ልጥፎች

#እንቁጣጣሽ።

ምስል
  #እንቁጣጣሽ ።   የማከብራችሁ ማህበረ ቅንነት፣ መጪው ዘመን የስኬት፣ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ። የእኔ ድንግል ጥበቃ አይለያችሁ። አሜን።   በተለይ ለኢትዮጵያ #እናቶች በሙሉ መጪው ዘመን #ከዕንባ #እርፍ የምትሉበት ዘመን ይሁንላችሁ። አሜን። በዱር በገደል፣ በእስር ቤት የምትገኙ ወገኖቼ አይዟችሁ። የእኔ ድንግል ጥበቃ አይለያችሁ። አሜን። ሁላችሁንም እመቤቴ ትጠብቅልኝ። አሜን።    ቅድስት አገር #ኢትዮጵያን ፣ ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድን ፣ ዓለማችን እግዚአብሄር አምላክ ሰላም ያድርግልኝ። አሜን። አዲስ ዓመት እየመጣ ዋዜማ ላይ ነን። አገር ቤት በተለይ ጎንደር ዋዜማው ላይ ልዩ ሥርዓት አለ። ያ ይናፍቀኛል። ማምሻ ላይ በግ፣ ዶሮ እየጮኽ፣ ቡና ተፈልቶ፣ አበባ ቆሎ እና ኑግ ተዘጋጅቶ ዳቦ ቀርቦ ልዩ የሆነች ፍቅር የሆነች የቤተሰብ አባል፣ ወይንም ወዳጅ ቡና ታፈላለች። ያ ድባብ እጅግ ይናፍቀኛል።   አዱኛወቼ ምዕራፍ ፲፮ በዚኽው ይከወናል። ከሁሉም ምዕራፎች አጭሩ ምዕራፍ ፲፮ ነው። ምክንያቴ አዲስ ዘመን በሩን ነገ ይከፍታል። በተጨማሪም አጤ አባይም ትልቅ ግሎባል ክስተት ነው። ስለሆነም ምዕራፍ ፲፮ ማጠናቀቅ ይገባዋል።   በመጪው ጥቂት ቀናት ምዕራፍ ፲፯ እጀምራለሁኝ። ተከባብረን የምንደማመጥበት የጨመተ ጊዜ እንዲሆንልን አምላኬን አላህን በርከክ ብየ እለምናለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን።   "አቤቱ #ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ጎዳናችን ንጹህ ልብ እንዲመራው ብንፈቅድ ተራራ የሚያክለውን ጥቅል የፈተና #ቱቦ መቋቋም ያስችለናል አምላካችን። እስኪ ደፍረን እንሞክረው።    ለቅኑ ጨዋ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለብሩሁ አዲስ ትውልድ ሲባል ቅን፣ ንጹህ፣ ሩህሩህ፣ አ...

#በኖኽ #መርከቡ የአባይ ብሥራታዊ ዕጹብ ብራንድ ትልም ፍፃሜ እንኳን ደስ አለሽ ልዕልት ኢትዮጵያ! በልጆችሽ የተግባር ልዕልና #ልዩው #ብራንድሽ ለወግ በቃልሽ! !#እሰይ! ዛሬ ለእኔ ዕንቁ #ብሄራዊ ቀኔ ነው።

