ልጥፎች

#በኖኽ #መርከቡ የአባይ ብሥራታዊ ዕጹብ ብራንድ ትልም ፍፃሜ እንኳን ደስ አለሽ ልዕልት ኢትዮጵያ! በልጆችሽ የተግባር ልዕልና #ልዩው #ብራንድሽ ለወግ በቃልሽ! !#እሰይ! ዛሬ ለእኔ ዕንቁ #ብሄራዊ ቀኔ ነው።

ምስል
  #በኖኽ #መርከቡ የአባይ ብሥራታዊ ዕጹብ ብራንድ ትልም ፍፃሜ እንኳን ደስ አለሽ ልዕልት ኢትዮጵያ! በልጆችሽ የተግባር ልዕልና #ልዩው #ብራንድሽ ለወግ በቃልሽ! ! #እሰይ ! ዛሬ ለእኔ ዕንቁ #ብሄራዊ ቀኔ ነው።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንሃለሁ።"         ዘለግ ያለ ጹሁፍ ነው። ለቅጽበታውያን ሳይሆን የተረጋጋ፤ የጨመተ መንፈስ ለተመረቀላቸው፤ የትውልድ ጉዳይ ህሊናቸው ለሆነ ቅኖቼ የተፃፈ ማስታወሻ ነው። አመሰግናለሁኝ ጊዚያቸውን ለእኔ ለሚሸልሙ አዱኛወቼ።    #መርኃች ሆነ መሪያችን የዕውነት ተፈጥሮ ይሆን ዘንድ እንፍቀድ። ትሁታዊ ልመናዬ።   ይህ ከደስታ በላይ ሐሤት ነው። ከምድር እስከ አርያም ፍጹም የሆነ ልዩ ቅዱስ መንፈስን የሚመግብ። የሰው ልጅ አለሁ፤ እየኖርኩ ነው ማለት የሚችለው ዕውነትን #የማይፈራ ሲሆን ብቻ ነው። ዕውነት ለቤት እና ለዱር እንሰሳት - አልተፈጠረም። ዕውነት ለጋራ ሸንተረሩ - አልተፈጠረም፤ ዕውነት ለወንዝ ፏፏቴ - አልተፈጠረም። ዕውነት ለዝናብ - አልተፈጠረም።    ዕውነት ለወጀብም - አልተፈጠረም። ዕውነትበዕውነትነት የተፈጠረው የሰው ልጅ እንዲኖርበት ነው። ዕውነት የሆነውን ዕውነት፤ ሃሰት የሆነውን ደግሞ ሃሰት ማለት ይገባል። በዘመናችን ታላቅ የተግባር ተጋሎ ለስኬት ሲበቃ የእኔ ማለት ይገባል። ሊቀ ትጉኃንን ለማመስገን ቆጥቋጣ ልንሆን አይገባም።   #ኢትዮጵያዊነት ሜዳ በቀል አይደለም! ኢትዮጵያዊነት የእዳሪ ግኝትም አይደለም። የዊዝደም እንጂ።   ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መሥራችነቷ፦ ኢትዮጵያ የዓለም አንድነት ከመሠረቱ ቀዳሚ አገሮች መመደቧ፤ ኢትዮጵያ የቀጥታ ቅኝ ግዛትን፤ የእጅ አዙር ቅኝ ተገዥነትን...

ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።

  ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።   "አቤቱ ንጹህ ልብፍጠርልኝ።" አሜን።     ጤና ይስጥልኝ እንዴት አደራችሁ ቤተ - ሥርጉትሻ ቅኖቼ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዩንቨርስ ጋር ያላት የዕውቀት ደረጃ #የሰመረ ነው። ሳይንስ በደረሰበት ዘመን አይደለም ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ሳይንቲስት የሆነችው። ፈላስፊት ኢትዮጵያ ፈላስፋ የሆነችው ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ሆኖ ግሎባሉ ዓለም በተቀበለበት ዘመንም አይደለም። ዩንቨርሷ ኢትዮጵያ ዩንቨርስን የቀመረችበን መክሊቷ የምዕት ነው። ኢትዮጵያ ጀማሪ አስትሮኖመር አይደለችም። #የፊደል ገበታ እንጂ። የእሷነት ሚስጢሯ ማህለቅ ደግሞ #ግዕዝ ቋንቋ ነው። ግዕዝ ቋንቋ ብቸኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅብዓዋ ነው። የተሰጠችው ከእዮር ነው።   ኢትዮጵያ ዊዝደሟ ከምድር እስከ እዮር የዘለቀ መሆኑ እኛ በደረስንበት ዘመን እንሆ #ገሃድ እየወጣ ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ብላቴናዋ ዶር ሮዳስ ጽፈው፤ ተንብየው፤ ተፈላስፈውበት የነበረው የፋክት እንክብል እንሆ ዕውን ሆነ። ሊቅነት በታምራት፤ ዕውነት በትንግርት ኢትዮጵያ #ልኳን ስታገኝ እንዲህ ነው።    ሊቀ - ሊቃውንቱ ዶር ሮዳስ ከእግዚአብሄር በታች እራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ በትህትና ላሳስባቸው እወዳለሁኝ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ሚስጢር እንዳይፈስ በአጓጉል ሁኔታ ጥንቃቄ አጀንዳወት ቢሆን ምኞቴ ነው።   ዓለማችንን በዩንቨርስ ዕውቀት የሚተረጉሙ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች በኋላስንት ሺህ ዘመናት በኋላ የተቋቋሙት የአስትሮኖመር የምርምር ተቋማት እንኳን የኢትዮጵያን የህሊና የሥልጣኔ ደረጃ ሊመክት ወይንም ሊለካካ ...

የአጤ አባይ #ዳግም ልደት እና የኢትዮጵያ #የፖለቲካ እስረኞች።

  የአጤ አባይ #ዳግም ልደት እና የኢትዮጵያ #የፖለቲካ እስረኞች።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   እኔ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በኢትዮጵያ ቴሌኮም፤ በኢትዮጵያ ሠራዊት፤ በኢትዮጵያ አባይ ግድብ ኢትዮጵያን በጥልቀት በሚወክሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ተቋማትን በሚመለከት የየዘመኑን ገዢወች በምሞግትበት ሁነት ፈጽሞ አላያቸውም። እራሳቸው ትውልድ ስለሆኑ። በጣም እጅግ #ቁጥብ ነኝ። በሙግት ፈጽሞ አልነካካቸውም። ይልቁንም ዝምታየን በማስተዋል እመግባቸዋለሁኝ። #እስቲ ዛሬ ………    #አያድርግብኝ እንጂ እኔ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ብሆን ኖሮ፥ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞችን ይዤ የአባይ ግድብን ዳግም #ልደትን እንዲዩ አደርግ ነበር። ይህ አዲስ ክስተት ለሌላ ንጹህ ግሎባል ፖለቲካ ሁነት ጋር ልዩ ቀረቤታ ሊኖረው ስለሚችል፤ አዲስ ጎዳና ይጠርግ ነበር። የዓለምም አዲስ #አጀንዳ ይሆን ነበር። ለግሎባሉ የሰብዓዊ መብት አስጠባቂ ተቋማትም ፈር ቀዳጅ የፊደል ገበታ በሆነ ነበር። የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የመናገር፤ የመፃፍ፤ የማሰብ፤ የመራመር፤ ሃሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸው ላይ የኢትዮጵያ ህገ - መንግሥት ፈቅድነውም አልፈቀድነውም፤ በሚፈቅደው ድንጋጌ ልክ ሊሆን ይገባል። የሚዲያ ሠራተኞች፤ ጸሐፊወች ሞጋቾችን እና የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚያገናኘው ድልድይ የኢትዮጵያ ህገ - መንግሥት ርካብ ብቻ ነው።   የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በድንገቴ ተውኔት የተዋጣላቸው ናቸው እና የፖለቲካ እስረኞችን ከአጤ አባይ ከሆደ ሰፊው፤ ከታጋሹ ጋር ፊት ለፊት ካአገናኙ በኋላ፤ ከእንግዲህ የፈለጋችሁ አብረን እንመለስ፤ የፈለጋችሁ ከዛሬ ጀምሮ መንግሥታችን ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ትቀላቀሉ ዘን...