ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ።

 

ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 May be an image of football, soccer and text that says 'FIFA'
 
የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በዳህላስ 70ሺህ ተመልካች በተገኘበት የሁለት ምርጥ የአውሮፓ ቡድኖች ጨዋታ አንዱ #ለሙሽርነት ሌላው #ላጃቢነት ሁኗል መቋጫው። እቴጌ ድንቡልቡል #ማጫ እያማታች ነው። ሌላም እየጠበቀች ነው። ማጫው በለጥ ላለው፤ ጥሩ አድርጎ ላጎናት፤ ለሰለቃት ታደላለች። 
 
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በከፍተኛ ራንክ ለዋንጫ የታጨው የፈረንሳይ ቲም፣ #ምን #እንደነካው አላውቅም በዛሬው በአገራቸውም ዛሬ ብሄራዊው #በዕላቸው ነው። ቀን ሳይቀናው ቀረ። ዛሬ ፓሪስ ምሽቱን እንዴት ታሳልፍ ይሆን?
 
የፈረንሳይ ቡድን እስከ 35ኛው ደቂቃ ድረስ #ምንም የግብ ሙከራ አላደረገም። አንድስም እንኳን። አይገርምም። በአንድ ጨዋታ ሦስት ጎል ያስቆጠረው ኮከብ አላቸው። ማፔም የተሰጠው ነው። በነፍስ ወከፍም በወልም ጠንካሮች ናቸው። ግን ዛሬ? 
 
ይልቁንም ከመጀመሪያው የውሃ እረፍት በፊት #ስፔን የቅጣት ምት አግኝቶ አንድ ጎል አስቆጠረ።
ከውሃ እረፍት እስከ ግማሹ መደበኛ እረፍት ጊዜ ድረስ ፈረንሳይ #ምንም ዓይነት የግብ ሙከራ ሳያደርጉ አንድ ለምንም ውጤት እረፍት ወጡ።
 
ከእረፍት መልስ የፈረንሳይ ቡድን ምንም ያሻሻሉት ነገር ሳይኖር ጨዋታው ቀጠለ። ስፔኖች አንድ መደበኛ የጎል ዕድል ቀንቷቸው #ሁለት #ለምንም መምራት ጀመሩ። በቀሪው ደቂቃ አካክሰው በአቻ ውጤት ጨዋታው ተራዝሞ ተጨማሪ ዕድል ይኖራቸዋል ብዬ ሳስብ፤ በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ የዕለቱ ጨዋታ ተጠናቀቀ።
 
……… #ከዛስ? ትንሽ ልመለስ መሰል። 
 
ከዛማ በ64ኛው ደቂቃ አካባቢ ሁለተኛ ዕድላቸውን ፈረንሳዮች ሞከሩ። #አልተሳካም። የረባ ማራኪ የጎል ሙከራ አላደረጉም። ምን እንደሆኑ የሚውቁት እራሳቸው ናቸው። ብዙ ጊዜ ኳስ ይሾልክባቸው ነበር።
 
ስፔኖች በተደጋጋሚ #የማጥቃት #የመከላከል ተግባርን #አጣምረው ከወኑ። የስፔን ቡድን የተደራጄ ንቅናቄም ነበራቸው።
ፈረንሳዮች ምን እንደነካቸው አላውቅም። በጨዋታው አርትም፣ በኮኦርድኔሽንም፣ #በአትኩሮት ስስነትም በተጠበቀው ልክ አላየሁም።
ኮለንብያ እና ሲዊዝን የዳኙት የኤልሳባዶሩ ዳኛ ነበሩ የዕለቱ ዳኛ። 
 
#ግን ፈረንሳይ ሁለት ለምንም በስፔን?
 
ስፔኖች ጠንካራ ስልት እና ጥበብ አላቸው። ፈረንሳዮችም እንዲሁ #የሚናፈቅ የግል እና የወል አቅም ነበራቸው። ዛሬ ግን ቀኑ #ከዳቸው
በካታሩ ጨዋታ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ካታር ያቀኑት የፈረንሳዩ #ፕሬዚዳንት በዘንድሮው እስከ አሁን ትውር አላሉም። የፊፋ ፕሬዚዳንት ግን ነበሩ።
 
ግን የዛሬ ጨዋታ በከፍተኛ ጉጉት ተጠብቆ በጨዋታ መሳብ፣ ትዕይንታዊነት፣ ፋክክር የጠበቃችሁትን አገኛችሁን? ትሁታዊ ጥያቄ ነው።
ለእኔ #የበረደው #ድብ ያለ ነው የሆነብኝ።
 
ስፔን ለዋንጫ፣ ፈረንሳይ ለደረጃ #አንድ /// #አንድ ጨዋታ ይቀራቸዋል። ማፔ በካታሩ የዓለም ዋንጫ #ሁለተኛ መውጣቱ በእጅጉ አሳዝኖት ነበር። ዛሬ የባሰ ሆነ። ለነገሩ የወርቅ ጫማ ውድድሩን ይረታ ይሆን? 
 
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
14/07/026.
ኳሲዝም ለምልም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።