የመቶ አርባ ደቂቃ «ሁለት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ» በቬንዙላ ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ ራሱን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የደገመ ይመስለኛል።
የመቶ አርባ ደቂቃ «ሁለት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ» በቬንዙላ ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ ራሱን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የደገመ ይመስለኛል።
• የእኔ ዕይታ ሂደቱ ፍትሃዊ ነው ወይስ አይደለም የሚለው አይደለም። "ኦፕሬሽን አብስሉት ሪዞልቭ" (Operation Absolute Resolve) የኦፕሬሽኑ ቁመና የሰጠኝን ንድፈ ሃሳባዊ ግብረ መልስ የክንውን አቅም ነው የገለጽኩት። የዕይታየ መነሻ የBBC ዘገባ ነው።
• ጫናን በሚመለከት፤ ወጀብ የሌለው፤ ሪስኩ የነጠፈበት የፖለቲካ ፍላጎት የለም። ፍትጊያ አለ። ፋክክር አለ። ሪስክም ይኖራል። በዚህ ውስጥ አልፎ ስኬቱ ዛን ሊመታ ስለመቻሉ ነው የቅድሚያ አትኩሮት ሊሆን የሚገባው። በአንድ ኦፕሬሽን ውስጥ መንሸራተትም ሊገጥም ይችላል። የመሪነት ልቅና የሚያስፈልገው ተዚህ ላይ ነው።
"አሜሪካ የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት የያዘችበት ዘመቻ እንዴት ተከናወነ?"
«አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።» አሜን።
ይህን ረቂቅ ኦፕሬሽን ለውይይት ማቅረብ ከባድ ይሆናል። ፕሮሲጀራል ሂደቱን ህግ ተከትለን እናስኬደው ቢባል መስዋዕትነቱም ይከፋል፤ ግቡም ጎዳና ተዳዳሪ ይሆናል። የየትኛውም ከፍተኛ ኦፕሬሽን ስኬት ሚስጢር ነው። ሚስጢሩን ትንፋሽ እንስጠው ቢባል አይደለም ስኬት ራስን የማዳን ሂደቱ ይዝረከረካል ከምል ይዝለገለጋል።
አንድ ልዩ ኦፕሬሽን የቅድሚያ ቅድሚያ እራሱን የመጠበቅ፤ እራሱን የማዳን ቁመና ሊኖረው ይገባል። ለዚህ መሰል የበቃ የመምራት አቅም ደግሞ መሰጠትን ይጠይቃል።
ይህ ጥንቁቅ ኦፕሬሽን "ኦፕሬሽን አብስሉት ሪዞልቭ" (Operation Absolute Resolve) የትራንፒዝምን ሌላ ብልህ እና የመፈጸም የክህሎት ከፍ ያለ ደረጃ ገፅታን በጥልቀት ያሳያል።
የልዩ ኦፕሬሽን የትልም፤ የሃሳብ ቅንጅ፤ የታክቲክ እና ስትራቴጂ ውህደት፤ የአትኩሮት እና የጥንቁቅነት ጥራት፤ የክህሎት እና የሥልጣኔ የማኔጅመንት ስምምነት፤ የዓላማ እና የስኬት የአፈፃጸም ልቅና፤ ሃሳብን በውል አደራጅቶ ሃሳብን በዲስፕሊን የማስገዛት ልዕልና በጉልህ የታየበት የዘመናችን አንቱ ኦፕሬሽን ነው። አዲስ ክስተት ነው። «ጀብዱ ነው፤ ጀግንነት ነው» ልላችሁ አልችልም። የመወሰን ልዩ አቅም፤ የአፈፃጸም ብልህነት፤ ሚስጢርን ጠብቆ የመምራት ልዩ ክህሎት ግን አይቸበታለሁኝ።
