#የይቅርታ #ደወል፤ የምህረት ዓዋጅ ለሁላችንም ያስፈልገናል። ሰሞናተ - አጽዋማት የክርስትና ይሁን የእስልምና ሃይማኖት በአጽህኖት ይህን ያጠይቃሉ እና።
#የይቅርታ #ደወል ፤ የምህረት ዓዋጅ ለሁላችንም ያስፈልገናል። ሰሞናተ - አጽዋማት የክርስትና ይሁን የእስልምና ሃይማኖት በአጽህኖት ይህን ያጠይቃሉ እና። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" . #ምዕራፍ ፲፰ ለሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቃናት #ከሊቅ እስከ #ደቂቅ በአክብሮት እምጠይቃቸው ውስጣችሁ #ለምህረት ፤ #ለይቅርባይነት #ቅርብ ይሆን ዘንድ ብትፈቅዱለት። ዛሬን የተሰጠንን ቅዱስ ቀን #ካቴና ላይ ስለሚገኙ ወገኖቼ ሰጥቸዋለሁኝ። ስለሆነም ዛሬን አብረን እንሆን ዘንድ ዘንከት ባለ ኢትዮጵያዊ ትህትና #ቅኖቼን እጠይቃለሁኝ። እኒህ አባት፤ ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ፤ ደፋር ሞጋች፤ ርትዑ፤ የታሪክ አዋቂ ከአቦይ ስብኃት፤ ከአቶ በረከት ስምኦን፤ አሁን ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር በሚር ማዕረግ ፈርሰስ ከሚሉት ከአቶ ጌታቸው ረዳ፤ የጦር መሪ ከነበሩት ከጄኒራል ፃድቃን አይደለም በላይ፤ አቻ የሚሆን ግድፈት ፈጽመዋልን? ይህን ያህል አሳራቸውን የሚዩት? ወይንስ አዘውንትነታቸው ተጠልቶ ይሆን? #እርግማንም ነው። አንድ መሪ ከቂም እና በቀል የጸዳ መንፈስ ሊኖረው ይገባል። #የምህረት እና የይቅርታም #ሞዴል ሊሆን ይገባል። በመሪነት ውስጥ አንዱ የቅርብ ዜጋ፤ ሌላው የእዳሪ ሊሆን ፈጽሞ አይገባም። መሪነት የውሃ ቅዳ፤ የውሃ መለስ #የኩታራ ድልቂያ አይደለምና። በብዙ ነገር ዝልቅ ትዕግሥት የሚደረገው አቅም አግባቡን ስቶ ሌላ ላይ እንዳያርፍ ለጥንቃቄ ነው። እንጂማ ……… ያ ሁሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የተፈታበት ሁነኛ ጎዳናን ዓመት ድገም የሚል ፈጣሪ ከመንበሩ ለቆ አይደ...