ልጥፎች

ስለትውልድ፤ ለትውልድ፤ የትውልድ የሚሆን ሰብዕና የአጽናኝነት ዋዜማ ለእማማ #ስለመናፈቅ።

ምስል
  ስለትውልድ፤ ለትውልድ፤ የትውልድ የሚሆን ሰብዕና የአጽናኝነት ዋዜማ ለእማማ #ስለመናፈቅ ።   " ነፍሰ ጡር እናት፤ ፬ ሰላማዊ ሰወች?" መራር ስንብትን አስመልክቶ ቢቢሲ ዘግቧል።    "አቤቱ እንደ ቸርነትህ ብዛት ማረኝ ይቅር በለኝ፦" አሜን።   በወርኃ መስከረም ዓዲስ ዓመት፤ ዓዲስ ዘመን አዲስ ተስፋ ይጠበቃል። ከበዓላቱ ጋር የፈጣሪ ጥሪ ቢኖር ቢከብድም ይቻላል እንደምንም። በአደጋ፤ በጦርነት ሲሆን ግን እራስን ይመረምራል። እራስን ይፈታትሻል። በየዘመኑ ስለትውልድ፤ የትውልድ፤ ለትውልድ የሚሆኑ ተግባራት ቢከወኑም፤ ስንቃቸው አመድ፤ ለቅሶ #ራሮት ከሆነ ድካሙ፤ ብድሩ፤ ወለዱ ለምን እና ለማን ያሰኛል።   በቤተክርስትያን ግንባታ ላይ እያሉ እንደወጡ የቀሩት፤ በጦርነት ምክንያት በጤና ክሊንክ ላይ የተሰው ንጹኃን፤ " ሴቶች ሱሪ አትለብሱም" ተብለው የተፈጠረ ግጭት እና ጉዳት፤ በሰማይም በምድርም በአገረ ኢትዮጵያ ሆነ በዓለም ደረጃ የሚወርደው የቀልሃ መርዝ እና ማግስት ሲታሰቡ ተስፋን በተፈጠረበት ምርቃት ልክ #ተስፋነት ለመጠበቅ ይከብዳል።    የሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋን ለመቋቋም፥ የአየር ብክለት ላይ ተግቶ ሊሠራ ይገባው ነበር። ሚሳኤል፤ ቦንብ፤ ሮኬት ወዘተ ከማምረት ይልቅ። በሌላ በኩል እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ደሃ አገራት በረጅም ጊዜ ብድር ይሁን፤ በዕዳ፤ በእርዳታም ቢሆን የተሰሩ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን እሱ እራሱ ጥበቃ ማድረግ የማይችል ከሆነ፤ እንዲሁም ለአገልግሎት ተጠቀማዊም የደህንነት ዋስትና መስጠት ካልቻለ የአገር መሪነቱ ድርሻ፤ ደረጃን ይፈትነዋል #እርሱ #በእራሱ ።    በህክምና ተቋማት፤ በትምህርት ቤቶች፤ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሱ የድሮን ይሁን የከባድ...

የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።

ምስል
  የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።   አቤቱ አምላኬ ሆይ! "በቸርነትህም ምራኝ።"       ዕውነት ለመናገር አገረ ግብጽን በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሁሉ በባዛ #ቅንነት ፤ በገዘፈ #ትዕግስት መጠኑን ባለፈ #የመቻል አቅም ነው ኢትዮጵያ የገጠማትን፤ የሚገጥማትን ችግር ሁሉ ያስተናገደችው። እንዲያውም ሥልጣን ላይ የነበሩ፤ አሁንም ያሉ የፖለቲካ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢሊቶች ለተፎካካሪያቸው ሆነ ለተቃዋሚ የፖለቲካ #ዕሳቤወች ሆነ #ተቋማት በዚህ ያህል ቅንነት፤ በዚህን ያህል ትዕግስት፤ በዚህ የመቻል አቅም #ጥያቄወቻቸውን ለማስተናገድ እንደምን እንዳልቻሉ፤ እንደማይችሉም ግርም ይለኛል። የሃሳብ ልዩነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሞት፤ ለእስራት፤ ለመገለል፤ ለመሰወር ይዳርጋል።   ዕውነት ለመናገር ለግብጽ ኢትዮጵያ #የእናት ያህል ነው ጥያቄወቿን ሁሉ ስታስተናግድ የኖረችው። የአባይ ግድብ ከሃሳቡ እስከ ፍፃሜው እጅግ በሚደንቅ፤ በሚያስደም ብልህነት ነው ኢትዮጵያ የከወነችው።    ይልቅ ኢትዮጵያ ማድረግ ያለባት የገለልተኛ አገራትን ባለሙያወች በህይወት እያሉ በክብር ጋብዛ #መሸለም እንዲሁም የምስክርነት ተመክሧቸውን ቃለ - ምልልስ በማድረግን በፍጥነት ልትከውን ይገባታል ባይ ነኝ።   አጤ አባይን በሚመለከት ያን የመሰለ #የህሊና በሳል ቅድመ ዝግጅት እና #ስኩን ክንዋኔም በዶክመንተሪ በፍጥነት ዘገባው ሊሠራ ይገባዋል ባይ ነኝ። ለዕውነት #ፈጣን መሆን ያስፈልጋል። ውሸት ሲደራረብ ዕውነት ይመስላል እና። በዘንድሮው የተመድ ጉባኤም ሆነ ከዛ በፊት በማደምጣቸው ጉዳዮች በግብጽ በኩል ኢትዮጵያ #ተጫኝ...