እንኳንስ በሌላ አገር፤ በራስ የግዛት አስተዳደር ያለውን ምስቅልቅል ለማስቆም መምራት በማይቻልበት ሁነት በሌላ አገር ግዛት ይህን የመሰለ ኪኖ የሚመስል ትዕይንት ሲፈጸም ሳይ የመሪነት አቅም ከሥልጣኔ ወይንስ ከቅብዓ? ሊመነጭ ቻለ የሚል እኔው፤ እኔን እየሞገተኝ ይገኛል።
ወይንስ የቅብዓ የክት እና የዘወትር ደረጃ ይኖረው ይሆን? መልስ አላገኜሁለትም። የሆነሆኖ ሰሞኑን ሁለት የአፍሪካ መንግሥታት ለአሜሬካ ዜጎች የጉዞ እገዳ እንደጣሉ ዘገባ አይቻለሁ። ተኝተው ቢያስቡበት ጥሩ ይመስለኛል። አንዷ ቡርኪ ናት። መሪነት ጊዜን በማስተዋል መምራት ይጠይቃል።
ይህ ብቻ ሳይሆን ሱማሌያዊቷ ፖለቲከኛ ከትራንፒዝም ጋር የገጠሙት ፋክክር መብትን በአግባቡ ማስተዳደር ካልተቻለ ጦሱ ለፍሪካውያን ቀጣይ የትውልድ የተሳትፎ መብት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፋ የሚችሉ ህግ እስከማውጣት ድረስ ሊያደርስ የሚችል፤ የታዳጊወችን ተስፋ ዘላቂ ማዕቀብ የሚስጥል ሊሆን እንዳይችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
ስሜትን - መቆጣጠር። ፍላትን - ማብረድ። ኮንፊደንስን በቅጡ ማስተዳደር ይገባል። ቃላት አመራረጥ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። የመብት እና የግዴታ ጣሪያና ግድግዳም ማወቅ ይገባል። «ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም።»
በሌላ በኩልም የትኛውም አገር ከአፍሪካውያን የሚያገኜው ጠረንም ሊጎድልበት አይገባም። ፖለቲከኝነት ድፍረት ብቻ ሳይሆን ሁለገብ ስኩን ብልህነትን ይጠይቃል።
• ዕይታየን ስከውነው።
የነፃነትን ወሰን ይሁን ደንበር እንደምን መወሰን እንደሚቻም ሌላ አዲስ የምርምር ማዕከል የሚጠይቅ ይመስለኛል። የንጉሦች ንጉሥ የዓጤ ቴወድሮስን መራራ ስንብት ወደ ፊት እናምጣ እና ከውስጣችን ጋር እናወያዬው ብለን ብንፈቅድ፤ የብፁወቅዱስወሰማዕት የነገረ አቡነ ጴጥሮስ ቀንን አቅርበን ብንመረምረው ናሳ ከተደራጀበት ሚስጢር በላይ ኢትዮጵያን የቁምነገር ማሳ የማድረግ ዊዝደም ይታፈስበታል። ጥያቄው ወደ እራሳችን ውስጥነት የመመለስ ህሊናዊ አቅም አለን ወይ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04-01-2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
***************************************************
• «አሜሪካ የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት የያዘችበት ዘመቻ እንዴት ተከናወነ?»
