ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በዳህላስ 70ሺህ ተመልካች በተገኘበት የሁለት ምርጥ የአውሮፓ ቡድኖች ጨዋታ አንዱ #ለሙሽርነት ሌላው #ላጃቢነት ሁኗል መቋጫው። እቴጌ ድንቡልቡል #ማጫ እያማታች ነው። ሌላም እየጠበቀች ነው። ማጫው በለጥ ላለው፤ ጥሩ አድርጎ ላጎናት፤ ለሰለቃት ታደላለች።
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በከፍተኛ ራንክ ለዋንጫ የታጨው የፈረንሳይ ቲም፣ #ምን #እንደነካው አላውቅም በዛሬው በአገራቸውም ዛሬ ብሄራዊው #በዕላቸው ነው። ቀን ሳይቀናው ቀረ። ዛሬ ፓሪስ ምሽቱን እንዴት ታሳልፍ ይሆን?
የፈረንሳይ ቡድን እስከ 35ኛው ደቂቃ ድረስ #ምንም የግብ ሙከራ አላደረገም። አንድስም እንኳን። አይገርምም። በአንድ ጨዋታ ሦስት ጎል ያስቆጠረው ኮከብ አላቸው። ማፔም የተሰጠው ነው። በነፍስ ወከፍም በወልም ጠንካሮች ናቸው። ግን ዛሬ?
ይልቁንም ከመጀመሪያው የውሃ እረፍት በፊት #ስፔን የቅጣት ምት አግኝቶ አንድ ጎል አስቆጠረ።
ከውሃ እረፍት እስከ ግማሹ መደበኛ እረፍት ጊዜ ድረስ ፈረንሳይ #ምንም ዓይነት የግብ ሙከራ ሳያደርጉ አንድ ለምንም ውጤት እረፍት ወጡ።
ከእረፍት መልስ የፈረንሳይ ቡድን ምንም ያሻሻሉት ነገር ሳይኖር ጨዋታው ቀጠለ። ስፔኖች አንድ መደበኛ የጎል ዕድል ቀንቷቸው #ሁለት #ለምንም መምራት ጀመሩ። በቀሪው ደቂቃ አካክሰው በአቻ ውጤት ጨዋታው ተራዝሞ ተጨማሪ ዕድል ይኖራቸዋል ብዬ ሳስብ፤ በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ የዕለቱ ጨዋታ ተጠናቀቀ።
……… #ከዛስ? ትንሽ ልመለስ መሰል።
ከዛማ በ64ኛው ደቂቃ አካባቢ ሁለተኛ ዕድላቸውን ፈረንሳዮች ሞከሩ። #አልተሳካም። የረባ ማራኪ የጎል ሙከራ አላደረጉም። ምን እንደሆኑ የሚውቁት እራሳቸው ናቸው። ብዙ ጊዜ ኳስ ይሾልክባቸው ነበር።
ፈረንሳዮች ምን እንደነካቸው አላውቅም። በጨዋታው አርትም፣ በኮኦርድኔሽንም፣ #በአትኩሮት ስስነትም በተጠበቀው ልክ አላየሁም።
ኮለንብያ እና ሲዊዝን የዳኙት የኤልሳባዶሩ ዳኛ ነበሩ የዕለቱ ዳኛ።
#ግን ፈረንሳይ ሁለት ለምንም በስፔን?
በካታሩ ጨዋታ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ካታር ያቀኑት የፈረንሳዩ #ፕሬዚዳንት በዘንድሮው እስከ አሁን ትውር አላሉም። የፊፋ ፕሬዚዳንት ግን ነበሩ።
ግን የዛሬ ጨዋታ በከፍተኛ ጉጉት ተጠብቆ በጨዋታ መሳብ፣ ትዕይንታዊነት፣ ፋክክር የጠበቃችሁትን አገኛችሁን? ትሁታዊ ጥያቄ ነው።
ስፔን ለዋንጫ፣ ፈረንሳይ ለደረጃ #አንድ /// #አንድ ጨዋታ ይቀራቸዋል። ማፔ በካታሩ የዓለም ዋንጫ #ሁለተኛ መውጣቱ በእጅጉ አሳዝኖት ነበር። ዛሬ የባሰ ሆነ። ለነገሩ የወርቅ ጫማ ውድድሩን ይረታ ይሆን?
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
14/07/026.
ኳሲዝም ለምልም።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