፈጥሮ ብልጽግናና ደልደል ብሎ፤ ኮራ ብሎ እንዲያሸንፍ አደረገው። ብልጽግናን ተመራጭ ያደረገው ቀውስ ነው። ብልጽግና ቀውሰኛ ፓርቲ ነው። የወረሰው ከፈጣሪው ከህወሃት ነው። 
 
የዓለም ሚዲያወች የ2013 ዓም ምርጫው #በሰላም ተጠናቀቀ ሲሉም ተደመጡ። አይፈረድባቸውም። የአገራችን ፖለቲከኛም "ከገመትኩት በላይ ምርጫው በሰላም ተጠናቀቀ" ሲሉ አዳመጥኩኝ።
 
በወቅቱ ጽፌበታለሁኝ። የምርጫው ሽርጉድ ከመጀመራቸው በፊት ብዙ አስጨናቂ ክስተቶች ነበሩ። እነዛ አስጨናቂ ክስተቶች ከብልጽግና ሌላ ማንም የለንም ብሎ ህዝብ ብልጽግናን ተሰልፎ እንዲመርጥ አደረገው። ትወናው ይህ ነበር። የተሻለም ተፎካካሪ ነበር ለማለትም ይከብዳል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ የድል መስመር ተስፋ ሁልጊዜ #እንደቆዘመ ነው።
 
የሆነ ሆኖ በ2013 ዓም በምርጫው ሰሞን ታጣቂወች ጸጥ ረጭ አሉ። ማገት የለ። መንገድ መዝጋት የለ። የሰው ግድያ የከተሞች ቃጠሎ የለ። ወቅቱ ጭምት ሆነ። ከወቅቱ ከፋኝ ኃይል ጋር በትብብር በዓይን #ጥቅሻ ስለሚግባቡ ብልጽግና የልቡ ደርሶ ተመረጠ።
 
ባይሆን ጉባኤው ላይ መፈንቀል እንዳይመጣ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እራሳቸው የአስመራጭ ኮሜቴ #ሰብሳቢ ሆነው፤ እራሳቸውን ጠቁመው፤ እራሳቸውን አስመረጡ። በታሪክ ብቸኛው እራሱን ያስመረጠ መሪ። #ስጋት ነበረባቸው ማለት ነው። ለአስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሚሆን የሚያምኑትም አንድም ሰው አልነበረም ማለት ነው።
 
ያ ሂደት ቀድሞ የተከወነው ቀውስ ሁሉ ለምርጫው ስኬት የተከወነ ነበር። አሁን በኤፍራታ እና በአርሲ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግድያ እና መፈናቀል እኔ እማየው አዲስ የስጋት የገብያ መደብር እንደ ተከፈተ ነው። ቀድሞ ሽብሩ ይጀምራል። በምርጫ ዋዜማ ይቆማል። #የታዋቂ ሰብዕ ህልፈትም ሊታጭ ይችላል ከምርጫው በፊት። 
 
ምርጫው ሲደርስ ታዩታላችሁ። ጸጥ እረጭ ይልና "ምርጫው በሰላም ተጠናቀቀ" ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉም የሚፈርምበት ይሆናል። ምክንያቱም ቀድሞ የተሰራ የህሊና ጉዳይ ስላለ። ይህ ስልት ግን ሰዋዊ አይደለም። ለሰው የተፈጠረው ፖለቲካ በጭካኔ ጭንቀት ውስጥ ለድል መብቃት የላይኛው ያያዋል። መንገዱም ጸረ ሰው አስተምኽሮ ነው። ቢቆም ባይ ነኝ። 
 
የትኛው አቅም ይሆን ብልጽግናን የሚያሰጋው? መንግሥት ለመሆንስ ማን - ምን አለው? ተጨባጩ እኮ ፋክት አለው። ሁነቱ ዕውነት አለው። አገር እኮ ገብያ ልሄድ ነው፤ እስክመለስ ቤት ጠብቁ ተብሎ የሚኬድበት አይደለም። ለዛውም ኢትዮጵያ???
የግለሰብ አቅም ሊኖር ይችላል በአንድም በሌላም፤ የኢትዮጵያን መንግሥታዊ ሥርዓት አጽንቶ ለማስቀጠል አስኳላዊ ሁለገብ ትጋት፤ ተመክሮ፤ የሃሳብ ልቅና ይጠይቃል። 
 
