#ማካካሻ። ፲ አለቃ መሳፍንት
#ማካካሻ ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰። ፲ አለቃ መሳፍንት ይመስለኛል ሥሙ። የጄኒራል ሳህረ መኮነን ጠባቂ የነበረ ወጣት ነው። እኔ #ታቅዶ የተመደበ ይመስለኛል። ከእሱ ይልቅ ለመታመን ሌሎች ተመሳሳይ ማዕረግ ያላቸው ነበሩ የወንዝ ልጆች ነበሩና። ጄኒራሉን ለመቅደም #ገዳዩ #ጎንደሬ መሆኑ የትወናውን ሁነት ያብራራል። በሌላ በኩል አገዳደሉን ማን ይምራው ማን? በፍጹም እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር በሰውኛ #ስሌታዊ አመክንዮውን ስለማይደፈር። ወላጅ እናቱ ክፍትፍት ባለ #ጉሮኖ ይኖራሉ። አሁን በምን ሁኔታ እንደሚገኙ አላውቅም። የፍርድ ውሳኔው ተሻሽሎለታል። እግሩ እና ዓይኑ ግን #በድብደባ ብዛት እንደተጎዳ ሰምቻለሁኝ። ደብዳቢወቹ ማን ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋክት መረጃ ማቅረብ ባይቻልም፤ በቀልን የጸነሱ፤ መበቀልን በእጥፍ ለመተግረብ የጭካኔ ረሃብተኞች እንደሚሆኑ ግን መገመት ይቻላል። ለኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ልኳ አይደለም፤ ለእኛም አንመጣጠንም የምለውም ለዚህም ነው። ህወሃትን ያህል የሴራ #ጉድጓድ ተሸክመህ፤ ሌላውን ቤርሙዳ ትርያንግሉን የማህበረ ኦነግን #ትብትብ አቅፈህ ይህ ብላቴና ግርማቸው የሚያስፈራውን መኮነን ደፍሮ ገደለ ለእኔ ብዙም ቅርብ ያልሆነ ሎጅክ ነው። መሪነት በግርግር ጊዜ ያላጠናቸውን፤ ግን የገደፋቸውን ስርክራኪ ሁነቶችን እንዲህ ቅንጡ ሆቴሎችን ለመመረቅ ሰፊ ጊዜ ሲሰጥ ደግሞ #ተግ ብሎ እንደነዚህ ዓይነቶችን እጅ እና እግር አልቦሽ የሆነ የበቀል መገበሪያ፤ #የቁርሾ ማካካሻ በሆኑ ዕውነቶች ላይ ጥርት ያለ የግንዛቤ ለውጥ አምጥቶ እራስን ማረመን - ይጠይቃል። ለመሆኑ ይህ ወጣት አሁን በምን ሁኔታ ላ...