ልጥፎች

ተጽዕኖ ፈጣሪነት ማለት መሪነት ማለት አይደለም፤ መሪነት ግን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ሊሆን ይችላል። Einfluss ist...

ምስል

የክፋ ሃሳብ ደንበኛ ላለመሆን ወሳኙ የራስ ፈቃድ ውሳኔ ነው። Es ist eine Entscheidung des Eige...

ምስል

ለአቅም አቅም የመሆን ብልህነት። Die Weisheit, es sich leisten zu können.

ምስል
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ቂመኛ፤ አድመኛ፤ አግላይ፤ አቅምን አማቂ፤ የአቅም አጋች፤ አቅም አሳዳጅ፤ እርምትን እንደ ጦር የሚፈራ፤ አቅም በታኝ፤ አቅም አባካኝ፤ አቅምን አምክሎ የመምራት አቅም የሌለው ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል አዲስ የፖለቲካ የባህል ለውጥ በእጅጉ ያስፈልገዋል።  

"የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ማዕከላዊው መንግሥት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል የሚፈፀሙ እገታዎችን እንዲያስቆም ጥሪ አቀረበ። bbc

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cgq2pq1e7ppo   3 መስከረም 2024 "የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ ) ማዕከላዊው መንግሥት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል የሚፈፀሙ እገታዎችን እንዲያስቆም ጥሪ አቀረበ። በሁለቱ ክልሎች ያሉ የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎችን እየተከታተልኩ ነው ያለው ኮሚሽኑ፣ በተለይ እገታን በተመለከተ የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች ተከትሎ ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ አሳውቋል። ኮሚሽኑ ይህን መግለጫ ያወጣው በጎንደር ከተማ አንዲት የሁለት ዓመት ሕፃን በአጋቾች መገደሏን ተከትሎ በከተማዋ ቁጣ መቀስቀሱን በተሰማ ማግስት ነው። ኮሚሽኑ በለቀቀው መግለጫ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ካለው የትጥቅ ችግር ጋር በተያያዘ በአንዳንድ አካባቢዎች የሕግ ማስከበሩ በመላላቱ ሰላማዊ ዜጎች በታጣቂዎች፣ በተደራጁ ቡድኖች እና በአንዳንድ የመንግሥት የፀጥታ አካላት የሚደርስባቸው እገታ ተባብሷል ብሏል። ኢሰመኮ በምርመራው እንደተመለከተው አጋቾች፤ ሰላማዊ ዜጎች ጉዞ ላይ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው አልያም ሥራ ላይ ሳሉ ታፍነው ተወስደው የማስቀለቀቂያ ገንዘብ ይጠይቃሉ። አክሎም ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ ሰዎችን ግድያን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ገልጿል። እገታዎች ለታጣቂዎች የገንዘብ ምንጭ ሆነዋል ያለው ኮሚሽኑ፣ በሌላ ወቅት ደግሞ ለበቀል ማስፈፀሚያ፣ ለፖለቲካ ዓላማ እንዲሁም የታገተን ሰው ለማስለቀቅ ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሆኑ አትቷል። በተለይ በሁለቱ ክልሎች በተንሰ