በምንም ታምር ብልጽግናን #በልጦ 50+ የሚያመጣ ተፎካካሪ ይኖራል ብዬ አላስብም። አጠቃላይ የኢትዮጵያን ሁነት ስዳስሰው አብዛኛው ለብልጽግና ያደላ መንፈስ ነው ያለው። ሚዲያ ላይ እንዳለው፤ እንደሚነገረው አይደለም። "ህዝብ ከተከፋ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም።" ሊከፋ ይችላል የመኖር ዋስትናው፤ የመኖር መቻሉ ጉዳይ፤ ግን ህዝብ የተሻለ አማራጫዊ እርግጠኛ የሚያደርግ የሚጨበጥ የሚዳሰስ ሁነት ይፈልጋል። ፈግጪው ምን እንደሚያስፈልገው ህዝብ ያውቃል። ይልቅ ተፎካክሮ አሸንፎ፤ ፓርላማ ላይ በሃሳብ በመሞገት ተስፋ ለህዝብ መሆን ስለሚቻል ነው፤ የምርጫውን ዕድል እንዳታፈሱ የምለው። በስማ በለው ከሚሆን ልክንም ለማወቅ መወዳደር። 
 
እርግጥ ነው ሌላ ማንሳት የምፈልገው ህወሃት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ሆኖ ሂደቱን ለማደናቀፍ አይሞክርም ብዬ አላስብም። ቀውስ ተደራጅቶ ሊመራ አይችልም ልል አልችልም። ህወሃት #ትሬኮላታ ነው። ግን የተኛውም ሁነት ብልጽግናን በብልጫ ከማሸነፍ አያግተውም። ባለፋት ጊዚያት ከከወናቸው ግዙፋ የአባይ ግድብን ለፍፃሜ ማብቃቱ ነው። ይህ መቼም ድንቅ ተግባር ነው። ብልጽግና በፕሬዚዳንቱ ምህንድስና ፕሮጀክት ይጀምራል፤ ይፈጽማል። ይህን የእኔ የሚሉ ወገኖች ብልጽግናን ከውስጣቸው የማድረግ ሁነት ሊፈጥር ይችላል።
 
ሰብዓዊ መብትን፤ ሰላምን፤ ፍትህን፤ የሃሳብ ነፃነት በሚመለከት አብዝሃኛው ዜጋ አጀንዳው አይደለም። 
 
#ብልጽግና በምን ሁነት 50+ በምርጫው ያገኛል አልኩኝ - እኔው። 
 
ተደማሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ማህበራዊ መሠረታቸው ከ፭ ዓመት በፊት እንደነበረው አይደለም። ለምሳሌ አብን። ግን #ብልጼው ያሸንፋል። እንዴት? እንዴት ማለት ጥሩ ነው።
 
ግምት ነው ዳታው፤ ከምከታተላቸው ሁነቶች ባገኜሁት ግብረ መልስ ነው።
 
*** ነገረ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን የፖለቲካ ውክልናቸው በብልጽግና መንግሥት ልሙጥ ነው። እምጠብቀውም ተስፋም የለም። የድምጽ ሁነትንም ለመመዘን ጋዳ ነው። በብዙ ቤተመቅደሷ የተጎዳች እየተጎዳች ያለችም ናት። በዝምታ ይሁን።
በሌሎች ጉዳዮች ግን ……/ 
 
1) በሻሻ + ወልቃይት ጠገዴ #ሰቲት ሁመራ ዞን + ሲዳማ + ስልጤ ዞን + #ሸገር #ሙሉዑ ድምጽ ተቀማጭ ጥሪቱ ነው ለብልፄው።
2) ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስተማማኝ የሆነ ከ70 - 90 %ድምጽ ብልፄው ያገኛል።
3) ድሬም ከ70 - 90 % ብልጼው ሎተሪው ይደርሰዋል።
 
