የትንሹ #አጽናኝ ቡድን ተሳካለት።
የትንሹ #አጽናኝ ቡድን ተሳካለት።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
ቤልጀሞች የማያገኙት ዕድል #አመለጣቸው። ከዚህ ቀደም እንደፃፍኩት ቤልጀም የኮኦርድኔሽን ችግር አለባቸው።
በሌላ በኩል #ሉካኩ በመደበኛ ጊዜ አልገባን። 60ኛ ደቂቃ ላይ ነው የገባው።
ምን አልባት ግዙፍ ሰውነት ስላለው ይደክማል ብለው ይሆናል። የሆነ ሆኖ የስፔኖች ድል ከ2010 በኋላ በዓለም ዋንጫ ከወሰዱ በኋላ ከዚህ ደረጃ አልደረሱም ነበር።
ቤልጀሞች ለጎል የነበራቸው ጥረት እንብዛም ነበር። ያ በመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከሩት #ተሳካላቸው። ለሁለተኛ ጊዜ ሞክረው ሳይሳካ ቀረ።
በአብዛኛው ኳስ #በስፔኖች ሥር ነበር። ዛሬ ብዙም የማዕዘን ምት፣ የእጅ ውርዋሮ ዕድል ብዙም ያልታየበት ጨዋታ ነበር።
በውነቱ ልብ የሚያንጠለጥል፣ ውብ እና #ማራኪ ለማለትም አልደፍርም። እንደ ኖርማል ጊዜ ጨዋታ ነበር ሂደቱ የተከወነው።
የስፔን ቀጣይ ተጋጣሚ #ፈረንሳይ ነው። ለፈረንሳይ ቤልጀሞች ቢሆኑ ጥሩ ነበር።
በተናጠል አቅምም ፈረንሳዮች ከስፔን ጋር ሲነፃጸሩ #በስሱ በለጥ የሚሉ ይመስለኛል።
የሁለቱ ጨዋታ ጥሩ ትዕይንት፣ ድንገቴዊ ሁነት ሊገጥመው ይችላል። ያ ከሆነ ደግሞ ጨዋታው ተገማች ሳይሆን በአንዱ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ይችላል።
ስፔኖች ከዚህ ቀደም #አዛውንት አሰልጣኝ ነበራቸው። የዓለምን ዋንጫ፣ የአውሮፓን ዋንጫ በተከታታይ ያገኙት በአሰልጣኛቸው ጥበብ ነበር።
ያሰረጹት ባህል #መጨረሻ ደቂቃ አካባቢ #በላይ በላይ ተጫዋች መቀዬር። የተጋጣሚውን መንፈስ ለመጫን፣ #ለመበተን ይመስለኛል። ይህን እንደ #ባህል ስፔኖች የወሰዱት ይመስለኛል። ያሳካሉም። ተቀይሮ የገባው ነው #ጎልም የሚቀናው።
በሙሉ አቅም ተቀያሪ ሲገባ በተቀናቃኙ ጎራ ያለውን መዳከም ተጠቅሞ ተቀያሪው ዕድሉን #ያቃናል።
የፈረንሳይ አሰልጣኝ ከቡድኑ ጋር አብረው የቆዩ ስለሆነ አወንታዊ ጎን አለው ይህ ገጠመኝ።
ጥንካሬን ለማስቀጠል ይሁን፣ የቲሙን ችግር በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል የአመራር #ተከታታይነት ሲኖር።
እኔ የጠበቅኩት ጨዋታው ተራዝሞ ሎተሪ #የፔናሊቲ እድል ቤልጀም ቢያገኝ የሚል ምኞት ነበረኝ።
ጨዋታው በመደበኛ ጊዜ ተጠናቀቀ። የቤልጀምን ቡድን የጎዳው 70ኛ ደቂቃው ላይ የቤልጀም ጎል ጠባቂ ተጎድቶ #ስለተቀየረም ይመስለኛል። በተጫዋቹ ላይ ይህ ድንገቴ ጫና ሊፈጥር ይችላል።
ዋና አዘጋጇን አሜሪካን በሰፋ የጎል ልዩነት የሸኜው አውሮፓዊው ቤልጀም እንደ ለመደበት #ሳይዘልቅ ወደ አገሩ ለመመለስ ተገዷል።
በዚህ ጨዋታ ወጀብ የበዛባቸው የፊፋው #ፕሬዚዳንት አልነበሩም።
ዛሬ ቀንበጡ #የማል ግብ ባይቀናውም ብዙ ተሯሩጧል። የክርስትያን ሮናልዶ መራራ ስንብት የተጋራበት ፍጥነት፣ ሁነት ልባዊነት ቀልቤን ገዝቶታል።
ስለዚህም በለቱ ጎል ባይቀናውም ይመቸው አልኩኝ። ፈጣን፣ ጠንቃቃ፣ አዛኝ እና አጽናኝነቱ አስደምሞኛል። እሚታውን በጣም ነው የሚወደው። የእሚታ ልጅ ይሆን?
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን፣ አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
ደህና እደሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
10/07/026.
ኳሲዝም ይለምልም። አሜን።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