ልጥፎች

#ጉግሱ #በአርጀንቲና አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

  #ጉግሱ #በአርጀንቲና አሸናፊነት ተጠናቀቀ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   ጉዳዩ ፖለቲካል ኢሹም የታከለበት ስለሆነ የመጀመሪያው የጨዋታ ጊዜ አየሩ አግሬሲብ ነበር። የማሸነፍ እና የመሸነፍ ጉዳይ ሌላ የውስጥ አጀንዳ ስለነበረበት ከበድ ይል ነበር።   የሆነ ሆኖ ከግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በኋላ ቀድሞ እንግሊዝ ባስገባው ጎል ሌላ ትዕይንት ተፈጠረ። ውጤቱም የአርጀንቲና #ሁለት እንግሊዝ #አንድ በማግኜት በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ተጠናቀቀ።   የመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ጊዜ #አስፈሪ ነበር። አየሩ እራሱ አግሬሲብ ነበር። የአርጀንቲናው 17 ቁጥር ነገረ ሥራው ያስፈራ ነበር። በኋላ ተቀይሯል።   አየሩ ረጋ ያለው፤ ትንሽ ሻል ያለው ከመጀመሪያው #ከውሃ እረፍት በኋላ ነበር። እስከ ውሃ እረፍት በነበረው ጊዜ በሁለቱም ተፋላሚ ቡድኖች ማህከል ግብ አካባቢ ሙከራ አድርገዋል።   ከመደበኛ እረፍት በኋላ 54.27 ደቂቃ ላይ እንግሊዞች ከመረብ ጋር #የታረቀ አንድ ጎል አስቆጠሩ። ይህን ጊዜ አርጀንቲናወች አቅማቸውን ጨምረው ፍልሚያውን #አፋሙት ።   አርጀንቲናወች ብዙ #የማዕዘን ምት ዕድል አግኝተዋል። በተጨማሪም የእጅ ኳስ ውርወራም ዕድል በስፋት ቀንቷቸዋል። ግን መረብ እና ኳስ ለረጅም ጊዜ #መታረቅ አልቻሉም ነበር።   እንግሊዝ ቡድን አንድ ጎል #ቀድሞ ካስገባ በኋላ ግን በተከታታይ በእንግሊዝ መረብ ላይ አርጀንቲናወች ጥቃቱን ቀጠሉ። በተከታታይ እና በትጋት የእንግሊዞችን መደበኛ ሜድ ከበው ተከታታይ ጥረት አደረጉ። አሳኩም።   አርጀንቲናወች በብዙ #አታካች ሙከራ #ላባቸውን ጠብ አድርገው በጥረታቸው የመጀመሪያውን የአቻነት ችቦ 85...

#እነማንን ይሆን የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

ምስል
  " #ሆደ ሰፊ እንሁ -----" #ን "። " ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።   #ምዕራፍ ፲፱።   "አሁን ግን #እንሰሶችን ጠይቅ፥ ያስተምሩኃልም፥ የሰማይ #ወፎችንም ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። ወይንም #ለምድር ተናገር፥ እርሷም #ታስተምርኃለች ፤ የባህር #አሳወችም ይነግሩሃል።" (መጸሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ከ ፯ - ፰።)        እንዴት ዋላችሁልኝ ክብሮቼ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።    ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የፓርላማው መደምደሚያ ቀን በንግግራቸው ማጠናቀቂያ ይህን ተናግረዋል። እርዕስ ያደረኩትን። ሃሳቡ ጥሩ ነው። ሃሳቡ ጥራት እና ብቃት ያለው ትውልድን ከዘመን ወደ ዘመን በተፈጥሮ ድልድይ ሊያሸጋገር የሚችል ነው።   "ሆደ ሰፊ እንሁን።" የወል ጉዳይ ነው --- አገላለጹ። #እነማንን ይሆን የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ከሳቸው በተጨማሪ ማን እነማንን ይመለከታል። እነማንንስ ያካትታል? ሌላው #ከመቼ ጀምሮ የሚል ተከታይ ጥያቄም ያስነሳል።   የውሳኔው ተፈፃሚነት፤ የሳቸው ቃል ከተነገረበት ቅጽበት ጀምሮ፤ ወይንስ በቀጠሮ? በአሳቻ ቀንና ወር ይሆን? የሚልም ሌላ ጥያቄ ያስነሳል። በሌላ በኩል አስበውበት መጥተዋል ለማለትም የማያስደፍር ዕውነት አለ።   አንድ የፓርላማ አባል ጥያቄ ሲያቀርቡ በቀደመው የመከፋት ድባብ ውስጥ ሆነው ሲያዳምጡ አይቻለሁኝ። ጥያቄ አቅራቢውን ማየት አልፈቀዱም። በልቤ ዛሬ በመሰነባበቻ ቀን እንኳን ያለውን ነገር ቻል አድርጉ ለማሳለፍ ስለምን አቃታቸው። እያልኩ ይህን ሳስብ መጨረሻ መልሶች ከሰጡ በኋላ፤ አስቀጥለው " ጀግና፤ አብረን እንስራ፤ #ሆደ ሰፊ እንሁን" ሌላም አለ እምጽፍበት የሚሉ ኃይለ ሐረጋት ወይንም ሥንኛ...

ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ።

ምስል
  ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት ። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በዳህላስ 70ሺህ ተመልካች በተገኘበት የሁለት ምርጥ የአውሮፓ ቡድኖች ጨዋታ አንዱ #ለሙሽርነት ሌላው #ላጃቢነት ሁኗል መቋጫው። እቴጌ ድንቡልቡል #ማጫ እያማታች ነው። ሌላም እየጠበቀች ነው። ማጫው በለጥ ላለው፤ ጥሩ አድርጎ ላጎናት፤ ለሰለቃት ታደላለች።    በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በከፍተኛ ራንክ ለዋንጫ የታጨው የፈረንሳይ ቲም፣ #ምን #እንደነካው አላውቅም በዛሬው በአገራቸውም ዛሬ ብሄራዊው #በዕላቸው ነው። ቀን ሳይቀናው ቀረ። ዛሬ ፓሪስ ምሽቱን እንዴት ታሳልፍ ይሆን?   የፈረንሳይ ቡድን እስከ 35ኛው ደቂቃ ድረስ #ምንም የግብ ሙከራ አላደረገም። አንድስም እንኳን። አይገርምም። በአንድ ጨዋታ ሦስት ጎል ያስቆጠረው ኮከብ አላቸው። ማፔም የተሰጠው ነው። በነፍስ ወከፍም በወልም ጠንካሮች ናቸው። ግን ዛሬ?    ይልቁንም ከመጀመሪያው የውሃ እረፍት በፊት #ስፔን የቅጣት ምት አግኝቶ አንድ ጎል አስቆጠረ። ከውሃ እረፍት እስከ ግማሹ መደበኛ እረፍት ጊዜ ድረስ ፈረንሳይ #ምንም ዓይነት የግብ ሙከራ ሳያደርጉ አንድ ለምንም ውጤት እረፍት ወጡ።   ከእረፍት መልስ የፈረንሳይ ቡድን ምንም ያሻሻሉት ነገር ሳይኖር ጨዋታው ቀጠለ። ስፔኖች አንድ መደበኛ የጎል ዕድል ቀንቷቸው #ሁለት #ለምንም መምራት ጀመሩ። በቀሪው ደቂቃ አካክሰው በአቻ ውጤት ጨዋታው ተራዝሞ ተጨማሪ ዕድል ይኖራቸዋል ብዬ ሳስብ፤ በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ የዕለቱ ጨዋታ ተጠናቀቀ።   ……… #ከዛስ ? ትንሽ ልመለስ መሰል።  ...

ቤተ - ሥርጉትሻ #ዘለፋ፤ #ስድብ፤ #አሽሙር አይሰተናገድበትም!

  ቤተ - ሥርጉትሻ #ዘለፋ ፤ #ስድብ ፤ #አሽሙር አይሰተናገድበትም!   አቃሎ፤ አጣጥሎ ሳቅ ከተጨመረበት #ይፈቀዳል ። ሳቅ የናፈቀን #ህዝብ ስለሆን።   "እንሆ አሳባችሁን፥ የመከራችሁብኝንም፡ ክፋ ምክር አውቄዋለሁ።" ይላል የእግዜሩ ቃል። (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፯)   #ምዕራፍ ፲፱።   ፌስቡክ እጅግ በጣም ዘግይቼ ነው የጀመርኩት። የእጅ ስልክም አልነበረኝም። የስልክ ፍቅርም የለኝም። መደወልም፤ መቀበልም ለእኔ ሁለቱም የጭንቀት ማዕከሎቼ ናቸው። እኔ ኢሜል ነው የምወደው። መልሴ ፈጣን፤ በሙሉ አቅም የምሳተፍበትም መስክ ነው።   ፌስቡክ ስጀምር ይህ ቤት እንዲህ የተከበረ፤ ጨዋ፤ ከትርፍ ነገር የታቀበ፤ ዘለፋ፤ ስድብ የማይዘወተርበት አልነበረም። ከዚህም አልፎ በማህበረሰባችን የሚነወር ፆታዊ ጉዳዮችም በይፋ #የሚቀነቀኑበት ነበር።   ሌላው የሰውን ልጅ በእንሰሳ ምስል መስራት ይዘወተርበት ነበር። ምስልን መዘቅዘቅ፤ ኤክስ ማድረግብ ተዘውትሮ የሚሠራበት ነበር። የሃይማኖታዊ ጉግሱም ጠና ያለ ነበር። ሁሉንም መስመር ለመያዝ ጊዜ ጠይቋል። ተደክሞበታልም። ተለፍቶበታልም።   አንድ ጊዜ ፖለቲካል ሳይንስ ያጠኑ በዕውቀት፤ በተመክሮም ዝልቅ አቅም ያላቸው፤ ሚዲያም አላቸው፤ በአንድ ዕውቅ ሌላ ፖለቲከኛ ላይ ፍየል በአፋቸው ላይ እየሸናች ፎቶ ለጠፋ። ውስጤ አዘነ። ሃዘኔን ዋጥ አድርጌ መራራ ስንብት ሆነ። ምክንያቱም ለቀጣዩ ትውልድ፤ አክሰሱ ላላቸው ታዳጊወች ይህን መሰል የፈጣሪን ፍጡር የተዳፈረ ትልልልፍ የሚያስተምረው በጎ ነገር ስለለ።    እኒያው ሰው ከአንዲት የቅርብ ወዳጄ ጋር ፌስቡክ እያዬን በእሷ ኮንፒተር ያልሆነ ነገር ፃፋ። እኔም ይህን ቃል አይጠቀሙ ብዬ ፃፍኩኝ። ...