"የአሜሪካ ሰላዮች ለወራት ያህል የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ሲከታተሉ ቆይተዋል።"
"የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እንደሚገልጹት፤ የ63 አመቱ ፕሬዝዳንት የት እንደሚተኙ፣ ምን እንደሚመገቡ፣ ምን እንደሚለብሱ እና "የቤት እንስሳቶቻቸውንም" ጭምር ክትትል ሲደረግባቸው ነበር። ይህንን ክትትል የሚያደርገው ደግሞ በቬንዙዌላ መንግስት ውስጥ ያለ አንድ ለአሜሪካ መንግሥት የሚሰራ ምንጭን በአባልነት የያዘ ትንሽ ቡድን ነው።"
"ከዚያም፤ በታህሳስ መጀመሪያ "ኦፕሬሽን አብስሉት ሪዞልቭ" (Operation Absolute Resolve) የሚል ስያሜ የተሰጠው ዘመቻ እቅዱ ተነድፎ ተጠናቀቀ። ወራትን የፈጀው እቅድ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎበት የተዘጋጀ ነው።"
"በእቅድ ዝግጅቱ ውስጥ የተሳተፉ የአሜሪካ 'ኤሊት' ወታደሮች፤ በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ የሚገኘውን የፕሬዝዳንቱን ደህንነቱ የተጠበቀ ማቆያ (safe house) አስመስለው በመገንባት ጭምር በምን አይነት መንገድ ማዱሮን እንደሚይዙ ተለማምደዋል።"
"ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ባልታየ አኳኋን ዋሽንግተን በላቲን አሜሪካ ልታደርግ ያቀደችው ይህ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት፤ በሚስጥር የተያዘ ነበር። የአገሪቱ ኮንግረስ ስለ እቅዱ አስቀድሞ ገለጻ አልተደረገለትም፤ ምክረ ሀሳቡንም አልተጠየቀም።"
"የዘመቻው ሂደት በዝርዝር ተዘጋጅቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ጥቃቱን ለመሰንዘር አመቺ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ መጠበቅ ነበረባቸው። በተቻለ ሁኔታ ኦፕሬሽኑ በድንገት እንዲፈጸም ፍላጎት እንደነበራቸው ባለስልጣናቱ ቅዳሜ ዕለት ተናግረዋል።"
"ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከአራት ቀናት በፊት ኦፕሬሽኑ እንዲፈጸም ፈቃድ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፤ የተሻለ የአየር ሁኔታ እና አነስተኛ ደመና የሚኖርበትን ጊዜ ለመጠበቅ ሲባል ጊዜው ተራዝሟል።"
"የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን የሆኑት ጄነራል ዳን ኬን ቅዳሜ ጠዋት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ "በገና እና በአዲስ ዓመት ሳምንታት፤ የአሜሪካ ጦር ሰራዊት አባላት ተገቢው ሁኔታ እስኪመቻች እና ፕሬዝዳንቱ ወደ እርምጃ እንድንገባ ትዕዛዝ እስኪሰጡን ድረስ በትዕግስት እየተጠባበቁ ነበር" ብለዋል።"
• "በሌሊት የተከናወነው ኦፕሬሽን"
"ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኦፕሬሽኑ እንዲጀመር ፈቃድ የሰጠውን ትዕዛዝ ያስተላለፉት በቬንዙዌላ አቆጣጠር ደግሞ ሌሊት ላይ ነበር። ፕሬዝዳንቱ፤ "ከአራት ቀናት በፊት፣ ከሶስት ቀናት በፊት፣ ከሁለት ቀናት በፊት ልንፈጽመው ነበር። ከዚያም በድንገት ሁኔታዎች ተመቻቹ። እኛም 'ጀምሩ' አልን" ሲሉ ከኦፕሬሽኔ በኋላ በፎክስ ኤንድ ፍሬንድስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።"
