ልጥፎች

#በፋኖነት ተጠርጥረው ካቴና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን በርካታ ናቸው። ምህረት #ሰፊነትን ይጠይቃል።

  #በፋኖነት ተጠርጥረው ካቴና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን በርካታ ናቸው። ምህረት #ሰፊነትን ይጠይቃል።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፯   ፋኖነት የዘመናት ትውፊት ነው። ትውፊቱ በየዘመኑ ኢትዮጵያዊነትን የታደገ ባለውለታ ነው። በዘመነ አብይዝም በብልጽግና እና በህወሃት በነበረው የፋመ ጦርነት ፋኖነት ብልጽግናን የታደገ ባለውለታ ነበር። ከህወሃት ጋር ብልጽግና ባደረገው ድርድር ግን ተገፋን በሚል ስሜት ፋኖነት ዱር ቤቴ ካለ ዓመት አህዱ፤ ዓመት ክለቱ፤ ዓመት ሠለስቱ እያለ ቀጥሏል።    ፋኖነትን በሚመለከት #አውድዮ ሠርቼ ዩቱብ ቻናሌ ላይ ስላለ መዘርዘር አያስፈልገኝም። ዕይታየን የፈቀደ ዩቱብ ቻናሌ ላይ ያገኜዋል። የሆነ ሆኖ በተገፋን ስሜት፤ በተገለልንም የውስጥነት ቁጭት፤ በተጨማሪ የአማራ ፖለቲካዊ ጭብጦች ፖለቲካዊ ጉዳዮች፤ አጋጣሚውን በመዳፍ ለሚፈቅዱ ፖለቲከኞችም ሁነውበት፤ በፋኖ ምክንያት ብዙ የአማራ ልጆች ለካቴና ተዳርገዋል።   አሁን በቅርቡ በአንዱ የፋኖ ድርጅትን አሻም ያለ የካፒቴን ፻ ዓለቃ ማስረሻ ሰጤ ድርድር ከብልጽግና ጋር አድርጓል። በፋኖ ምክንያት የታሠሩትስ በዚህ ሂደት መፍትሄ ይሰጣቸው ወይንስ #አይሰጣቸው የሚታወቅ ነገር የለም።   ሁሉም እናት አለው እና የአማራ እናቶች ምህረትን፤ የምሥራች ዜና ይናፍቃቸዋል እና ፈጣሪ ይረዳቸው ዘንድ አምላኬን እለምናለሁኝ። በአፋር በርሃ ታስረው የነበሩ በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች ሁኔታም መረጃው የለም። በብልጽግና መንግሥት በይፋ የወጣውን ነው የለጠፍኩት። ምህረት #ሰፊነትን ይጠይቃል። ቸራችሁን ያሰማን። አሜን።   ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን...

#አባት እና የኢትዮጵያ #ፖለቲካ። ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ፤ የታሪክ ሙሁር፥ #ደፋር ተናጋሪ፤ ሞጋች፤ የአማራን መንፈሳዊ ጸጋ አክባሪ ናቸው አቶ ታዲዮስ ታንቱ

