ልጥፎች

አሽዋማ

 አሽዋማ     ልብ ሰንቆ ብሩህ ትውልድን ማሰብ አይቻልም። ሥርጉትሻ 2024/05/21

ማድመጥ

  ማድመጥ   እያራደ ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ህልም ነው። አድማጭ ፖለቲከኛ አለን??? ሥርጉትሻ 2024/05/21

ህም! #ህም። #ህም። "

  # ህም ! #ህም ። #ህም ።   "ገዢው የዞግ ድርጅት ተፎካካሪወችን፤ ተቃማዊወችን ማፈን መብቱ ነው። ሥራውም ነው እንደ ድከመት ሊታይ አይገባም" የሚል የአማራ ሊቅ ለዛውም የህግ አንበል? ምጥ ነው። እንዲህ ከተባለ #ዴሞክራቶች #ሪፓብሊካን ይፈኑን? #ያሳድዱን ? #ይገቱን ? የሚገርመኝ አወያዩም አልሞገተም። አንድ ሚዲያ ላይ ክፍል ሁለት ውይይት ላይ ነው ያዳመጥኩት። አወያዩም እንደ ቅዱስ ቁርባን ተመስጌን ብሎ የተቀበለው ይመስላል። የማይሰማ የለም። ውዶቼ ደህና ቆዩኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/2024

#እግዚአብሄር ይፈራ።

  #እግዚአብሄር ይፈራ። ፖለቲካ እግዚአብሄር አይደለም። ፖለቲካም ከእግዚአብሄር በላይ አይደለም። እኛን ጨምሮ ሊስተዋል የሚገባው ጉዳይ ፖለቲካ ስለ ሰው ነው። ሰው ደግሞ ከእግዚአብሄር በታች ነው። እግዚአብሄር አክላለሁ ብሎ መንጠራራት ቅስፈትን ያመጣል። መረገምንም ይቀልባል። ስለሆነም ሰውነትን ከፈጣሪ ጋር ማተካከል ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው። የላይኛው ፍርዱ ኃያል ነውና። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ግን እንዴት አደራችሁልኝ ጌጦቼ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ ሥርጉትሻ2024/23/05

ጠቅላይ ሚር አብይ እና ቅንነት #ህምም #እምም?

  ጠቅላይ ሚር አብይ እና ቅንነት #ህምም #እምም ? ቅንነት እኮ አዛኝነት፦ አጽናኝነት፤ አይዟችሁባይነት፦ ታጋሽነት፤ አወንታዊነት፤ ታማኝነት፤ ደግነት፤ አሳታፊነት፤ አድማጭነት፤ እራስን ገሳጭነት፤ ህዝብ አክባሪነት፤ ህዝብ ወዳጅነት፤ ወዘተ ነው። እና እሳቸው እና ቅንነት አብረው ኑረው የሚያውቁ አይመስለኝም። ክፋት ክፋነት ጭካኔ በሚመራት ኢትዮጵያ ቅንነትን እንደ መንገድ ማቅረብ የማይመጥን አቅርቦት ነው። ዕውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነትን መጥኖት አያውቅም። የላችሁም። ወና። ውዶቼ ቸር ዋሉልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 2024/05/23

እንዴት ናችሁ ወንድሜን አቤ ቶክቻውን የሞገትኩበት ሊንክ አኑሬያለሁ፨ ምክንያቱም ሞጋች ፎቶወችን መለጠፍ ስላልቻልኩ።-

    ·        # የኢትዮጵያ ሰነደቅ ዓላማ የነፃነት ካሪክለም ነው። ·        # ፋኖ የአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ነው። ሁለት ዕርዕሰ ጉዳይ በወጥ የወግ ገበታ አቀርባለሁ።       https://www.facebook.com/share/p/5Lvb8HF4a3mFPEoi/ እ ንዴት ናችሁ ወንድሜን አቤ ቶክቻውን የሞገትኩበት ሊንክ አኑሬያለሁ፨ ምክንያቱም ሞጋች ፎቶወችን መለጠፍ ስላልቻልኩ። -