"ትራምፕ ትዕዛዙን ያስተላለፉት በቬንዙዌላ ሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት ቀደም ብሎ በመሆኑ ሠራዊቱ አብዛኛውን እንቅስቃሴውን በጨለማ እንዲያደርግ አስችሎታል። የአሜሪካ ወታደሮች በአየር፣ በየብስ እና በባህር ተንቀሳቅሰው ሁለት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ የፈጀ ኦፕሬሽን ፈጽመዋል። የኦፕሬሽን መጠን እና የተከናወነበት ሁኔታ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ሊባል የሚችል ነው።"
"ይህ የአሜሪካ እርምጃ በቀጣነው ከሚገኙ በርካታ ኃይሎች ውግዘት የደረሰበት ወዲያውኑ ነበር። የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ፤ የቬንዙዌላው መሪ በኃይል መያዛቸው "ለመላው ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሌላ እጅግ አደገኛ አካሄድ" ነው ብለዋል።"
"ትራምፕ የኦፕሬሽኑን ሂደት የተከታተሉት በዋይት ሃውስ 'ሲቹዌሽን ሩም" አልነበረም። ይልቁንም በፍሎሪዳ ፓልም ቢች በሚገኘው ማራ ላጎ ክለባቸው ውስጥ በአማካሪዎቻቸው ተከበው ሂደቱን በቀጥታ ስርጭት ተከታትለዋል። የሲአይኤ ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮም ከጎናቸው ነበሩ።"
"ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ከኦፕሬሽኑ በኋላ ሲናገሩ "ለማየት የሚያስደንቅ ነገር ነበር" ብለዋል። "የተፈጠረውን ተመልክታችሁ ቢሆን ኖሮ፤ ማለቴ ልክ እንደ ቴሌቪዥን ድራማ ነበር የተመለከትኩት። ፍጥነቱን እና የተወሰደውን የኃይል እርምጃውን ብታዩት... በጣም የሚያስገርም ነው" ብለዋል።"
"ባለፉት ወራት፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማዱሮን በዕፅ ዝውውር እና በዕፅ-ሽብርተኝነት (narco-terrorism) ሲከስሱ እንዲሁም በቀጣናው እፅ ያጓጉዛሉ የተባሉ በአስር የሚቆጠሩ ትናንሽ ጀልባዎች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ከርመዋል።"
"ከዚህ ጊዜ አንስቶም በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ተሰማርተዋል። የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ እና ከአስር ከሚበልጡ የጦር መርከቦችም ተንቀሳቅሰዋል። ባላፉት አስርት ዓመታት የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል በዚህ ደረጃ በቀጠናው ሲሰፍር ይህ የመጀመሪያው ነው።"
"ኦፕሬሽን አብስሉት ሪዞልቭ" እየተካሄ ስለመሆኑ የጠቆሙት የመጀመሪያ ምልክቶች የታዩት ሰማይ ላይ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደሚናገሩት፤ በሌሊቱ በተካሄደው ኦፕሬሽን ላይ ቦምብ ጣዮችን፣ ተዋጊ ጄቶችን እና የስለላ (ሰርቬላንስ) አውሮፕላኖችን ጨምሮ ከ150 በላይ ተዋጊ አውሮፕላኖች ተሰማርተዋል።"
"ትራምፕ፤ "[አውሮፕላኖች] ያረፉበት መንገድ፣ የተዋጊ አውሮፕላኖች ብዛት፤ ሙሉ እንቅስቃሴው እጅግ ውስብስብ ነበር" ሲሉ ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል። "ሊፈጠር ለሚችለው እያንዳንዱ ሁኔታ ተዋጊ ጄት ነበረን" ሲሉም አክለዋል።"
"በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ በካራካስ ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል፤ በከተማዋ ሰማይ ላይ የጭስ ደመና ታይቷል። የቢቢሲ ዘጋቢ አና ቫኔሳ ሄሬሮ፤ "ከፍተኛ ድምጽ ሰማሁ፤ ከፍተኛ ፍንዳታ" ስትል ሁኔታውን ገልጻለች።"
