10 ጎል ከመረብ ጋር #የተጋባበት የደረጃ ጨዋታ።

 

10 ጎል ከመረብ ጋር #የተጋባበት የደረጃ ጨዋታ። 
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
የመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ በእንግሊዝ 4 ፈረንሳይ ምንም በሆነ ውጤት ፈረንሳዮች ምን ነካቸው የሚል የቤት ሥራ ለተመልካች #ሸልመው ግራ ቀኙ ተጫዋቾች ወደ እረፍት አመሩ።
 
ከእረፍት መልስ ፈረንሳዮች ተጠናክረው ገብተው ሦስት ጎል አስገቡ። እንግሊዞች #የቅጣት ምት አገኙ እና ከ4 ወደ 5 ከፍ አሉ።
ፈረንሳዮች የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለው አንድ በመጨመር ወደ 4 አደጉ። ይህን ጊዜ ጨዋታው ሊራዘም ይችላል የሚል ተስፋ ቢጤም ነበር። ነገር ግን እንግሊዞች 1 አክለው 6 እንዳሉ ጨዋታው #ተጠናቀቀ
 
በደረጃ ጨዋታ ይህን ያህል ጎል በጣም ብዙ ነው። የእንግሊዞች በአርጀንቲና መሸነፍ፣ የፈረንሳይ ደረጃውን ስፔኖች መውሰድ #የመድከም#የመዛል ሊሆን ይችላል።
 
በዚህ ጨዋታ #ማፔ ሁለት ጎል አስገብቷል። ቢጠነክር ዛሬ ተጨማሪ ጎሎችንም መጨመር ይችል ነበር። #የወርቅ ጫማዋ ብትቀናው ምኞቴ ነው።
 
#የወርቅ ቀለበትም ተዘጋጅቷል አሉ። እኔ አይደለም ያልኩት። ቢቢሲ ነው።
ነገ ለፍፃሜ አርጀንቲና እና ስፔን ይጋጠማሉ። የነገ ሰው ይበለን። አሜን።
ጨዋታው በመደበኛ ጊዜ ነው የተጠናቀቀው። #ደክሟቸዋል #ይረፋ
የእንግሊዞች የደረጃ ሽልማት እዬተሰጠ ነው። #ሦስተኛ ደረጃ ይዘው።
 
ጨዋታውን ይህ ዓይነት ነበር ለማለት አልቻልኩም። ደንብ እና ህግ ስለሆነ ብቻ የከወኑት ነው የሚመስለው። #የማይቀርበት ስለሆነ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
19/07/026

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።