ቢያንስ በሚያስደነግጠው

  እንዴት አደራችሁልኝ? ቢያንስ በሚያስደነግጠው የሰው ልጅ ድንገተኛ ችግር መደንገጥ እንዴት ቸገረን? እኛ ብቻ አይደለነም ዓለማችንም። ለዚህ ነው እኔ ክፋትን፤ ጭካኔን የሚመክት የፍቅር ተፈጥሮ ካሪክለም ይነደፍለት የምለው። ሰውና ሰው ምን እና ምን እዬተኳኳኑ ይሆን? ሥርጉትሻ 2024/05/21

አሽዋማ ልብ ሰንቆ

 አሽዋማ ልብ ሰንቆ ብሩህ ትውልድን ማሰብ አይቻልም። ሥርጉትሻ 2024/05/21

ማድመጥ እያራደ ዴሞክራሲ

  ማድመጥ እያራደ ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ህልም ነው። አድማጭ ፖለቲከኛ አለን??? ሥርጉትሻ 2024/05/21

ዕውን የኢትዮጵያ የመንግሥት አደረጃጀት #ፌድራሊዝም ነውን?

ምስል
  ዕውን የኢትዮጵያ የመንግሥት አደረጃጀት #ፌድራሊዝም ነውን? የት ቦታ ይሆን አማራ በቁጥሩ ልክ ውክልና ያለው። በራሱ በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ። ይህ የፋኖ #መቅድመ የመደራደሪያ አንኳር ነጥብ ሊሆን ይገባል። የፖለቲካ ውክልና #ይሉኝታ ሊገዛው አይገባም። ፈጽሞ። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።" የአማራ ህዝብ ደግነቱ፤ ችግርን ተሸክሞ መኖሩ መቀጫ እንጂ መመስገኛ፤ መከበሪያ አልሆነው። አሁን ያለው ሥርዓት ለዚህ የበቃው እኮ በአማራ ድምጽ ነው። ሌሎች የተከደኑ ጥረቶች ተዘሎ። ዕውነት ለመናገር አማራ እጁ አመድ አፋሽ ነው። ምንም ያልተደረገላቸው ጋዜጠኛ አቶ ታዲዮስ እና ወጣቱ ባለቅኔ በላይ በቀለ ለአብነት አሉ እንጂ።   ለእኔ ፌድራላዊት ኢትዮጵያ አይደለም። የፌዳሪዝልም ዕውነት ያለው አማራ ክልል ብቻ ነው። የቀደመው የመለሲዝም ክልሎች፤ የዛሬ የአብይዝም ተጨማሪ ክልሎች የፌድራሊዝም ጭላንጭል የለባቸውም። ድቅድቅ ጨለማ ናቸው። ገና ፊደል ያልቆጠሩ ልሙጥ። ልግጫ ነው። ደቡብ በጆግራፊ ነው የተደራጀው። ሌላው ደግሞ በተጫኝ #ዞጎች ። ዕውነቱ ይህ ነው።   አማራ ክልል አርጎባ፤ አገው፤ ኦሮሞ፤ ቅማንት ልዩ ወረዳ፤ ልዩ ዞን አላቸው። በራሳቸው የእኔ በሚሉትም አካል ይተዳደራሉ። የሚገርመው የፖለቲካ ሥልጣን ውክልናው ዞጋቸው ሌላ ሆኖ ኮታው ግን እንደ #አማራ ይወሰዳል። የነበሩት የአገር መሪወች ሁሉ ውህድ ማንነት የነበራቸው፤ ወጥም የሆኑት አጤ የኋንስን ሳይቀር አማራ የሚከሰሰው እሳቸውም አማራ እንደሆኑ ነው።   ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ኦሮሞ ናቸው ነው የሚባለው። አጤ ኃይለሥላሴም ቅንጣቢ የላቸውም ከአማራ ነው የሚባለው፤ ግን የአማራ ገዢ መደብ ይባላል። አጤ ሚኒሊክም ውህድ ማንነት የነበራቸው ናቸው።

መኖር ቀለበት ነው።

  መኖር ቀለበት ነው። ቸር እደሩልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 2024/05/2024