"መስኮቶቹን በሙሉ አንቀሳቀሳቸው። ወዲያውኑ ሙሉ እይታ የሚጋርድ የጭስ ደመና ተመለከትኩ" ብላለች። አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች በተከማዋ በሙሉ ሲበርሩ ይታዩ እንደነበረም ጠቅሳለች።"
"በአገሪቱ ተፈጸውን ሁኔታ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት በአጭር ጊዜ ውስጥ ነበር። ተዋጊ አውሮፕላኖች በሰማይ ላይ እየበረሩ እንዲሁም ከፍንዳታ በኋላ የተፈጠረውን ሁኔታ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ተለቅቀዋል። ከእነዚህ ቪዲዮዎች አንዱ ላይ ከፍንዳታ የተነሳ የሚመስል ጭስ እየተነሳ ሳለ፤ ዝቅ ብለው የሚበሩ ሄሊኮፕተሮች ስብስብን አሳይቷል።"
"ዳኔላ የተባለች የአይን እማኝ፤ "ከሌሊቱ 7 ሰዓት 55 ደቂቃ አካባቢ ከፍተኛ የፍንዳታ እና በካራካስ ሰማይ የሚበሩ አውሮፕላኖች ድምጽ አነቃን። ሁሉም ነገር ፍጹም ጨለማ ውስጥ ነበር፤ ብርሃን የሚታየው በአቅራቢያችን የሚፈጸሙ ፍንዳታዎች ከሚፈጥሩት ብልጭታ ብቻ ነበር" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።"
"ቢቢሲ ቬሪፋይ (BBC Verify) የትኞቹ ቦታዎች ዒላማ እንደተደረጉ በትክክል ለመለየት በካራካስ ዙሪያ የነበረውን ፍንዳታ፣ እሳት እና ጭስ የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮዎችን መርምሯል። እስካሁን ድረስም ጥቃት የተፈጸመባቸው አምስት ቦታዎች ተረጋግጠዋል።"
"ከእነዚህም መካከል፤ የጄኔራሊሲሞ ፍራንሲስኮ ደ ሚራንዳ አየር ኃይል ጣቢያ፣ ላ ካርሎታ ተብሎ የሚጠራው የአውሮፕላን ማረፊያ እና የካራካስ ዋነኛ የካሪቢያን ባህር መተላለፊያ የሆነው ላ ጉዋይራ ወደብ ይገኙበታል።"
"ከጥቃቶቹ መካከል የተወሰኑት የአየር መከላከያ ስርዓቶችን እና ሌሎች ወታደራዊ ዒላማዎችን ያነጣጠሩ እንደነበሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ትራምፕ፤ ኦፕሬሽኑ ከመጀመሩ በፊት አሜሪካ የካራካስን የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳቋረጠች ጠቁመዋል። ይህ እርምጃ እንዴት እንደተከናወነ ግን በዝርዝር አልገለጹም።"
"ባለን የተለየ የሙያ ብቃት የተነሳ የካራካስ መብራቶች በአብዛኛው እንዲጠፉ ተደርገው ነበር" ብለዋል።"
• "እየመጣን እንደሆነ ያውቁ ነበር"
"የአሜሪካ ጦር ወደ ካራካስ የገባው በከተማዋ ዙሪያ ፍንዳታዎች እየተሰሙ በነበረበት ወቅት ነው። በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ምንጮች እንደሚናገሩት ኦፕሬሽኑ ውስጥ "የኤሊት ዴልታ ፎርስ" እንዲሁም የአሜሪካ ከፍተኛ ልዩ ተልዕኮ አሃድ አባላት ተሳትፈዋል።"
"በከፍተኛው ደረጃ ታጥቀው የነበሩት እኚህ ወታደሮች፤ የማዱሮን ደህንነቱ የተጠበቀ ማቆያ የብረት በሮች ለመቁረጥ የሚያስችላቸውን የእሳት ማቅለጫ ይዘው እንደነበር ተነግሯል።"
"እንደ ጄነራል ኬን ገለጻ፤ ወታደሮቹ ወደ ማዱሮ መገኛ የደረሱት ሌሊት ስምንት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመረ ከአጭር ጊዜ በኋላ ነው። ትራምፕ ፕሬዝዳንቱ የነበሩበትን ቤት በካራካስ እምብርት ያለ "ምሽግ" ሲሉ ገልጸውታል። "በተጠንቀቅ ሁኔታ ላይ ሆነው እየጠበቁን ነበር። እየመጣን እንደሆነ ያውቁ ነበር" ብለዋል።"
