ልጥፎች

1 ሚሊዮን ብር ለመጋረጃ? የበግ ገመድ ከመሸጥ እስከ ትልቅ ድርጅት ባለቤትነት! እናታችን ለማደጎ ሰጠችን! #i...

ምስል
" #ገነት እናት #ሥር ናት።" (የእስልምና ሃይማኖት አስተምህሮ።) እኔ ደግሞ እላለሁኝ እናት የህይወት የመጀመሪያ ት/ቤት፤ የፊደል ገበታ እና #መምህርትም ናት

#የአንከር ሚዲያ ሰሞናተ - ሙግቱ ይበል ያሰኛል። ሚዛን ግን ይጠይቃል ሰላሙ ለአማራ እናትስ ይላል።

ምስል
  #የአንከር ሚዲያ ሰሞናተ - ሙግቱ ይበል ያሰኛል። ሚዛን ግን ይጠይቃል ሰላሙ ለአማራ እናትስ ይላል።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       ትናንት ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ከአቶ ሚኪ ተስፋዬ ጋር ቃለምልልስ ነበረው። ሙሁራን አቅርቦ ሲሟገት እከታተለዋለሁኝ። ተደማጭም ጋዜጠኛ ነው። እንግዶቹን ወደ እሱ ምልከታ ለማምጣት የሚያደርገው ፍልሚያም የጉድ ነው። ድሮ ድሮ በብዙ እሞግተው ነበር። አሁን ሙግት አቆሚያለሁኝ። እሚገርመኝን አመክንዮ ግን ማቅረብ ግድ ይሆናል። ከተደመጠ #ስርክርክ የሚሉ ዕሳቤወችን ማጽዳት ይገባል። ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የትግል ሚዲያ ክፍሉ ይመስለኛል። ዝንባሌውም ወደዛ ነው። የሆነ ሆኖ ሰሞኑን ግን እሱን እራሱ በራሱ ሚዲያ የሚሞግቱት በርክተዋል። በተራው እዬተሞገተ ነው። ይህ ሸጋ ገጠመኝ ነው። የጠበቃ አርበኛ አስረስን ሙግትም አዳምጫለሁኝ።   ጠበቃው ቀላል አልነበረም። ፍላጎቱን አስከብሮ ነበር ውይይቱ የተጠናቀቀው - በእኔ ሚዛን አርበኛ አስረሱ አሸንፏል ባይ ነኝ።።። ብቁ ወጣት ነው ጠበቃ አስረስ። ለህይወቱ ግን #እሳሳለታለሁኝ ። አይደለም ለአማራ ለኢትዮጵያም የሚጠቅም፦ እራሱን በአግባቡ መግለጽ የሚችል ወጣት ነው። በሚያምንበት ሃሳብ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ማሳ ቀለመ #ህብር ያደርገዋል እና። ሰላሙ ቢገኝ።   ትናንትም አቶ ሚኪ ተስፋዬም እንደ ጉድ ነበር የሞገቱት ጋዜጠኛ መሳይ መኮነንን። ኢትዮጵያ ውስጥ በዜግነት ፖለቲካ ላይ የሚሠራ #ሰላማዊ ታጋይ ይህን ያህል አቅም ያለው አለን ብያለሁኝ። ሚዛን ላይ ሆነው የሚያምኑበትን ፋክት አላስነካም ብለው በድፍረት፤ በእርግጠኝነት ወሳኝ በሆኑ አመክንዮወች ጋዜጠኛው እስኪበቃው ተሞግቷል። አልተበገሩለትም። ደስ የሚል ፍልሚያ ነበር። ...

#አንዱ #የእኛ #ግርማ - የዘመን ሁነኛ! የሚሊዮኖች ድምጽ ይጮኃል!

