ቤተ - ሥርጉትሻ #ዘለፋ፤ #ስድብ፤ #አሽሙር አይሰተናገድበትም! አቃሎ፤ አጣጥሎ ሳቅ ከተጨመረበት #ይፈቀዳል። ሳቅ የናፈቀን #ህዝብ ስለሆን።

 

ቤተ - ሥርጉትሻ #ዘለፋ#ስድብ#አሽሙር አይሰተናገድበትም!
 
አቃሎ፤ አጣጥሎ ሳቅ ከተጨመረበት #ይፈቀዳል። ሳቅ የናፈቀን #ህዝብ ስለሆን።
 
"እንሆ አሳባችሁን፥ የመከራችሁብኝንም፡
ክፋ ምክር አውቄዋለሁ።" ይላል የእግዜሩ ቃል።
(መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፯)
 
 May be an image of one or more people and people smiling
#ምዕራፍ ፲፱።
 
ፌስቡክ እጅግ በጣም ዘግይቼ ነው የጀመርኩት። የእጅ ስልክም አልነበረኝም። የስልክ ፍቅርም የለኝም። መደወልም፤ መቀበልም ለእኔ ሁለቱም የጭንቀት ማዕከሎቼ ናቸው። እኔ ኢሜል ነው የምወደው። መልሴ ፈጣን፤ በሙሉ አቅም የምሳተፍበትም መስክ ነው።
ፌስቡክ ስጀምር ይህ ቤት እንዲህ የተከበረ፤ ጨዋ፤ ከትርፍ ነገር የታቀበ፤ ዘለፋ፤ ስድብ የማይዘወተርበት አልነበረም። ከዚህም አልፎ በማህበረሰባችን የሚነወር ፆታዊ ጉዳዮችም በይፋ #የሚቀነቀኑበት ነበር።
 
ሌላው የሰውን ልጅ በእንሰሳ ምስል መስራት ይዘወተርበት ነበር። ምስልን መዘቅዘቅ፤ ኤክስ ማድረግብ ተዘውትሮ የሚሠራበት ነበር። የሃይማኖታዊ ጉግሱም ጠና ያለ ነበር። ሁሉንም መስመር ለመያዝ ጊዜ ጠይቋል። ተደክሞበታልም። ተለፍቶበታልም።
 
አንድ ጊዜ ፖለቲካል ሳይንስ ያጠኑ በዕውቀት፤ በተመክሮም ዝልቅ አቅም ያላቸው፤ ሚዲያም አላቸው፤ በአንድ ዕውቅ ሌላ ፖለቲከኛ ላይ ፍየል በአፋቸው ላይ እየሸናች ፎቶ ለጠፋ። ውስጤ አዘነ። ሃዘኔን ዋጥ አድርጌ መራራ ስንብት ሆነ። ምክንያቱም ለቀጣዩ ትውልድ፤ አክሰሱ ላላቸው ታዳጊወች ይህን መሰል የፈጣሪን ፍጡር የተዳፈረ ትልልልፍ የሚያስተምረው በጎ ነገር ስለለ። 
 
እኒያው ሰው ከአንዲት የቅርብ ወዳጄ ጋር ፌስቡክ እያዬን በእሷ ኮንፒተር ያልሆነ ነገር ፃፋ። እኔም ይህን ቃል አይጠቀሙ ብዬ ፃፍኩኝ። ባለ ኮንፒተሯን ቤተሰቤን አስፈቅጄ። ቤት ሙሉ ስድብ ተሳደቡ። እንዲህ አላውቃቸውም ነበር። ለካ ይህን መሰል ሰብዕና ይዘው ነበር አደባባይ የወጡት። ትልቅነትን ለማዝለቅ "ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅም።" የሚለውን የቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስን መልዕክት ማሰብ ይገባል። በተለይ ለክርስትና እምነት ተከታዮች። ከማክበር መከበር ይመነጫልና።
 
