#በበዛ የመቻል፣ #የአደብ፣ #የአቅል #ጥንካሬ ተጋድሎ ውስጥ ነጥሮ የወጣ #ዕውነት።

 

#በበዛ የመቻል፣ #የአደብ#የአቅል #ጥንካሬ ተጋድሎ ውስጥ ነጥሮ የወጣ #ዕውነት
 
"እግዚአብሄርን እመነው እንጂ
ይረዳኃል ሥራህን አቅና፣ በእሱም እመን።"
(መጽሐፈ ሲራክ ም ፪ ቁጥር፮)
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
እንዴት ነን። ከእኛ ሙቀቱ ደስ ይላል። ልዕልቷ ከቤተ- መንግስቷ ወጥታ #ፏ ብላ #ፏን እያደለችን ነው።
 
የሰሞኑን የፓርላማ ውሎ የተወሰነውን አዳምጬ ነበር። ዛሬ ግን ሙሉውን አዳመጥኩት። ደግሜ ለማድመጥም እፈልጋለሁኝ።
ይህ ዛሬ ፖስት ያደረኩት የቀደመ ቪዲዮ ነው። ያቆየሁት የሳምንቱ መግቢያ ላይ የነበረው የፓርላማ ጉባኤ መንፈሱ ጤናማ እስኪሆን #ጥበቃ ላይ ስለነበረ ነበር። 
 
ለንጽጽር እንዲረዳ የማስበው ነገረ አዘገየዋለሁኝ። አክሰሱ ላላቸው የትውልድ አባላት በጥንቃቄ መያዝ ስላለበት ነው።
"የአብረን #እንሥራ ግብዣ።" በሌላ በኩል ከዚህ ሁሉ የዓይን ዱላ፣ ግልምጫ፣ ግለት፣ የማጣጣል እና የማቅለል ሁነት በኋላ ክቡር ዶር ደሳለኝ ጫኔ በክብር '#ጀግና" ሲባሉ ማድመጥ ለእኔ ክስተት ነው። 
 
ይህን መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚያደምጠው ትውልዱ በሃቅ፣ በዕውነት፣ በድፍረት፣ በራስ የመተማመን አቅም የሚያምንበት ባገኘው ዕድል ተጠቅሞ መግለፁ፣ ማብራራቱ የማታ ማታ ዕውነት በራሱ ጊዜ፣ ለራሱ ለሃቃዊነት #ሁነኛ መሆን እንደሚችል ያመሳጠረበት ክስተት ነው።
 
አንድ ጊዜ የተቃዋሚ፣ የተፎካካሪ፣ የተመጋጋቢ፣ የተቀላች መሪወችን ፊት ለፊት ከጠቅላይ ሚር አብይ ጎን ለጎን በአንድ ረድፍ እንዲቀመጡ ተደርጎ ነበር።
 
ቲም ደሳለኝ የአብን ልጆች ከኋላ #ሙጣጭ ላይ ነበር ቦታ የተሰጠው። "እንዳያማ ጥራው እንዳይበላም ግፋው።"
 
በወቅቱ የዛን ጊዜ ልጅ ጋሻው መርሻ በአንድ ሚዲያ ላይ ቅሬታውን ገልፆ ነበር። እኔም ውስጤን አሞኝ ስለነበር በወቅቱ ጽፌበት ነበር።
አንገት የማንደፋበት ጉዳይ የአማራ ልጆች ቁልፍ ተሳትፎ ባስገኜው ስኬት ያን ያህል #ግለት አቁስሎኝ ነበር።
 
አግሬሲብ የሆኑ ጹሁፎችን እጽፍ የነበረውም ግለቱ እና ጫናው #ለከት የለሽ መሆኑ ነበር።
የአማራ መንፈስ ተቃሎ መታየቱ፣ ጥቃቱን መሸከም አልቻልኩም ነበር። ጥቃት አልወድምም። ሂደቱ እንዴት እንደ ተፈጸመ አውቀዋለሁና።
"ከጎዳና ወደ ፓርላማ" የብልፄው ሞቶ።
 
ጠና ያለ ሰላማዊ ተጋድሎ አማራ ክልል ላይ ነበር። ብልፄው "ከጎዳና ወደ ፓርላማ" በሚል ሞቶ በተካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ፣ ዶር ደሳለኝ ጫኔ ጨምሮ 5 የፓርላማ ወንበር ተገኜ። ዶክተሩ የፓርላማ ዕድላቸውን አላፈሰሱም። 
 
በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተዘጋጅተው ይገባሉ። ይሞግታሉም። እኔ ከድፍረታቸው #ፊት መነሳታቸውን ከምንም ሳይቆጥሩ፣ ጉባኤው ላይ ይገኛሉ ይሞግታሉ።
 
ይሳቅባቸዋል፣ ይቃለላሉ፣ ይጣጣላሉ፣ ዕድል ይነፈጋቸዋል። አፈ ጉባኤው ሳይቀሩ #ይጫኗቸው ነበር። ጠቅላይ ሚር አብይ በሚመለከት ከመናገረው ቢዲዮው ይመስክረው።
 
የማይቻል የለም ሁሉንም ቻሉ። የማያልፍ የለም ሁሉም አለፈ። የ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፓርላማ አባላት ስንብት ላይ "አብረን እንስራ፣ ጀግና፣ ዕይታወት ጠቅሞናል።" 
 