መስዋዕትነትን ማመጣጠን፦ መቀነስ በትግል ዓለም ውስጥ ሊታቀድ የሚገባው በኽረ ጉዳይ ነው።

  መስዋዕትነትን ማመጣጠን፦  መቀነስ በትግል ዓለም ውስጥ  ሊታቀድ የሚገባው በኽረ ጉዳይ ነው።   እንዴት ናችሁ የአገሬ ልጆች።   ደህና ናችሁ ወይ። በለውጥ ጊዜ የሚሆን ነው እዬተባል የትውልድ አጨዳ እና ጉስቁልና፤፦የኢኮኖሚ ድቀት እና እንግልት እንደ ጀብዱ ባይታይ ጥሩ ነው። ትግል ላይ ያለውም ቢሆን ትርፍ እና ኪሳራውን መዝኖ አትራፊነት ሚዛን እንዲፋ ጥበብን ማከል ይገባል። ሌላው አቅም የለሹም አቅም እንደሌለው አምኖ በፈቃዱ በሚችልበት መሳተፍ ብልህነት ነው። ምክንያቱም አዳዲስ ተቋም ተፈጥሮ ለስኬት ሳይበቃ ሲተን በዛ ውስጥ የፈሰው አቅምና የተገበረው ህይወት እውቅና ሊሰጠው ይገባል። በተጨማሪም ተደጋጋሚ ግድፈት እንዳይኖር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። አትራፊነት ከአመራራ አቅም ተመክሮ ይመነጫልና። የሆነ ሆኖ ለትግል፤ ለስኬት፤ ለሂደት እንደሚታሰበው ሁሉ ያ 50 ዓመት ሁሉ እንደ ጥንቸል ሙከራ የሚደረግበት ህዝብ መስዋዕትነቱ በቀነሰ መልኩ እንዲሆን ሊታሰብበት ይገባል።    በዚህ የ50 ዓመት ተጋድሎ ድልን በመቋደስ ብቻ ተጠቃሚው ደቡብ ነው። መልካም ነው። ግን ይህም ሊጠና ይገባል። እንደ አንድ ፕሮጀክት ምርምር ሊካሄድበት ይገባል። የትውልድ ጉዳይ የሚያገባው ሁሉ ይሰብበት። የደቡብ ብልህነት ጠቀሜታው ይጠና። በጥሞና። ማገዶነትም እስከመቼ ሊሉ ይገባቸዋል የተማገደውን የሚማገደውን ማህበረሰብ እንመራለን የሚሉ ወገኖቻችን። ለምሳሌ ኢዲዩ፤ ኢህአፓ፤ ሻብያ፤ ከፋኝ፤ ግንቦት 7 // እራሱ ኦህዴድ የትግል በዓቱ ስሜን ነው። ስሜነኞች ከትምህርት ተገልለው ሲታገሉ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ይማሩ ነበር። በኋላ የጠሚ ቦታ ለአቶ ገዱ፦ ወይንም ለዶር አንባቸው አልተሰጠም አቶ ደሳለኝ ኃይለማሪያም ጠሚር ሆኑ፤ በጦርነቱ ስንት ስማርት እንደወጣ ቀርቷል። የስሜን ህዝቡም ነበ

#ህም! #ህም። #ህም።

  #ህም ! #ህም ። #ህም ። "ገዢው የዞግ ድርጅት ተፎካካሪወችን፤ ተቃማዊወችን ማፈን መብቱ ነው። ሥራውም ነው እንደ ድከመት ሊታይ አይገባም" የሚል የአማራ ሊቅ ለዛውም የህግ አንበል? ምጥ ነው። እንዲህ ከተባለ #ዴሞክራቶች #ሪፓብሊካን ይፈኑን? #ያሳድዱን ? #ይገቱን ? የሚገርመኝ አወያዩም አልሞገተም። አንድ ሚዲያ ላይ ክፍል ሁለት ውይይት ላይ ነው ያዳመጥኩት። አወያዩም እንደ ቅዱስ ቁርባን ተመስጌን ብሎ የተቀበለው ይመስላል። የማይሰማ የለም። ውዶቼ ደህና ቆዩኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/2024