  #አባት እና የኢትዮጵያ #ፖለቲካ ።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፯   ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ፤ የታሪክ ሙሁር፥ #ደፋር ተናጋሪ፤ ሞጋች፤ የአማራን መንፈሳዊ ጸጋ አክባሪ ናቸው አቶ ታዲዮስ ታንቱ። ህይወታቸው ከካቴና ጋር የተዋደደ ነው። ምክንያቱም ንግግራቸውን፤ ዕምነታቸውን፤ ዕውቀታቸውን ለማስተላለፍ የግል ኤዲትንግን የማይሹ ግልጽ እና #ቀጥተኛ የሆነ ሰብዕና አላቸው።    እርግጥ ነው ቃለ - ምልልስ ሲደረግላቸው ጥንቃቄ የሚጠይቁ፤ #ጊዜ የማይፈቅድላቸው የአገላለጽ ልበለው የታሪክ ምስክርነትን አጉልተው እንዲያቀርቡ ሲፈለግ የሳቸው መዋለ ዕድሜ #ካቴና እንዲሆን ገጠመኙን አመቻቸ። #ዕውነት ተስማሚ ጊዜ ይጠይቃል። #ፍትህም ወቅት ነው የሚወስንለት ብዬ አስባለሁኝ። በእኔ ፍልስፍና ውበት እራሱን አካባቢ ይወስነዋል ብዬ አስባለሁኝ። ለሁሉም የመኖር ዘይቤወች ሬድሜድ ሊጠበቅ አይገባም ባይም ነኝ።   ድንጋጌሜ እንደ #ተርጓሚው ነው። እኛ የፍትኃብሄር ይሁን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ እና ሥርዓቱን ይሁን የአፈፃጸም ሂደቱን ከባለሙያወች በላይ #ጊዜ ሰፊውን የኃላፊነት ድርሻ ይወስዳል። በዘመኑ ባለው ሥርዓት ውስጥ ነው የሂደቱ ክንዋኔወች የሚወሰነው።    ሰሞኑን በዩክሬን እና በራሺያ ጦርነት ኢኮኖሚው የደቀቀው #ዘለንስኪዝምን ለማትረፍ አውሮፓ ማዕከል ላይ ራሺያ አምና፤ ተማምና ያስቀመጠችው ገንዘብ ለዩክሬን ይሰጥ የሚል ጠንካራ አቋም አዳምጫለሁኝ።    በዚህ ሃሳብ ይሁን ውይይት ውስጥ የየአገሮች ህገ - መንግሥት፤ ዓለም ዓቀፋ የፋይናስ ሥርዓቱ እና አፈፃጸሙን፤ #ዴሞክራሲ እና ተስፋውን፤ ዕውነት እና ሚዛናዊነት፤ ፋክት እና ትውልዱን ያሳየን ጊዜ ራዲዮሎጂ ነበር...

አባት #ታመዋል አሉ። ጋዜጠኛ፣ የታሪክ ጸሐፊ፥ ሞጋች እስረኛ አቶ ታዲዮስ ታንቱ ታመዋል አሉ።

ምስል
  አባት #ታመዋል አሉ። መረጃው ከአሹካ ፔጅ ነው ያገኜሁት። የእኔ ድንግል ትድረስላቸው። አሜን። እኔማ ምን #አቅም አለኝ????    #ሰሚስ ማን አለና????    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።      ሥርጉትሻ 2025/12/22።

#ትውልድን በልቅና የመቅረጽ #የጎጆ ተጋድሎ። #የ40 ልጆች ህሊና ባለውለታ ሦስት ጉልቻ።

ምስል
#ትውልድን በልቅና የመቅረጽ #የጎጆ ተጋድሎ። #የ40 ልጆች ህሊና ባለውለታ ሦስት ጉልቻ።    • ለእኔ ይህ ፕሮጀክት አልበርት አንስታይን በኢትዮጵያ ደግሞ የመፍጠር ትጋት ነው።   https://www.youtube.com/watch?v=zyrq6OmpTtE&t=262s «ከጎዳና ተነስቶ እዚህ መድረስ የሚያስደንቅ ነው ፥አዲሱን ቤታቸውን ጎበኘሁ #love #lovestory #ethiopianpodacst #ethiopia »   #ምዕራፍ ፲፯   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       የፈጣሪ ጥበብ የታዬበት ጎዳና። የአቶ ፍጹም ፍሰሃ፤ የመምህር ዳኒ እና የቅድስት ማርታ ዕውነተኛ ታሪክ ከድንቅ በላይ ነው። የትውልዱን ፈተናን የማሸነፍ ልዩ አቅም የሚያሳይ ታምራታዊ ሂደት ነው።   የፍፄን ታሪክ በስሱ ሰከላ አባይ ሚዲያ ላይ ይገኛል። የመምህር ዳኒ እና የቅድስት ማርታ ደግሞ ንቁ አንደበቶች ንቁ ፖድካስት ላይ ይገኛል። ሆሊውድ ቢያገኜው ይህን ታሪክ ሁሉ እላለሁኝ።   የትውልድ ጉዳይ በዝንቅንቅ ገጠመኝ የሚሞከር አይደለም። ከስሜታዊነት በፍጹም ሁኔታ የጸዳ፤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው አጽናኝ ውስጣዊነትን ይጠይቃል።   ሴት ወጣት በዚህን ያህል ጥንካሬ ማየት ለእኔ ፈውሴ ነው። ምህረቴም። የዘለው ተስፋዬ የሚረጋጋው ይህን የመሰለ ትንግርት በድርጊት ስመለከት ነው። ወጣቶቹ ጥሪያቸውን አላስተጓጎሉም።   ድፍረታቸው ይገርመኛል። ጥንካሬያቸው ይደንቀኛል። በዚህ ውስጥ ፈላስፊት ኢትዮጵያ ሳያት ተስፋዬ ያቆጠቁጣል። ተስፋዬ ተስፋን ያማትራል።    እነኝህ ጥንዶች ለ2018 የ12 መልቀቂያ ፈተና 40 ታዳጊወችን በሥነ ምግባር፤ በሞራል፤ በህሊና ብቃት፤ ...

