#ጉግሱ #በአርጀንቲና አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

 

#ጉግሱ #በአርጀንቲና አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
ጉዳዩ ፖለቲካል ኢሹም የታከለበት ስለሆነ የመጀመሪያው የጨዋታ ጊዜ አየሩ አግሬሲብ ነበር። የማሸነፍ እና የመሸነፍ ጉዳይ ሌላ የውስጥ አጀንዳ ስለነበረበት ከበድ ይል ነበር።
 
የሆነ ሆኖ ከግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በኋላ ቀድሞ እንግሊዝ ባስገባው ጎል ሌላ ትዕይንት ተፈጠረ። ውጤቱም የአርጀንቲና #ሁለት እንግሊዝ #አንድ በማግኜት በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ተጠናቀቀ።
 
የመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ጊዜ #አስፈሪ ነበር። አየሩ እራሱ አግሬሲብ ነበር። የአርጀንቲናው 17 ቁጥር ነገረ ሥራው ያስፈራ ነበር። በኋላ ተቀይሯል።
 
አየሩ ረጋ ያለው፤ ትንሽ ሻል ያለው ከመጀመሪያው #ከውሃ እረፍት በኋላ ነበር። እስከ ውሃ እረፍት በነበረው ጊዜ በሁለቱም ተፋላሚ ቡድኖች ማህከል ግብ አካባቢ ሙከራ አድርገዋል።
 
ከመደበኛ እረፍት በኋላ 54.27 ደቂቃ ላይ እንግሊዞች ከመረብ ጋር #የታረቀ አንድ ጎል አስቆጠሩ። ይህን ጊዜ አርጀንቲናወች አቅማቸውን ጨምረው ፍልሚያውን #አፋሙት
 
አርጀንቲናወች ብዙ #የማዕዘን ምት ዕድል አግኝተዋል። በተጨማሪም የእጅ ኳስ ውርወራም ዕድል በስፋት ቀንቷቸዋል። ግን መረብ እና ኳስ ለረጅም ጊዜ #መታረቅ አልቻሉም ነበር።
 
እንግሊዝ ቡድን አንድ ጎል #ቀድሞ ካስገባ በኋላ ግን በተከታታይ በእንግሊዝ መረብ ላይ አርጀንቲናወች ጥቃቱን ቀጠሉ። በተከታታይ እና በትጋት የእንግሊዞችን መደበኛ ሜድ ከበው ተከታታይ ጥረት አደረጉ። አሳኩም።
 
አርጀንቲናወች በብዙ #አታካች ሙከራ #ላባቸውን ጠብ አድርገው በጥረታቸው የመጀመሪያውን የአቻነት ችቦ 85 ደቂቃ አካባቢ መረብ #ናፈቀቻቸው፣ መረብ ፈቀደችላቸው እና #ፏ ብላ ተቀበለቻቸው። የመጀመሪያውን ሳይ አጣጥመው ሳያጠናቅቁ፤ ሌላ የዕድል በርም #ቧ ብሎ ተከፈተላቸው።
 
ከዛማ ማን ችሏቸው የባከነ ጊዜ #ለዘጠኝ ደቂቃ ሲታከል #ውሮወሸባዬን መረብ አስነክታ #እቅፍ ድግፍ አደርጋ #ድገሙኝ ስትል በቁልምጫ ልዕልቷ ስትጠይቅ፤ ምን ገዶን ብለው አርጀንቲናወች #ቅብጥ እና #ቅልጥ ያለ #ማጫቸውን አቅርበው ለእሁድ ሁለተኛ ሙሽራ ሆነው #ታጩ
 
እንግሊዞች ስፔኖች እንዳደረጉት ያገኙትን ድል #የማስጠበቅ፣ የመንከባከብ፣ ለተጨማሪ #ድልም የማማተር አቅማቸው በውነቱ ውስን ነበር። 
 
በእንግሊዞች በራሳቸው ሜዳ ጥሩ አቀባበል የአገኜው የአርጀንቲና ቡድን ገጠመኙን በተደላደለ ጊዜ፣ በአለቀ ጊዜም #ሁለተኛውን ደግሞ ደልደል ብሎ፤ ቀኑም #ፏ ድሉም #ፍንትው ብሎ በሺወች የተገኜውን ደጋፊ በሙሉ በሐሤት አንበሸበሹት።
 
ዳህላስም ሁሉን በእኩልነት አስተናግዶ፣ በትዕይንቱ ተደምሞ፤ በውሽክታ ግራ ቀኙን በፍቅር ተቀብሎ በፍቅር ሸኜ።
ዘውድ ለደረጃ ከፈረንሳይ ጋር ግጥሚያ ይኖረዋል። እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ለቅዳሜ ለአጃቢነት። ሌላኛው ዘውድ ስፔን ደግሞ ደግሞ ከአርጀንቲና ጋር ለሙሽርነት ወይንም ለዋና ሚዜነት ለለተ ሰንበት ተቀጥሯል።
 
የአርጀንቲናዋች የጨዋታውን አየር ሙሉለሙሉ መቅጣጠር ተደክሞበታል። በድካም የተገኜ ድል፣ በልፋት የተገኜ ስኬት ደማም ነው። ይመቻል። ያስመቻልም።
 
አርጀንቲና የካታር ዋንጫ ባለቤት፣ ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ባለቤት የፖለቲካ ቁርሾ በሌለበት ሁኔታ ልዕልት ድንቡልቡልን ዕለተ ዕሁድ በልዩ ትዕይንት ይሞሽሯታል።
 
መተንበይ አይቻልም። እርግጥ ስፔኖች ያጠናሉ። የአቅመኛ ተጫዋችን የደም ቧንቧ መስመር የመዝጋት አቅም አላቸው። ትናንት ማፔን፤ ደንበሌን ያደረጓቸውን አይተናል። አርጀንቲና በመሲ መሪነት በአለቀ ሰከንድ አድብቶ ትልሙን የማሳካት ባህል አለ። ለኳስ አፍቃሪወች በተለይ ዕለተ እሁድ ሰላማዊ፤ ስክን ያለ፤ የተረጋጋ ጥሩ ጊዜ ይኖራል ብየ አስባለሁኝ። የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩ በወከባ ተጠናቋል።
 
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን፣። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
15/07/026.
ኳሲዝም ይለምልም። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።