ምስል
  የሚሊዮኖች ድምጽ ይጮኃል! አዳኝን ገድሎ የውስጥ ሰላም ይሰደዳል። ለገዳዮች በከንቱ የፈሰሰው የፈው የደም ጠብታ ሁልጊዜም ይጮኃል! እዮራዊ ርትህ ይሻልና!   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"                 #አንዱ #የእኛ #ግርማ - የዘመን ሁነኛ!   ዕንባ~~~~ ባባ በዕንባ~~~~ ዘንባባ ስለራሱ~~~ አነባ። በባሩድ~~~ ድብደባ በጭካኔ~~~ ደባ ዕንባ~~~ ባባ ስለራሱ አነባ። የሰውነት~~~~ ዓርማ ነበር~~~ ለእማማ #አንዱ የእኛ ግርማ የዘመን ሁነኛ! ቡቃያ~~~ ሲነቀል~~~ሲነቀል ዋይታ~~~ ሲበቃቀል~~~ እህህህ~~~ #ህህ ሲተከል --- ሲተከል፦ ንፁኃኑ በግፍ እንዲህም ሲገድል ዕንባ ይኽው ባባ ስለራሱ - አነባ። የበቀሉ ብቅል #ከ -አረሙ ከርፍቷል ትውልድ በምንጣሮ መጠጊያ ተነጥቋል። ዘረፋ - ዘረፋ -- የትንታግ ዘረፋ~~~~ የእስትንፋስ ዘረፋ~~~ የመኖር ዘረፋ --- ዘረፋ~~~~ዘረፋ የዕድሜ ---- ዘረፋ --- የትውልድ ዘረፋ ~~~ #የዊዝደም ዘረፋ #ከረፋ ! 06/02/2025 12.00 ሰዓት። ቢንተርቱር። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08/02/2025

#የአማራን #እናትን #ማሳደድ #ይቁም!

ምስል
  #የአማራን #እናት #ማሳደድ #ይቁም ! #አማራን #የሚከብሩ #እኛወችን #ማንገላታት #መግፋት ፦ #ይቁም ! #ቋያ #ውስጥ #ስቃይ ላይ የሚገኙት የአማራ ህዝብ #የዘመናት ስልጣኔ #ትንታጎች ! ኑሩልን። አሜን።                ሥርጉትሻ2025/02/08 አማራነት ይከበር! ፍትህ ለአማራነት! የአማራን እናት #ማሳደድ ይቁም!

ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………

ምስል
  ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     #ጠብታ ።   ወርኃ የካቲት የታቦቴ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን በስጋ የተለዬን ስለሆነ እያዘከርነው ቢሆን። ለ17 ዓመታት በዘለቀው በእምዬ ሲዊዘርላንድ በራዲዮ #ሎራ 97.5 መካከለኛ ሞገድ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ በቀን ቅዱስ ከ15.00 -16.00 ጸጋዬ ራዲዮ በድንቁ አማርኛ ቋንቋ በሚተላለፈው መሰናዶ በአግባቡ በዬአመቱ ተከብሮ ይዘከራል። የራዲዮ ፕሮግራሙ የተመሰረተበት ዓላማም ግብም ይኽው ነውና። ለታላቅ ባለውለታ የቅኔ አባት መታሰቢያው ክብሩን፤ ልዕልናውን፤ የአማርኛ ቋንቋን የሥልጣኔ ትውፊቱን ማስቀጠል ነውና የትውልዱ ድርሻ።    #ውሽክታ ። አቶ ጃዋር መሃመድ ስለ አዲስ አበባ ሰሞኑን ያለው ቁምነገር አለ። ከዛ ያጎረፈ ሃሳቡ በፍፁም የተለዬ አዲስ አበባን የገነባትን #ጉራጌን አትዝለሉ ሲል ለኦሮሞ እና ለአማራ የአዲስ አበባ አቀንቃኞች መልዕክቱን ሳደምጥ #ቁጥር አንድ ውሽክ አልኩ። በነገራችን ላይ የጨመቱ ጉራጌ፤ ጋሞ፤ ወላይታ፤ አማሮ፤ አፋር ወዘተ ማህበረሰቦች ኢትዮጵያ ስለሰጣት ፈጣሪን አላህን ልታመሰግን ይገባታል።    ቁጥር ሁለቱ ውሽክታ ደግሞ በአገረ ጀርመን ላይ "እኛ መንግሥት መገልበጥ ሰልችቶናል" ሲል ውሽክ ብዬ ነበር። ኧረ በሞቴ አይሰልችህና ሞክረው በማለት መልሱንም ጥፌያለሁ። ሊንኩም ተቀምጧል።   ሰሞኑን ደግሞ በኦነግ ዓርማ በተንቆጠቆጠው አዳራሽ በአሜሪካ ኦሪንገን ላይ ተሰብሳቢወች በጀርባ በሚታዩበት የጃዋሪዝም ጉባኤ ላይ በኦሮምኛ ተናግሮ የተተረጎመውን " ማለዳ " በሚባል ዩቱብ ቻናል፤ "መንግሥት መገልበጥ ከሰለቸን ተሃድሶ ይባል፤ ተጠግኖ ተጠግ...