ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር #ህሊናው ሊሆን የሚገባው #ኦርጋኒክ ሰብዕና ያለው አቶ ኦባንግ ሜቶ ነበር።
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፲፱።
ኦባንግሻ #ለፈላስፊት ኢትዮጵያ #ኦርጋኒክ ማንነት፣ #ልኩ ኦርጋኒክ ሰብዕናው የሚመጥን ነበር። ሁልጊዜ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት እነቃለሁ። እንደ ነቃሁ የሚያስቀጥል ሃሳብ አዕምሮዬ ካመነጨ ይህንኑ አዲስ ሃሳብ እያጠናሁ ይነጋል።
ዛሬ ሌሊት ኦባንግሻን አሰብኩት #ዘለግ አድርጌ። ሁልጊዜም አስብለታለሁኝ። ምክክሩ ከወደ ጋንቤላ አዲስ "ምክክር" የሚባል ቤቢ አግኝቷል። ስሙም "#ምክክር" ነው። ይደግልን። አሜን።
ከንቲባ ወሮ አዳነች አበቤ የአራስ ወጉን ሲያደርሱ አይቻለሁ። ይህ መልካም ነገር ነው። መልካም ነገርን የማነወር ሰብዕና የለኝም። እንዲለመልም መመኜት እንጂ።
አዲስ ለተገኜው የጋንቤላው ልዩ ህፃን የተደረገው እንክብካቤ #ማለፊያ ነው። የዓለምን የሚዲያ አውታር ያጨናነቀው የስፔኑ ያማል ታናሽ ወንድም ነው። ብርቅ ድንቅ ደጋፊነቱ ልዩ አትኩሮት ስቧል። ሁለቱንም ዓለም አደነቀ።
ልዩ የሰብአዊነት አቅም የኢትዮጵያ #አንከር አቶ ኦባንግ ሜቶስ? ለአዲሱ ቤቢ ክብር፣ እንክብካቤ ጥሩ ነገር ነው። የትናንቱ የኢትዮጵያ ባለውለታ መኖሩን እንኳን ለማወቅ አለመቻላችን ያሳስባል።
ኦባንግሻን የበላ ጅብ አልጮኽ አለ። አይደለም ኢትዮጵያ #አህጉራችን ሊወክል የሚችል #አብነታዊ ሰብዕና ያለው። አምኖ፣ አገሩ ገብቶ፣ ንጹህ #መታመን ከድቶት እንዲህ ዝግትግት ባለ መረጃ አልቦሽ ሁኔታ መጨነቄ ለእኔው አሰብኩለት።
አገራዊ ምክክሩ አጀንዳውን አንብቤለሁኝ። ስለ #ሙስና ያነሳው ገርሞኛል። ስለ ሰብዕዊነት፣ ተፈጥሯዊነት ሰውን ስለማትረፍ አጀንዳው ቢሆን ብዬም አሰብኩኝ። የሰብአዊነት #አንበል አቶ ኦባንግ ሜቶ የኢትዮጵውያን ጉዳይ ሊሆን ይገባል።
በየዘመኑ በሚፈጠሩ ሁነቶች እራስን #ማግለሉ ሳይሆን ዕድሉን መጠቀሙ ቢጠቅም እንጂ አይጎዳም ባይ ነኝ። ከውስጥ ሆኖ መሞገቱ መጠየቁ የተሻለ ነው። በዚህ የምክክር ጉባኤ አቶ ኦባንግ ሜቶ ቢኖርበት ኢትዮጵያ ታተርፍበት ነበር። ያምርባትም ነበር። ተቀራራቢ መንፈስ ያላቸው ሰብዕናወች ተስፋን #ያጩም ነበር።
"ኢትዮጵያ #እንድናገር ፈቀደችልኝ" የሚል ድምጽ አድምጫለሁኝ። የኢሠፓ ጉባኤ አሳታፊ ነበር። ፓርላማም ነበር። ኢህዴግም በራሱ ፎርማት ብሄር ብሄረሰቦችን የሚያሳትፍበት ነበረው። በየኮርሱ የኢትዮጵያ መልኮች ይገኙ ነበር። ያ በመሆኑ ነው ዛሬ በባህሉ፣ በወጉ፣ በልማዱ፣ በቋንቋው የመገኘቱ ሚስጢር።
#የብሄረሰቦች መምሪያ የሚባል በዘመነ ኢሠፓ ነበር። #እርሾም፣ #መሰረትም እንዳልነበረ ባይደረግ ጥሩ ነው። ብዙ የተደከመባቸው ዘርፎች ስላሉ። እራሱ ሃሳቡ #ምንጭ አለው።
ለመናገር፣ ለመፃፍ፣ ለመደራጀት ሙሉዑ ነፃነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ድፍረት የለውም። እንዲህ በራስ መንፈስ መንገድ ሁነት ደግሞ መነጋገሩ በዘመነ ብልፄው #ለተፈቀደላቸው ጥሩ ነው። መጀመሩ በራሱ መልካም ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ትብትብ ነው።
ክብረቶቼ እንዴት አረፈዳችሁልኝ።
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
17/07/026.
#ሰብዓዊነት #ይከበር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