ልጥፎች

«በሞኝ ክንድ ጉድጓድ አይለካበትም።» "የውክልና ጦርነት" አይኖርም አሉ።

ምስል
  «በሞኝ ክንድ ጉድጓድ አይለካበትም።»   ብዙ ጊዜ ሃሳባቸውን ሲለዋውጡ ስለማያቸው ልብ የሚያስጥል ባይሆንም፣ አሁን ላለው የቀንዱ ውጥረት ግን ጠቃሚ ውሳኔ ነው። በትክክል ገብቷቸው ይህን አቋም አጽንተው ከቀጠሉበት " በሞኝ ክንድ ጉድጓድ አይለካበትም? ኢትዮጵያዊው ብሂል ዘመን ሰጠው ማለት እችላለሁኝ። አንድ የአገር መሪ፣ ወይንም የአንድ ንቅናቄ መሪ በዓቱን ከጦር ሜዳነት መከላከል ብልህነት ነው።   ይህ ዜና ከጸና ለኢትዮጵያ የምሥራች፣ ለግብጽ ግን መርዶ ይመስለኛል። የግብጽ የፖለቲካ ሊቃናት ኮተት እያሉ የሚድሁበት መንጠላጠያ ፍላጎታቸው አንኳሩ ኢትዮጵያን መፎካከር፣ የአፍሪካ መሪ ሆኖ ለመውጣት ማለም ነው። አባይ ምክንያታዊ የመንፈስ ማረፊያቸው ቢሆንም ፋንታዚያቸው ግን የአፍሪካ አንከር መሆን ነው። የእኔ መረዳት እንዲህ ነው። ሥርጉትሻ 2025/09/24   ዝርዝሩን BBC አማርኛው ዘግቦታል።    https://www.bbc.com/amharic/articles/c62ld9dy4v2o «የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአገራቸው ውስጥ እንዲዋጉ እንደማይፈቅዱ ተናገሩ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአገራቸው በሰላም ማስከበር ላይ የሚሰማሩ የኢትዮጵያ እና የግብፅ ወታደሮች ወደ ግጭት ሊገቡ የሚችሉበት ምክንያት እንደሌለ በመግለጽ "የውክልና ጦርነት" አይኖርም አሉ።   ፐሬዝዳንቱ ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩት በሁለቱ አገራት መካከል "በሶማሊያ ምድር" የሚካሄድ ጦርነት እንደማይኖር እና ሶማሊያም ይህንን እንደማትፈቅድ አሳውቀዋል።   የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ላይ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በሶማሊያ ውስጥ ግ...

አብሶ በትምህርት ዘርፍ #ዛሬን #ሳያመልጥ መሻማት ነገን #ያበጃል። ዛሬ አጀንዳ ሲሆን ነገ #ያበራል። ነገ በዛሬ #የተባ ድርጊት ብቻ ነው የሚገኜው።

ምስል
  አብሶ በትምህርት ዘርፍ #ዛሬን #ሳያመልጥ መሻማት ነገን #ያበጃል ። ዛሬ አጀንዳ ሲሆን ነገ #ያበራል ። ነገ በዛሬ #የተባ ድርጊት ብቻ ነው የሚገኜው። #ምዕራፍ ፲፯   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     #ጠብታ ።   በአገሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ነክ ጉዳዮች፤ ለዛውም በአማርኛ ቋንቋ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገኝም። ከጋሜየ እስከ ሙሉ ዕድሜ ተዘለቀበት እኮ። የሠራሁበት እኮ ነው። በሌላ በኩል እያንዳንዱ ሰው በራሱ ህሊና የመጠቀም ሙሉ መብት አለው። በክራይ፤ በወለድ አገድ እስካላያስያዘው ድረስ። ሙሉ ዕድሜየን ነፃነቴን ለማንም ለምንም አሳልፌ ሰጥቼ አላውቅም። እኔን ሆነ ህሊናዬን አከራይቼ አላውቅም። የፈለገ አገረ ገዢ ይሁን። የፈለገ ሚሊዮኖች ይከተሉት። በሌላ በኩል ደግሞ እኔ ጎርፍ አምጥቶ ደለል የሠራብኝ ሴት አይደለሁም። ወይንም አብይዝም ሲመጣ አብሬ መጥቼ #ደራሽ ፖለቲከኛም አይደለሁም። ህሊናየንም ለማንም አከራይቼ አላውቅም።    በፊት ለፊቴ፥ ይሁን በጀርባየ የማስከትለው የሌላ አካል ወይንም ተቋም ወይንም የግለሰብ ፍላጎት እና አጀንዳም የለም። #እኔ እኔ ብቻ ነኝ። በቃ! እኔ እማስበው ከውስጤ የፈለቀ ሃሳብን ነው ሼር እማደርገው። በሌላ በኩል አንድም ቀን የእኔን ግራ ቀኝ ዩቱብ ቻናል፤ ብሎግ፤ ፌስቡክ፤ ራዲዮ ፕሮግራም ሳብስክራይብ፤ ሼር ላይክ አድርጉ ብየ አላውቅም። ወይንም #ፈንድ አድርጉልኝ፤ #ዶኔት አድርጉ ብየ ጠይቄም፤ አስቸግሬም አላውቅም። ለምን? ነፃነቴን አብዝቼ እሳሳለትአለሁኝ።   የማስበውን በነፃነት የሚያስገልጸኝ ይኽው መስመር ብቻ ነው። በሌላ በኩል የሰውን ልጅ ፈቅዶ ያድርገው እንጂ እኔ ልጫነው አይገባም የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ፌስቡክ ላይ ሼር እ...

"ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?"

ምስል
  ከአቶ ዋስ ያገኜሁት ትምህርት ነው። ይጠቅማል ትርጉም ማወቅ። " ማዕዶት" የሚል በጸጋየ ድህረ ገጽ አንድ መምሪያ ነበረኝ። እኔ በአማርኛ እርባታውን ተጠቅሜ ነበር ማዕዶት ያልኩት። ማዕድ የሚለውን ሥረ ቃል መነሻ አድርጌ የጥበብ ምግብ እንደማለት ነበር የተጠቀምኩት። በአማርኛ ፍሰት እኔ ተ ፊደልን ስለምወደው ሁልጊዜ ቃላትን ሳራባ ተን እጨምራለሁኝ። ሥርጉተ ወዘተ ነው ። የሆነ ሆኖ በግእዝ "መሻገሪያ" ማለት እንደሆነ ትርጉሙ ይገልፃል። አባ በጸሃ የሚባሉ የቄስ ትምህርት አስተማሪየ የቅኔም መምህር አንዱ መፃህፌ ላይ ግጥም ጽፌላቸዋለሁኝ። ትርጉሙን ዛሬ አገኜሁት "ደረሰ" ማለት ነበር ለካ።   "ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?"     "1 ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው 2 ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው። 3 ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው 4 ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው። 5 ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው። 6 ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት 7 ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው። 8 ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው። 9 አስካል፦ፍሬ ማለት ነው። 10 በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው። 11 መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው። 12 መንክር፦ልዩ ማለት ነው። 13 ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው። 14 ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው። 15 ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው። 16 ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው።ቅዱስ ለወንድ ነው። 17 ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው። 18 ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው 19 ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው። 20 ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው። 21 ጸገየ፦አበበ ማለት ነው 22 ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው። 23 ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው። 24 ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው። 25 ሰናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።...

#ኢሠመኮ የት ነው ያለው? የተቋሙ #ነፍሱ አለን? ለመሆኑ አዲሱ የኢሠመኮ አመራር #ይተንፍሳልን???