ምስል
  #በኖኽ #መርከቡ የአባይ ብሥራታዊ ዕጹብ ብራንድ ትልም ፍፃሜ እንኳን ደስ አለሽ ልዕልት ኢትዮጵያ! በልጆችሽ የተግባር ልዕልና #ልዩው #ብራንድሽ ለወግ በቃልሽ! ! #እሰይ ! ዛሬ ለእኔ ዕንቁ #ብሄራዊ ቀኔ ነው።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንሃለሁ።"         ዘለግ ያለ ጹሁፍ ነው። ለቅጽበታውያን ሳይሆን የተረጋጋ፤ የጨመተ መንፈስ ለተመረቀላቸው፤ የትውልድ ጉዳይ ህሊናቸው ለሆነ ቅኖቼ የተፃፈ ማስታወሻ ነው። አመሰግናለሁኝ ጊዚያቸውን ለእኔ ለሚሸልሙ አዱኛወቼ።    #መርኃች ሆነ መሪያችን የዕውነት ተፈጥሮ ይሆን ዘንድ እንፍቀድ። ትሁታዊ ልመናዬ።   ይህ ከደስታ በላይ ሐሤት ነው። ከምድር እስከ አርያም ፍጹም የሆነ ልዩ ቅዱስ መንፈስን የሚመግብ። የሰው ልጅ አለሁ፤ እየኖርኩ ነው ማለት የሚችለው ዕውነትን #የማይፈራ ሲሆን ብቻ ነው። ዕውነት ለቤት እና ለዱር እንሰሳት - አልተፈጠረም። ዕውነት ለጋራ ሸንተረሩ - አልተፈጠረም፤ ዕውነት ለወንዝ ፏፏቴ - አልተፈጠረም። ዕውነት ለዝናብ - አልተፈጠረም።    ዕውነት ለወጀብም - አልተፈጠረም። ዕውነትበዕውነትነት የተፈጠረው የሰው ልጅ እንዲኖርበት ነው። ዕውነት የሆነውን ዕውነት፤ ሃሰት የሆነውን ደግሞ ሃሰት ማለት ይገባል። በዘመናችን ታላቅ የተግባር ተጋሎ ለስኬት ሲበቃ የእኔ ማለት ይገባል። ሊቀ ትጉኃንን ለማመስገን ቆጥቋጣ ልንሆን አይገባም።   #ኢትዮጵያዊነት ሜዳ በቀል አይደለም! ኢትዮጵያዊነት የእዳሪ ግኝትም አይደለም። የዊዝደም እንጂ።   ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መሥራችነቷ፦ ኢትዮጵያ የዓለም አንድነት ከመሠረቱ ቀዳሚ አገሮች መመደቧ፤ ኢትዮጵያ የቀጥታ ቅኝ ግዛትን፤ የእጅ አዙር ቅኝ ተገዥነትን...

ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።

  ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።   "አቤቱ ንጹህ ልብፍጠርልኝ።" አሜን።     ጤና ይስጥልኝ እንዴት አደራችሁ ቤተ - ሥርጉትሻ ቅኖቼ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዩንቨርስ ጋር ያላት የዕውቀት ደረጃ #የሰመረ ነው። ሳይንስ በደረሰበት ዘመን አይደለም ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ሳይንቲስት የሆነችው። ፈላስፊት ኢትዮጵያ ፈላስፋ የሆነችው ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ሆኖ ግሎባሉ ዓለም በተቀበለበት ዘመንም አይደለም። ዩንቨርሷ ኢትዮጵያ ዩንቨርስን የቀመረችበን መክሊቷ የምዕት ነው። ኢትዮጵያ ጀማሪ አስትሮኖመር አይደለችም። #የፊደል ገበታ እንጂ። የእሷነት ሚስጢሯ ማህለቅ ደግሞ #ግዕዝ ቋንቋ ነው። ግዕዝ ቋንቋ ብቸኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅብዓዋ ነው። የተሰጠችው ከእዮር ነው።   ኢትዮጵያ ዊዝደሟ ከምድር እስከ እዮር የዘለቀ መሆኑ እኛ በደረስንበት ዘመን እንሆ #ገሃድ እየወጣ ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ብላቴናዋ ዶር ሮዳስ ጽፈው፤ ተንብየው፤ ተፈላስፈውበት የነበረው የፋክት እንክብል እንሆ ዕውን ሆነ። ሊቅነት በታምራት፤ ዕውነት በትንግርት ኢትዮጵያ #ልኳን ስታገኝ እንዲህ ነው።    ሊቀ - ሊቃውንቱ ዶር ሮዳስ ከእግዚአብሄር በታች እራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ በትህትና ላሳስባቸው እወዳለሁኝ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ሚስጢር እንዳይፈስ በአጓጉል ሁኔታ ጥንቃቄ አጀንዳወት ቢሆን ምኞቴ ነው።   ዓለማችንን በዩንቨርስ ዕውቀት የሚተረጉሙ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች በኋላስንት ሺህ ዘመናት በኋላ የተቋቋሙት የአስትሮኖመር የምርምር ተቋማት እንኳን የኢትዮጵያን የህሊና የሥልጣኔ ደረጃ ሊመክት ወይንም ሊለካካ ...