በተጨማሪም እኔ ፌቡ ስጀምር ያን ጊዜ ቃሎቹ ኖረው፤ ግን ባልተፃፈው ህጋችን የማይፈቀዱ፤ ነውር የሆኑ የአነጋገር ዘየወችን ሁሉ፤ ሰብዕናን የሚደፍር፤ ሞራል አልቦሽ ሃሳብ ይቀርብ ነበር። ያ ሁሉ ዛሬ የለም። ብዙ በጣም ብዙ ለፍቼበታለሁ። ብዙ አቅም አፍስሼበታለሁኝ። 
 
የሻሸመኔ የዕንባ ሰሞናተ - ነነዌ ከዚህ ቤት የነበራችሁ አይታችኋል። የሃይማኖት፤ የዞግ ልዩነት ሳይገድብ ቤታችን የህማማት፤ የሱባኤ፤ የህብራዊነት የፆም የጸሎት ቤት ነበር። እኔ እራሴ በህይወት መኖሬን #የመረቅሁበት ጊዜ ነበር። ከዛ ጸያፍ ከሆነ ቅይጥ ሁነት ተወጥቶ የተከረከመ፤ ቁጥብ፤ ሰውነትን፤ ተፈጥሯዊነትን ያከበረ፤ ያስከበረ ስፕሪት መፍጠር የሚችለው አምላካችን፤ አላኃችን ሲረዳ ብቻ ነውና፤ እረድቶኝ እንደ ልቤ የሆነ ፔጅ ሆነ።
 
በአማርኛ ቋንቋ የሚገኙ ግን ማህበረሰብን፤ ግለሰብን የሚጫኑ አገላለፆች ሳይቀር ቤቱ አለማስተናገዱ፤ እንክርዳድ የተወገደበት ንጹህ ሰብል የሚመረትበት ቤት ለመገንባት አስችሏል።
 
ለምሳሌ በፆታቸው የሚተዳደሩ፤ አግብተው የፈቱ፤ ያላገቡ፤ ወይንም ትዳራቸው በሥጋ የተለየባቸው፤ ወዘተ የሚሉ አቻ የሆኑ ቃላትን፤ ሥንኛትን፤ ዐረፍተ ነገራትን በመጠቀም ያን ነወረኛ ሁነት መንፈስን ከጥቃት ለመከላከል ጥረት ተደርጓል። በተጨማሪም አንድ ማህበረሰብ ልጠራ በሚልበት ሥም ብቻ መጥራት ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶት የተሰራበት ነው።
 
በቆዳ ቀለማችን የከፍታ እና ዝቅታ፤ በጸጉር አበቃቀላችን ላሁጫ እና ከርዳዳነቴ፤ በሰብዕና ቅርበት እና እርቀት ሰውነታችን ፈተና ውስጥ የሚጥሉ የተዛቡ ሁነቶችም ነበሩ። ያን ዝበት በሰፋ ትዕግሥት ለማረም፤ ለማስተካከል ተችሏል።
 
በሌላ በኩል ዕድሉን መልክ ባለው፤ በተደራጀ እና ተመክሮ ዘለቅነቱ በአግባቡ ሊቀናበት እንዲችልም ጥርት ያሉ ተግባራት ተከውኖበታል። ለምሳሌ ሼር ለሚያደርግ ሁሉ አመሰግናለሁ የማይቀር የቤተ - ሥርጉትሻ መርህ ነው። ቋሚ ባህሏ ነው። ስገባ እና ስወጣም፤ ሰነባብቼ ስወጣ እና ስገባም በከበረ ሰላምታ እና የስንብት ቃል ሁሉም ነገር ሥርዓት ባለው ሁነት ይፈጸማል።
 
በሌላ በኩል ኃይለ ቃላት፤ ዕርዕስ ላይ #ይህ ምልክት ይደረጋል። ሌላ ቃላትን በማቆላመጥ፤ በማባባል ጹሁፍ አሰልቺ እንዳይሆንም ብርቱ ጥረት ተደርጓል። ብልጽግናን #ብልፄው፤ ጎንደርን #ጎንደሪና፤ ህውሃትን #ህውሃትሻ፤ ሥርጉተን #ሥርