ልጥፎች

በነገረ ሐራ መሬት የነገ #ስጋቴን ብገልጽስ? #ነገን ሰላማዊ ተከታይ ስለማድረግ።

  በነገረ ሐራ መሬት የነገ #ስጋቴን ብገልጽስ?   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   #ጠብታ ።   በብልጽግና መንግሥት የተፈቀደለት ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በአፋር እንዳለ ሳድምጥ ቆይቻለሁኝ። ለሽምቅ ኃይሉ የፖለቲካ ክንፍ እንደተደራጀለትም ይገባኝ ነበር። ግን የእኔን የመረዳት መጠን መሬት ላይ ካለው የራሱ አካል ማረጋገጫ እስኪሰጥበት ድረስ ጸጥ ብዬ መጠበቅ ነበረብኝ።   ሰሞኑን በአርተስ የዜና ዕውጃ ከስምረት ፖለቲካል ፓርቲ በተገኜ መረጃ መሰረት የኃራው ታጣቂ ሸማቂ ኃይል ክንፋ እንደሆነ ዜናው ያትታል። እኔም አውቄው ስለነበር አላስደነገጠኝም። እንዲህ ገልፆ መናገር መልካም ነገር ነው።   #ጥቃትን መቅደም እና መቀደም።   በጣም ከሚያሳዝኑኝ የዓለም ማህበረሰብ ውስጥ ሊባኖናውያን አንዱ ናቸው። ሊባነን መንግሥት አላቸው። መንግሥታቸው ግን ለህልውናቸው ቀጣይነት የደህንነት ዋስትና የመስጠት አቅም የለውም።   አቅሙ ያለው ከመንግሥት ውጭ የሆነው #ሂዝቦላ ነው። የሂዝቦላ የፖለቲካ ክንፍ የሊባኖስ ማዕከላዊ መንግሥት ሳይሆን አገረ #ኢራን ናት። የኢዝቦላ ተቋማት ሁሉ በሊባኖሳውያን ውስጥነት ታዳሚወች ናቸው። ወጩ የሚሸፈንለት በኢራን መንግሥት ነው። የሂዝቡላ የፖለቲካ ያው ሃይማኖታዊ ነው፤ የታጣቂ ኃይል መሪ የኢራን መንግሥት ፖለቲካ ነው።   ሂዝቦላ ለሚወስደው እርምጃ ዋጋ የሚከፍለው ደግሞ መከረኛው የሊባኖስ ህዝብ ነው። ይህ ወጣ ገብ ሁነት የተፈጠረው ከጥንስሱ የሊባኖስ መንግስት የራሱን የፖለቲካ፤ የሚሊተሪ ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ባለመቻሉ ነው። የዘገዬ እና ፍዝ አቋም ያለውም ነው። አሁን የሊባኖስ ንጹኃን የሚከፍሉት ዋጋ ተመን ሊወጣለት የማይችል ነው። ከሊባኖ...