«#ማቆም።» #የመንፈስ #ቅዱስ #ስጦታ። የመወሰን አቅም #በ፭ አመቷ ህፃን። #እኛንም #ታዘብኩት። #እኛንም #ፈራሁት።

ምስል
  • « #ማቆም ።» #የመንፈስ #ቅዱስ #ስጦታ ። የመወሰን አቅም #በ ፭ አመቷ ህፃን። #እኛንም #ታዘብኩት ። #እኛንም #ፈራሁት ። ሀ) የኮመዲ እሸቱ መለሰ የጥያቄ ኮድ ነው። ለ) ደግሞ የቅድስት ህፃን ኤልዳና ባዬ መልስ ይሆናል።    "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል። ሰው ግን አያስተውለውም።"       የእኔ በኽረ አጀንዳ ትውልድ እና እናትነት ነው። እመኑኝ ብዬ አላስቸግርም። ማታ ሸምቼ የማድረው ይህን የምክር አገልግሎት ነው። በዚህ ዓውድ የሰማዕት እናት ቅድስት እየሉጣ እና የህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ታሪክ ጋር ጭብጡ ተዋህደብኝ። ስለሆነም እኔ የተሰማኝን ውስጥ ላጋራችሁ ፈለግሁኝ። አደብ። አቅል። ተመስጦ። ተደማዊነት ይጠይቃል።     ግልቢያ፤ ግልብልብ የሆነ ነገር፤ ጥድፊያ እና ችኮላ ግጥሜ አይደሉም። የሆነ ሆኖ እናትነትም፤ ነገን ለማን የሚያስጨንቃችሁ ቅን ወገኖቼ ህሊናን የሚጠይቅ፤ የሚፈትሽ የቅድስት ኤልዳና ባዬን ቆይታ በዶንኪ ቲውም ትከታተሉት ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁኝ። ቤተመንግሥትም የኢትዮጵያው እንዲያዳምጠው እመኛለሁኝ።    ሥጦታ የመንፈስ ቅዱስ ነውና። ግን ውስጥን አጥርቶ ሊሆን ይገባል። ከአንደበት ውጪ ያሉ የአካላችን ክፍሎች ቋንቋ አላቸው። ወደ ጦርነቱ ቀጠና ቃለ ምልልሱ ሲገባ እንደ እናት ኮስተር ስትል፤ እንደ ምክር አገልግሎት ሰጪም ውሽክ ብላ ስትገልጽ የምህረት ዓዋጅ ኪኖ ነው። ማስተዋሉን ለሰጠው።   እራሱ ዶንኪ ቲዩብ መንፈስ ቅዱስ እንዳልራቀው ምልክት ነው። በእኔ በኩል ገንፎ ነገር፤ ተጨማሪ ማስታወቂወችን ደርቶበታል። ቢቆርጠው ኤዲት ቢያደርገው ምኞቴ ነው። ለነገሩ እኛን እንደ ሰው የሚቆጥር የለም። ፌስቡኩን ተከትዬው...