ነፍሱ ከሥጋው የተለዬ፤ ሰላማዊ እረፍቱን የተነሳ የሰው ልጅ #አስከሬን ለፖለቲካ መደራደሪያ #የሚሰቃይበት ዘመን ያሳዝናል። «ትራምፕ እና ኔታንያሁ በጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተስማሙ» ዘገባው የBBC ነው። «የመካከለኛው ምሥራቅ እና የአውሮፓ መሪዎች የጋዛን የሰላም ዕቅድ እንደሚደግፉ ገለጹ»

ምስል
      ነፍሱ ከሥጋው የተለዬ፤ ሰላማዊ እረፍቱን የተነሳ የሰው ልጅ #አስከሬን ለፖለቲካ መደራደሪያ #የሚሰቃይበት ዘመን ያሳዝናል። አቤቱ አምላኬ ሆይ!    "በቸርነትህ ምራኝ።" አሜን።        ፕላኔታችን ትሁን፤ ስለ ሰው ልጅ መብት መረገጥ ግድ የሚላቸው ደጎች ሁሉ፤ ቁመን ለምንሄደው ቢቀር በሥጋ የተለዩት አካላቸው ለየትኛውም ዓለም የፖለቲካ ቅድመ መደራደሪያ #መያዣ የማይሆንበት ዘመን እኔ ይናፍቀኛል። ሰቅጣጭ እና አሰቃቂ አቋም ነውና።   እኔ ከዚህ በተረፈም የሰውን ልጅ የሚጎዳ ማናቸውም #የመዳህኒት #ቅመማ ሁኔታም የዓለም መወያያ አጀንዳ ይሆን ዘንድ እመኛለሁኝ። ጎጂ እንሰሳት፤ ጎጂ አረሞችን የሚቋቋም መዳህኒት መፈልሰም ለሰው ልጅ መኖር #ጥበቃ ያደርጋል። መሰሉን ለሰው ልጅ መጠቀመም ግን #ሰውኛም ፤ #ተፈጥሮኛም አይደለም። አቅሙ ምን ያህል እንደ ሆን ባላውቅም #ተመድ በዚህ ላይ አትኩሮት ቢሰጥ የሚል ህልም አለኝ።   አስቦበት የሚያውቅ ግን አይመስለኝም። ምንጊዜም ለሰው ልጅ ደህንነት እና የውስጥ ሰላም ማግኜትን ጥበቃ የምታደርግ ፕላኔትን አዘውትሬ እመኛለሁኝ።   አሁን ቢቢሲ አማርኛውን ስጎበኝ መልካም ዜና፤ #ቸር ዘገባ አገኜሁኝ። ለፍፃሜ ከበቃ ያን ሁሉ የሰቆቃ ገጠመኝ ያስተናገደው የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት በመልክ በመልኩ መቋጫ ያገኛል። ብዙ እጅግ ብዙ ጉዳትን ያስተናገደ ጊዜ ነበር። አሁንም ጦርነቱ አልቆመም። ይህ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሆነ በግራ ቀኙ በኩል #ይሁንታ አለ።    ይሁንታው ታትሞ ዕንባ ሲቆም፤ መጨካከን ቀጥ ሲል፥ ትውልድ ተስፋን የማየት #ፍንጣቂ ብርሃን ሲወጣለት ከደስታ በላይ ሐሴት ይሆናል። ጥ...