ምስል
  #ኢሠመኮ የት ነው ያለው? የተቋሙ #ነፍሱ አለን? ለመሆኑ አዲሱ የኢሠመኮ አመራር #ይተንፍሳልን ???    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።         የሁሉም በሽታ መነሻ የአንጀት ጉዳይ ይመስለኛል። አንጀት ደህና ከሆነ ሌላው አካልም ደህና ይሆናል ብየ አምናለሁኝ። የአንጀት በሽታ ከባድ እና ውስብስብ ነው። የአንጀት በሽታ መለያው ገረጭራጫ የሆነ #ባህሬ #ቢስም ነው። የአንጀት በሽታ #ጠቡ ከምግብ እና ከመጠጥ ጋር ነው። ካልተበላ እና ካልተጠጣ ደግሞ የሰው ልጅ ህይወቱ አይቀጥልም። አንድ የአንጀት በሽተኛ #ይርበዋል ። ሲበላ ደግሞ ስቃዩ ይጨምራል።    አንድ የአንጀት በሽተኛ ይጠማዋል #ሲጠጣ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ስቃይ ነው። አንድ የአንጀት በሽተኛ በተሟላ ኑሮ እንኳን እያለ #ያሻውን አይመገብም። ሁልጊዜ ታጥቆ ስንዱ ሆኖ #በጥንቃቄ ነው የሚኖረው። አንድ የአንጀት በሽተኛ ሲጓዝም ከመገብ ይልቅ #እርሃቡን ይመርጣል። ስቃዩ #አሰቃይ ነውና።   በዚህ ላይ የሃኪም ክትትል #መከልከል ፤ በተጨማሪም ውስብስቡ የእስር ቤት ህይወት ጋር #የአንጀት ህመም ፈታኝ ገጠመኝ ነው። ስቃዩን የሚያውቅ ያውቀዋል። እስር ቤት ሆኖ የአንጀት በሽተኛ መሆን የቅጣቱ መልክ እና ይዘት እጅግ #የከፋ ይሆናል።   አባት ታዲዮስ ታንቱም #የአንጀት በሽተኛ ናቸው። ቆሎ ብቻ ይመገቡ እንደ ነበር ባለፈው ከእስር ሲፈቱ ሲገልጹ ሰምቻለሁኝ። ቢያንስ እስር ቤት ለሚገኙ፤ በእጁ ላይ ባሉ ህሙማን #እርህርህና በአንድ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ ስለምን #እንዲሰደድ ይፈቀድለታል። አንድ ህሙም ስለምን ህክምና #ይነፈጋል ? ለምን? ሰው በአገሩ መንግሥት የህክምና አገልግሎት ሳያገኝ ተጨማሪ...

ለቀጣዩ ትውልድ ከልብ #ከውስጥነትም የማሰብ ጸጋ እንዲህም ይገለጣል።

ምስል
  • ለቀጣዩ ትውልድ ከልብ #ከውስጥነትም የማሰብ ጸጋ እንዲህም ይገለጣል።   https://www.bbc.com/amharic/articles/cwydn14d4pyo «ትራምፕ ኦቲዝም ያስከትላል ያሉትን መድኃኒት ነብሰ-ጡር ሴቶች እንዳይወስዱ አሳሰቡ» የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ዶክተሮች ለነብሰ-ጡር ሴቶች ታይሌኖል የተባለውን ማስታገሻ መድኃኒት እንዳይሰጡ አሳስበዋል።»   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     ይህ ለቀጣዩ ትውልድ ከልብ ከውስጥም የማሰብ ጸጋ በእጅጉ #መሰጠኝ ። ስለሆነም ሼር አደረግኩት። በትውልድ ጉዳይ ላይ ጤነኛ ሃሳብ የሚያቀርቡ ሁሉ ለእኔ #ብጹዓን ናቸው። እንደ #ተራራው #ስብከትም ነው የማየው።   ዛሬ በዓለማችን ጎልተው ከወጡት ችግሮች ውስጥ እጅግም አሳሳቢው ጉዳይ፤ የህፃናት ተስፋ አብረው #በሚወለዱ መንፈሳዊ፤ አካላዊ ጉዳቶች መሰቃየታቸው ነው። ይህ አዌርነስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ሴቶች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከውስጥ፤ ለውስጥ የተላከ #ቅዱስ #መልዕክት ነው።   በዘርፋ ላሉ ተመራማሪወችም፤ ፈላስፎች #አዲስ #በር የሚከፍት ይመስለኛል። በሉላዊ ደረጃ ከተደማጭ ሰብዕና የፈለቀ ሃሳብን #ባሊህ የሚሉ በርካታ ልባሞች ዓለማችን አላት እና።    ስለሆነም ኢትዮጵውያን ሃሳቡን #ከልብ #ቢያዳምጡት ጥሩ ይመስለኛል። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር ትጉህ አገልጋይ ቃለ ወንጌል።   በሁሉም ዘርፍ ከመውለድ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ጥንቃቄ የኢትዮጵያ ሴቶች እንዲያደርጉ ቤተሰብ፤ የትዳር አጋር፤ በዘርፋ ያሉ ባለሙያወች ሁሉ ሃሳቡን ሳያጣጥሉ ከ...