"ወታደሮቹ እንደደረሱ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። ከአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች አንዷ ተመታ የነበረ ቢሆንም መብረር አላቆመችም። ጄኔራል ኬን "በቁጥጥር ስር የማዋል ኃይሉ ወደ ማዱሮ ግቢ በመውረድ በፍጥነት፣ በቅልጥፍና እና በከፍተኛ ስነ ምግባር ተንቀሳቅሷል" ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ በበኩላቸው፤ "ሰብሮ ለመግባት ወደማይቻልባቸው ቦታዎች ሰብረው ገቡ፤ የብረት በሮቹ የተቀመጡት ለዚህ ተብሎ ነበር" ብለዋል።"
"አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ስለ ዘመቻው ለኮንግረስ አባላት ማሳወቅ ጀመሩት የማዱሮ ባለቤት ሲሊያ ፍሎሬስም ጭምር የተያዙበት ይህ ኦፕሬሽን እየተከናወነ ሳለ ነው። ይህ የፕሬዝዳንት ትራንፕ ውሳኔ በተወሰኑ የኮንግረስ አባላት ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።"
"በሴኔት የዴሞክራቶች መሪ የሆኑት ቸክ ሹመር፤ "በግልጽ ልናገር፤ ኒኮላስ ማዱሮ ህገ-ወጥ አምባገነን ነው። ነገር ግን ከኮንግረስ ፈቃድ ውጭ እና ቀጣዩ ሁኔታ ምን እንደሚሆን የሚያሳይ አስተማማኝ እቅድ ሳይኖር ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ግድየለሽነት ነው" ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።"
"ሩቢዮ ቅዳሜ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ አስቀድሞ ኮንግረስን ማሳወቅ ኦፕሬሽኑን ለአደጋ ያጋልጠው ነበር ብለዋል። ትራምፕም፤ "ኮንግረስ መረጃ የማሹለክ ዝንባሌ አለው" በማለት አክለዋል። ኤሊት የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ማዱሮ ግቢ ሲጎርፉ፤ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ወደ መሸሸጊያው ክፍል ለመሸሽ መሞከራቸውን ትራምፕ ተናግረዋል። "ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ ለመሄድ እየሞከረ ነበር፣ ነገር ግን ቦታው ደህንነት ያለበት አልነበረም፤ ምክንያቱም በ47 ሴከንድ ውስጥ በሩን እናፈነዳው ነበር" ብለዋል።
"ትራምፕ አክለውም "በሩ ጋ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ሊዘጋው አልቻለም፤ በፍጥነት ስለደረሱበት ወደ [ክፍሉ] መግባት አልቻለም" በማለት ተናግረዋል። በአውሮፓውኑ 2013 ወደ ስልጣን የመጡት አምባገነኑ ማዱሮ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቃወሞ ኖሮ አሜሪካ ልትገድላቸው ትችል እንደነበር የተጠየቁት ትራምፕ፤ "ሊሆን ይችል ነበር" ብለዋል። በአሜሪካ በኩል "ጥቂት ሰዎች" ቢመቱም የተገደለ የአሜሪካ ወታደር እንደሌለ ገልጸዋል። የቬንዙዌላ ባለስልጣናት ጉዳት ስለመድረሱ እስካሁን አላረጋገጡም።"
"አሜሪካ ይህንን ኦፕሬሽን ከመፈጸሟ አስቀድሞ፤ ማዱሮን ለመያዝ የሚያስችል መረጃ ለሰጠ ሰው የ50 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጅታ ነበር። ከዚህ ኦፕሬሽን በኋላ ግን የአሜሪካ ወታደሮች ማዱሮን እና ባለቤታቸውን አሳፍረው ከቬንዙዌላ ግዛት ወጥተዋል። ቀጥታ ወደ ኒው ዮርክ የተወሰዱ ሲሆን በዚያም የወንጀል ክስ እንደሚመሰረትባቸው ይጠበቃል።"
"ኦፕሬሽኑ ከተከናወነ ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ ትራምፕ አሜሪካ የቬንዙዌላውን መሪ መያዟን አስታወቁ። "ማዱሮ እና ባለቤቱ በቅርቡ የአሜሪካ ፍትህን ሀያልነት ይጋፈጣሉ" ብለዋል።"

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