የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ #ዕውቅና የመስጠት። …
የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ #ዕውቅና የመስጠት። … • … በዛ ልክ ፍላጎትን የማደራጀት አስፈላጊነት ቁርጥ ይህን #ጭብጥ #ይመስላል ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ብዙ ዓይነት #መሻቶች አሉ። መሻቶቹ ዕውን ሊሆኑ የሚችሉት የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ #በሚፈቅደው ልክ ከተደራጁ ብቻ ይሆናል። አንዳንድ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሪያት #ዘለግ ያለ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ። አንዳንዶቹ ደግሙ #አጭር ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል። በዛ ልክ መሻት #ተደራጅቶ ከተመራ መሻት ከግብ ይደርሳል። በስተቀር መሻት #ተንሳፎ ይቀራል። #ፋንታዚ ሆኖ። ለዚህ ነው ደጋግሜ ስለዘመኑ ባህሬ ዕውቅና ስለመስጠት እና ማድመጥ እንደሚገባ አበክሬ የምገልጸው። የፈለገ #ዕንቁ ሃሳብ፤ ህዝብ ጠቀም፤ ተፈጥሮ ጠቀም፤ ሐሤት አፍላቂ፤ ሰላም ዓዋጅ ይሁን፤ የዘመኑ ባህሪ ካልፈቀደ #ውትልፍ የለም። ከዘመኑ ባህሬ ያፈነገጡ መሻቶች ሳይሳኩ ሲቀሩ ደግሞ የሥነ - ልቦና ችግር ይፈጥራል። ተስፋ #ቆራጭነት ይሰፍናል። ያለንበት የዘመኑ ባህሪ #ተለዋዋጭ ፤ #ቅጽበታዊ እና #ድንገተኝነት ይታይበታል። በባህሬው ልክ መፍጠን ካልተቻለ የተስፋ ሹልከት ይገጥማል። የዘመናችን ትንፋሹ የሚለካው በዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ ፍሬም ወርክ ነው። ባለፈው የአረብ ኢምሬት የተከታታይ ውሳኔወችን ያን መነሻ በማድረግም አጠናክሬ መፃፌ ይታወሳል። አንድ ጊዜ "ድርድር #ፖለቲካ ሆኖ" ደግሞ ተብሎ ስላቅ ቢጤ ነበር። ያሉትን የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ሳስብ ሁልጊዜ ይገርመኛል። አይደለም ለፖለቲካ ለትዳር፤ ለመኖር፤ ለዕውቀት፤ ለሽያጭ እና ለግዥ ድርድር አውራ ነው። ለዛውም በዚህ ቆሞ በማይጠብቅ ተለዋዋ...