እሳቸው ናቸው ወይንስ #AI ብዬ የተሰያዩ የመንግሥት ሚዲያወችን ስመረምር ጠቅላይ ሚር አብይ እራሳቸው ናቸው።
ይህን አጋጣሚ እንዲህ ስለሆነ፣ እንዲያም ስለሆነ፣ ወይንም እንዲህ ሊሆን ይችላል ልለው አልፈልግም።በቅንነት፣ በአወንታዊነት ልቀበለው ፈቀድኩኝ። 
 
ሂደት በራሱ ጊዜ የሚጠራው ዕውነት ስለሚኖር ጊዜ ሰጥቶ ማየቱ ይጠቅማል። ሟርትን ከማስቀደም።
 
የዶር ደስአለኝ ቀጣይ አቅጣጫ አስመልክቶ ቢቢሲ ላይም እሬሳቸው የፃፉትን አነበብኩኝ። አልወዳደርም ሲሉ ሞግቻቸው ነበር።
የአብንን ሊቀመንበርነት እኮ በራሳቸው ፈቃድ ነበር #ሊቀመንበርነቱን የለቀቁት። አዲስ ነገር የለም። በአንድ ቦታ ላይ መቆየትን የሚፈቅዱ አይመስለኝም። ማዬት ይፈልጋሉ፣ ይፈትሹታል። ይወስናሉ።
 
ለውሳኔ #ቅርብ ናቸው ማለት ነው። ለትውልዱ በሁሉ መስክ አብነትነታቸውን አጽንተዋል።
ይህ አቅማቸው ጠሚር አብይን ልብ ገዝቷል። ሌሎችንም ታዝበዋል ብዬ አስባለሁኝ። 
 
ሚዛን የደፋው አመክንዮ የደፋሩ፣ የቻዩ፣ የሞጋቹ፣ የክቡር ዶር ደስአለኝ የአቅም ጥንካሬ፣ የሰብዕናቸው አወቃቀር #አናባቢነት ጠቅላዩን ማርኳል። 
 
በሳቸው ላይ ሲሳለቁ፣ በዓይናቸው ሲገርፏቸው ለነበሩት ሁሉ ደግሞ አዲስ የቤት ሥራ ተሰጥቷል። አንዲትም ቃል ሳይተነፍሱ የተሰናበቱም ይኖራሉ።
 
#የሂደቱ መምህርነት።
 
1) የሰው ልጅ #ህሊናውን ብቻ ማመን እንዳለበት።
2) የሰው ልጅ ህሊናውን ለሌላ ማወስ እንደለለበት።
3) በራስ ህሊና መመዘን፣ የመዳኜትን አስፈላጊነት ሂደቱ አስተምሯጓል።
 
በዚህ የግዜ ማዕቀፍ ውስጥ የሌላ አካልን ፍላጎት መሸከም፣ ለዛም መጣር #ከንቱነትን ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ አሳይቶናል።
ቀጣዩ ፓርላማ #ምደባ ስለሆነ፣ ድርጅታዊ ሥራ እየተሰጠ #ፌክ ዕይታወችን አዳምጡ ካልተባለ በስተቀር ጸጥ፣ እረጭ ያለ፣ #የጫታ ጊዜ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ።
 
ሌሎች ከሰሞናቱ የፓርላማ ጉባኤ እኔ ላነሳቸው የምሻቸው ጉዳዮች ቀስ እያልኩ ዕይታዬን አቀርባለሁኝ።
 
#አንድ ለእናቱ እንደ አጤ ቴወድሮስ የመቻል #መሰጠታቸውን፣ አቅም ያላችሁ ወጣቶች ብትጽፋት ትውልዱ ያተርፋል። እየሰማን፣ እያዬን፣ እንደዛ ማየት የማይፈቅዱትን ሰብዕና ጋር ጠቅላይ ሚር አብይ አቅርበው አብረው ችግኝ ሲተክሉ ማየት ክስተት ነው።
 
ያሸነፈው ዕውነት፣ ጥረት፣ በራስ መተማመን፣ ግልጽነት፣ ቅንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ከፍ ሲል፣ ዝቅ ሲል የአማራ ሊቅነት ነው። ይህን አስተውሎ ሚዛናዊ ውሳኔ መስጠት፣ ለማንም ሳይሆን ለትውልድ የህሊና ብርታት ቀና ጎዳና ነው።
 
የተከበሩ ዶር ደስአለኝ ጫኔ አመሰግነወታለሁኝ። ቀሪ ጊዜወትን ፈጣሪ አምላክ የቀና እና ብሩህ እግዚአብሄር ያድርግለወት። አሜን።
ለሚሊዮኖች ድምጽ በመሆነወት የእኔ ድንግል ጥላ ከለላ ቶሁንልወት። ቤተሰበወትንም ትጠብቅ። አሜን።
 
በጠቅላይ ሚር አብይ የሰማሁት "ጀግና" የሚለውን ቃል ስሰማ ቃለ ህይወት ያሰማልን ብያለሁኝ። የመቻልም አይነት አለው። የዶር ደሳለኝ ጫኔ የመቻል አቅም አናባቢ ነው። ለዚህ ዕውቅና መስጠት መልካም ዜና ነው ለእኔ።
 
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
10/07/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ለዕውነት ወጌሻም፣ ጋራጅም አያስፈልገውም።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።