#አፍሪካዊው #የፈረንሳይ ቡድን፣ #አውሮፓዊውን #የሞሮኮ ቡድን ሁለት #ለልሙጥ ሸኜው።

 

ፈረንሳይ 2: ሞሮኮ 0
 
'አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 May be an image of soccer, football and text that says 'FIFA FA'
 
የአፍሪካን ድጋፍ ያላስፈለጋቸው የሞሮኮ መንፈስ ዛሬ የፊፋው ፕሬዚዳንት በተገኙበት ወሳኝ የጨዋታ ምዕራፍ በተካሄደው ውድድር በፈረንሳይ #ጥንግ ድርብ ነጥብ ሞሮኮወችን #በልሙጥ ተሸኝተዋል።
 
ፈረንሳዮች በጨዋታ መግቢያ ደቂቃወች ላይ የሞከሯቸው ሁለት የግብ ጥረቶች ባይሳኩም።
 
በተጨማሪም የቅጣት ምት አግኝቶ ማፔ #ቢስትም፣ ማፔ ይህን አካክሶ #በ59ኛው ደቂቃ ላይ ተስፋ ቀና ብሎ ፍሰሃውን ሲያውጅ #በ65ኛው ደቂቃ ላይ ለጥንድ ድል በቁና እና ድሉ ተበሰረ። ለዛውም በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ።
 
በውነቱ በፈረንሳይ በኩል ብዙ ወርቅ የግብ ዕድሎች ቢሳኩ ኖሮ #አውሮፓዊው የሞሮኮ ቡድን መንፈሱ ለረጅም ጊዜ #ለሽ ይል ዘንድ ይፈረድበት ነበር።
 
የሞሮኮ ቡድን እኔ እንደ ገመትኩት አስልተው የገቡት መደበኛውን የጨዋታ ጊዜ ተራዝሞ፣ ተጨማሪ ደቂቃ ታክሎ፣ #በፔናሊቲ መለያዬትን #የናፈቁ ይመስላሉ።
 
#የረባ የጎል ጥረት አላደረጉም። ጨዋታው በፈረንሳይ የበላይነት #ፈርሰስ ብሎ፣ #ተረጋግቶ ነበር የተከወነው።
 
ፈረንሳዮች ሁሎችም የኮከብነት አቅም አላቸው። ይህን አቅም በቲም ወርክ አፋፍተው እቴጌዋ ድንቡልቡሊት እንዳትከፋባቸው በወል ጥረት፣ በግል ኃላፊነት እና ተጠያቂነት #ጥፍጥ ያለ ጨዋታ የማሳየት ባህላቸው ጠንካራ ነው። ጎሉም አያመልጣቸው፣ የጨዋታ ትዕይንትም አይደርቅባቸው። 
 
#የሲዳን ተተኪወች ሁልጊዜም በጥንካሬ እየገሰገሱ ነው። ከፓራጓይ ጋር የገጠማቸው ቻሌንጅን ተቋቁመው እዚህ ደርሰዋል። ለነገ እራሱን ነገ ያዘጋጅላቸዋል።
 
ዛሬ አፍሪካዊው ፈረንሳይ #ፏ ይላል። አውሮፓዊው ሞሮኮደብዘዝ ብሎ ጓዝ ጥቅለላ ይሆናል።
 
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
ደህና እደሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
10/07/026.
ኳሲዝም #ለምልም
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።