4) ሱማሌ ክልል የሚገርም ኃይል እየመጣ ነው። አሁን 50+ የብልጽግና የፖለቲካ ውክልና ቁልፍ ቦታ የተቆጣጠረው መንፈስ፤ ታማኝም #ደቡብ ነው። ሱማሌ ተወዳዳሪ እየሆነ እየመጣ ነው። በብቁ ሙሁራን ነው አቅም እየተደራጄ ያለው። ሰላም መሆኑ በራሱ ለሥራም፤ ለኑሮም፤ በዕድል ተጠቃሚነትም ሱማሌ አንደኛ ነው። የወደፊት የኢትዮጵያ የአመራር መዋቅርም ዕድሉ እየተደለደለት ነው የሚገኘው። ስለዚህ ጥቅሙን የሚፃረር ተጠቃሚ ስለለ ከ85% ብልጽግና የመረጥ ዕድል አለው ብዬ አስባለሁኝ።
 
5) አፋር ክልልም ከ60 - 85 % ብልፄው ይቀናው ይሆናል።
6) የእስልምና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵውያን በየትኛውም ክልል ይሁን ስስ ልብ ለብልጽግና አላቸው፤ ፈቃዳቸውን ያወርሱታል ብዬ አስባለሁኝ።
 
7) በየትኛውም ክልል የሚገኙ የፕሮቴስታንት ኃይማኖት፤ የብልጽግና ወንጌል፤ የሙሉ ወንጌል አማኞች ዘመናችን ነው ለሚሉት ብልጽግናን ይፈቅዱታል ብዬ አስባለሁኝ።
 
8. ከበሻሻ ውጪ አርሲ፤ ባሌ፤ አርባምንጭም ከ50+ በላይ በብልጽግና ላይ እምነት ይጥላሉ። ቻሌንጁ የሚኖር ወለጋ፤ አንቦ ላይ ሊሆን ይችላል። ደብረዘይት እና ናዝሬትም ብዙ ችግር ይኖራል ብዬ አላስብም።
 
9) በተለየ ሁኔታ ቀደምቱ ከንባታ እና ሃድያ ለብልጽግና የተለዬ ቀረቤታ እንዳላቸው አያለሁኝ። በጽኑ ሊፎካከሯቸው የሚችሉት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ነበሩ፤ እሳቸውም በአንድ ቀን ህመም በህይወት የሉም። ጠቅላይ ሚር አብይ ፈቅደው ለተተኪያቸው ለዶር ራሄል ባፌ "ይሁነን ብለን" ቦታ እንለቃለን ስላሉ፤ ካልፈጸሙ፤ እርግጠኛ የሚያደርግ ድምጽ ያገኛል ብልጽግና በከንባታ እና ሃድያ ማህበረሰብ። 
 
10) አዳዲስ ክልሎችም በደቡብ የተፈጠሩት ለዚህ መሰል የድምጽ አደረጃጀት እና አመራር እንዲያግዝ ተብሎ የተሳላ ጉዳይ ስለሆነ በዚህም የተሳካ የድምጽ ውጤት ብልጽግና ይኖረዋል።
 
11) አዲስ አበባ ሁሉም የሚፎካከርበት ሜዳ ነው። በማዶ ያለው የጭንቀት ደወልም ለስሜን ሽዋ፤ ለአርሲ ሳይሆን ለአዲስ አበባ የብልጽግና የማሸነፍ ሂደት ተጨማሪ አቅም እንዲሰጥ፤ ግሉኮስ እንዲሆን ታስቦ ስለሆነ፤ በፈለገ መሥፈርት 50+ አዲስ አበባ ላይም ብልጽግና ያገኛል። አዲስ አበባን አበራንላት ይላሉ እኮ እነ ብልጼ። 
 
