በዚህ ጨዋታ ያልታዬ ነገር የለም። #አርጀንቲና 3 #ሲዊዝ 1።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

በተደራጄ ሴራ የተገኜ ድል። ሲዊዝ አንድ ጎል በማስገባቷ እና ከአርጀንቲና ጋር #አቻ መሆኗ ዳኛውን አበሳጬ። ከዛ ኢንቤሎን #በቀይ ካርድ እንዲወጣ ተደረገ። የሚፈለገው #ሜሲ እንዲያሸንፍ ነው። #ሜሲ ቢዝነስ ነው። ተሳክቷል። #በኢምቤሎ ላይ በርካታ ተደጋጋሚ በደሎችን አርጀንቲናወች ቢፈጽሙም የዕለቱ ዳኛ እንዳላዩ አለፋት። ዳኛው እነሱን ሳይቀጡ #ኢንቦሎ ከጨዋታ ውጭ አደረጉት። #በቀይ #ካርድ ተሰናበተ።
ምን አልባት ጥሩ ይሆን የነበረው አርጀንቲናወችም ዳኛውም በኢምቤሎ ላይ #ጫና ሲያበዙ #ኢንቤሎ ቀድሞ ተቀይሮ ቢሆን ኖሮ የእምዬ ሲዊዝ ልጆች ከሜሲ ጋር በጎደሎ የመጫወት ቻሌንጅ አይገጥማቸውም ነበር። ሁሉንም አቅም ተጠቅመዋል። ሁሉንም አድርገዋል። #ምንም ወቀሳ ሊደርስባቸው አይገባም።
ከዛ በኋላ የሲዊዝ ቲም በጎደሎ መጫወቱን ቀጠለ። ይህም ሆኖ አንበሶቹ የሲዊዝ ቲም #በጥንካሬ ቀጠሉ። ከዛ ጠንካሮቹ የሲዊዝ ቲም ሙሉ #የመደበኛ የጨዋታ ጊዜውን ከአርጀንቲና ጋር #በአቻ ነጥብ፤ ድላቸውን አስጠበቁ። አንድ ተጫዋች #ጎድሎባቸው ቲማቸውን አስከብረው 90 ደቂቃውም፤ የባከነ ጊዜውንም #በአቻ ነጥብ መደበኛ ጊዜው ተጠናቀቀ።
ልዩ ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶም የመጀመሪያውን የጨዋታ ጊዜ #በአቻነት ቀጠሉ። ከእረፍት መልስ በተጨማሪ ጊዜው #ሁለት ጎል አክለው አርጀንቲናወች #አሸነፋ።የሲዊዞች ጥንካሬ እጅግ የሚገርም ነበር። በጣም #በትጋት #በጋራ ሁሉንም ተቋቁመው ተጫውተዋል። #ጀግኖች ናቸው።
#የሚጸጽት፤ #የሚቆረቁር ነገር የለውም። የአርጀንቲና ቡድን በዕለቱ ዳኛ #ኢፍትኃዊ እርምጃ እና #ተጫኝነት ነው ያለፈው። ይህ ዓለም የሚየው #ሃቅ ነው። ምክንያት #የሜሲን #ሰብዕና #መጠበቅ የብዙ #ተቋማትን #የቢዝነስ #ህይወት #ማስቀጠል ነውና። በዚህ ጉዳይ በተከታታይ ጽፌበታለሁኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ.
Sergute©Selassie.
12/07/026.
#ፍትህ ለኳስ ተጫዋቾች።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