የጨዋ ህዝብን መንፈስ #ማዋለል ለምን? የመልሰን "#እናጤነዋለን" ቀጠሮው ለመቼ? #መወሰን ያቃተው ነፍስ መኖር አልጀመረም።

  የጨዋ ህዝብን መንፈስ #ማዋለል ለምን? የመልሰን " #እናጤነዋለን " ቀጠሮው ለመቼ? #መወሰን ያቃተው ነፍስ መኖር አልጀመረም።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ። "   #ምዕራፍ ፲፱።   ይገርመኛል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁልጊዜ #በቀጠሮ ። "ቁርጥ ያጠግባል" ይላል ባለ ቅኔው ጎንደሬ። ይህ አሳረኛ ህዝብ እየተገበረ አሳሩን አዬ። ፍቅሩን በንጹህ ልቡ ቢሰጥም፤ መዝኖ ቢያስተዳድርም ስቃዩ ሊያባራ አልቻለም። መሻልን ለማሳዬት ሆኖ መገኜት ነው። ኢትዮጵያን ያህል አገር ለመምራት እራስ ሲታጭ ምን አለኝ ብሎ መነሳትን በእጅጉ ይጠይቃል። አገር ሱቅ በደረቴ አይደለችም።   #እፎካከራለሁ ስትል አቅምህን ነው እምታቀርብ እንጂ አንደበትህን አይደለም። ሙሉ አገርን ለመምራት የሰከነ፤ የሚዘልቅም ራዕይ፤ የተሰናዳ የተግባር ቅደም ተከተል፤ ብቁ መንፈስ እና ተመክሮ ይጠይቃል። ከምትፎካከረው፤ ከምታጣጥለው፤ ከምታቃልለው ይሁን፤ ከምታከብረው የፖለቲካ ድርጅት መሻልህን ህዝብ መስማት ሳይሆን ማዬት ይሻል።   የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን ኢትዮጵያ ፍቅሩንም፤ ክብሩንም፤ ዕውቅናውንም ለሁሉም በገፍ ሰጥቶ አይቷል። ተፈታትሿል። የኢትዮጵያ ህዝብ ስልጡን ህዝብ ነው። ቅኑ እና ቀናው ህዝባችን ምን እንዳለው፤ ምን ደግሞ እንደሌለው ያውቃል። በዝምታው ውስጥ እራስ እግሩ ብልህነት #ተደላድሎ የሰከነበት ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍጹም አድማጭም ነው። ፍጹም ቻይ ህዝብም ነው።    የሚገርመኝ ግን በመንፈሱ ስለምን በተለያዩ በሚዋልሉ፤ በሚያረገርጉ፤ እርስ በርስ በሚጠላለፋ ሃሳቦች፤ መሻቶች እና ፍላጎቶች ይሁኑ አቋሞች ላይ #እንዲቀጣ እንደሚደረግ አላውቅም።    መወሰን ያቃተው ነፍስ መኖርን አልጀመረም። 15 ቀ...

"#ማንም ዜጋ መለመን የለበትም።" (ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ።) እንደ ምኞተወት ያድርግልን። አሜን።

  " #ማንም ዜጋ መለመን የለበትም።" (ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ።) እንደ ምኞተወት ያድርግልን። አሜን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   #እፍታ ።   ትሁታዊ ሰላምታ አቀርባለሁኝ ለቤተ - ቅንነት እንዴት አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ? ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ዙሪያ የምጽፈው። የሚሞገቱበት ጠፍቶ ሳይሆን፤ በሴት የፖለቲካ ሊቃናት ላይ በአንፃራዊነት ለዘብተኛ ነኝ። የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ሊቃናት አዋን መድረክ አግኝተው፤ ወጥተው እኔ ታክዬ #ቲካቲካ የተገባ ነው ብዬ አላምንም።    የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሴቶችን ተጫኝ፤ የገበርዲን እና የከረባትም ስለሆነ ንጥረ ነገር የጎደለበት፤ የእናታዊ ጸጋ የተነነበት ስለሆነ ስኬቱም ሲትበሰበስ ነው የኖረው። በሰሞኑ የምግብ ማዕከል ምርቃት እና ንግግር መነሻነት ዛሬ የተሰማኝን ለመግለጽ አህዱ ብያለሁኝ።   #መቅድም ።   ከንቲባ አዳነች አበቤ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ "ድረሽልኝ" ባሏቸው የኃላፊነት ደረጃወች ሁሉ በመገኜት የልብ አድራሻቸው ብቻም ሳይሆኑ፤ የቅርብ፤ የሚያምኑት፤ የማይጠረጥሩት ሰብ ከኖራቸው፤ ከንቲባ አዳነች አበቤ ነው ሊሆኑ የሚችሉት።   በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃወች ፈቃዳቸውን በመፈጸም ቁጥር ፩ የጠሚሩ አጋር ይመስሉኛል - የዛሬዋ የመዲናችን የአዲስ አበባ ከንቲባ። ናቸው አላልኩም። ሊሆኑ ይችላሉ፤ ይመስሉኛል ነው ያልኩት። እምከታተለው በርቀት ስለሆነ።    #እንደ በር።   ዕድሜ ልኩን ታግሎ ኦነግ አንዲት አቅም ያላት አንስት ፖለቲካ ማብቀል አልቻለም። ኦፌኮ ጋር ፕሮፌሰር ዶር. መራራ ጉዲናን በአካል ሳገኝ በወጣቶች ፖለቲከኞች...