#አማራ ክልል።
 
12) ጎንደር ከተማ የተረጋጋ ስብሰባ አድርጎ አይቻለሁኝ። ጎንደር ላይ አሁን ከሆነ የመንግሥት አትኩሮት አያለሁኝ። "የወልቃይት ብረሳሽ" ጉዳይ ደግሞ ለጎንደሬ የህሊናው በኽረ አጀንዳው ነው። ውሳኔ ያላገኜ ተንጠልጥሎ ያለ ጉዳይ ነው። ይህ መንፈስን ገዳይ፤ ተስፋን የሚቀማ ጉዳይ ባሊህ ካልተባለ ጊዜው #እየመሸ ሊሄድ ይችላል። 
 
ግን ምርጫን በሚመለከት ያለውን አቋም ለመተንበይ ጎንደር ከተማን ይከብዳል። በቅርብ ርቀት ፋኖወች አሉ። ጸዳ፤ ማክሰኝት፤ እንፍራዝ፤ ቆላድባ፤ ጯሂት ወዘተ ……… ደልጊ አለፋ ጣቁሳ፤ ሠራባ፤ አይከል፤ ተንከል፤ ደባርቅ እና ዳባት ……… ያሉበት የጸጥታ ሁኔታ ወጣ ገብ ነው። ወጥ ጸጥታ የለም። የህወሃት ባላንባራሶችም ድምጣቸውን አጥፍተው አሳቻ ጊዜ እንደሚጠብቁ አሊ ማለት አይቻልም። የሆነ ሆኖ አማች አገር ጎንደር ምን ሊወስን እንደሚችል አደብን ከሁላችን ይጠይቃል። አማችነቱን አሻም፤ ወይንስ ይሁነኝ ይል???
 
13) በሌሎች የአማራ ከተሞች ደሴ፤ ኮንቦልቻ፤ ንፋስ መውጫ፤ ደብረታቦር ወረታ እና አዲስ ዘመን፤ ደብረብርሃን፤ ፍኖተሰላም ዳንግላ የአማራ ክልል ከተሞች የጸጥታ ሁኔት አስተማማኝ ስላልሆነ ለግምት ይከብዳል።
 
"#በምርጫ አትሳተፋ" መሪ ኃይል ያደረጉ ሚዲያወች በዘርፋ ተግተው ስለሚሠሩ በሂደት የሚታይ ይሆናል። ይህንን የሚመጥን የተሟጋች አቅም #ብልጽግና በፋና መድረክ በሁለቱም ዙር አላዬሁም። ኃይልን ሊቋቋም የሚችል የፖለቲካ ሃሳብ አቅም፤ ክህሎት፤ ተደማጭነት የሚልቅ ሥራ የበለጠ ይጠይቃል።
 
14) ባህርዳር የአማራ ክልል መናህሬያ ብቻ ሳይሆን የተለዬ ሁነት ያለባት ከተማ ስለሆነች፤ ልቧ፤ ኩላሊቷ፤ ነርቧ፤ ህሊናዋ፤ የደም ዝውውሯ ሁሉ ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ይመስለኛል። ለምርጫ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ አገረ መንግሥትም ሊዘለሉ የማይገባቸው አመክንዮወች ባህርዳር ላይ አለ። 
 
15) ብልጽግና አማራ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት ጥረቱ እንብዛም ነው። አቅልሎ ነው የሚዬው። ለምርጫው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የመንግሥት ሥርዓትም ሳንክ የሚሆን አቋም ይመስለኛል።
 
16) ብልጽግና አማራ ክልል በማወቅሩ ውስጥ ያለውን መንፈስ ሃንድል ለማድረግ በአደባባይ እማዬው የለም። ብሄራዊ የምህረት ዓዋጅ ያስፈልግ ነበር። ብልጽግና ከአባይ ወዲህ ይበቃኛል ያለ ይመስለኛል።
 
------ ቢሆንም ግን በአማራ ክልል የሚያጣውን የድምጽ ድጋፍ ብልጽግና የሚያካክስበት ሁነት በበቂ ደረጃ አለ። ------
 
17) ውህድ ማንነት ያላቸው ዝንባሌያቸው ኢትዮጵያዊነት ነው። መጠጊያ ስለላቸው፤ ማንን ይመርጣሉ???? ብይን መስጠት ይከብዳል።
18) የብልጽግና አባላት እና አካላት ከጋንቤላ፤ ከአማራ ክልል ውጪ ለራሳቸው ጥቅም ተፃራሪ ሆነው ይቆማሉ ብዬ አላስብም። 
 ተጠቃሚወችም ናቸው ቢያንስ 85% የሚሆኑት ብልጼን ይመርጣሉ ብዬ አስባለሁኝ። ጉሮሯቸው እኮ ነው #ብልጼው
 
19) ሴቶች እና ምርጫ በየዘመኑ ያተረፍነው ዕንባን ስለሆነ የማንም የመሆን ፈቃድ የሌላቸው ሴቶች ሊኖሩ ይችላሉ።
 
20) ገበሬወች የፖለቲካ ውክልና በኢትዮጵያ ፖለቲካ የላቸውም። የመምረጥ ግዴታ እንጂ የመመረጥ መብት የላቸውም። ሰላም በሰፈነበት እንደ ሲዳማ ባሉ ቦታወች፤ እንደ ሰቲት ሁመራ ዞን እና እንደ በሻሻ፤ ሱማሌ ክልልን አክሎ ገበሬወች ብልጽግና #ቢገባቸውም /// ባይገባቸውም ይመርጡታል 95% ብዬ አስባለሁኝ። 
 
21) ጠረፍ ላይ ስላሉ ከተሞች በብልጽግና ልዩ አትኩሮት፤ ልዩ ዕውቅና ሲሰጥ አይቼ አላውቅም። ይህ ደግሞ ለምርጫ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለዘላቂነት ሉዓላዊነት ግዴለሽነት ዋጋ በእጥፍ ያስከፍላል። በተለይ የግራ ቀኙ የሱዳን ጉዳይ።
 
22) የፖለቲካ ውክልና #የሌለው፤ ዕውቅናማ የማይሰጠው ዝምተኛው ማህበረሰብ Silent Magority ( ጀርመኖች stille Meherheit የሚሉት) የዚህ ጨዋ ማህበረሰብ አቅምን፤ ዝንባሌን፤ ባህሪን፤ አቋምን #መተንበይ አይቻልም። ግን ተጨባጭ የሆነ ዕውነት እና ፋክት በኢትዮጵያዊነት ቀለም ካገኜ ደንበር - አልቦሽ፤ ቅድመ- ሁኔታ አልቦሽ ነው ድጋፋ። የፖለቲካ ውክልና የለውም። እንደ አቅም አይታይም። የራስህ ጉዳይ የተባለ ማህበረሰብ ነው። ግን ከመዳፋ የብዙ ትብትብ ችግሮች የሠረገላ የቁልፍ መፍቻ ያለው፤ ብልህ የተረጋጋ፤ አደብ ያለው ብልህነት ጣዝማው የሆነ ማህበረሰብ ነው።
 
23) አሁን ያለው ወጣት ኢህአዴግ ገብ ነው። ስለዚህ ምርጫውን እንደ ራሱ ተጠቃሚነት ሰፍሮ ይሆናል ድምጽ የሚሰጠው። ወጣትነትን የሚፈትኑ ሁነቶች ወዘተረፈ ናቸው። 
 
24) ትግራይ በስምረት እና ከህወሃት ውጭ ባሉ ልትወከል ብትችልም፤ በበዓት የመወዳደር ዕድሉ ጠባብ ነው። ሌላ ቦታ ተጠልሎ መወዳደር ይቻል ይሆናል። በስጋት መታያየቱ ግን አይቀሬ ነው። በፈለገው ዓይነት ስሌት ብልጽግናን የመምረጥ ፍላጎት ……… እኔ እንጃ??? 
 
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አመሻችሁልኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergure©Selassie
04/03/2026
 
በሰላማዊ ትግል ያላችሁ ሁሉ ጥሩ ልምድ ነውና ምርጫ ላይ ተሳተፋ።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።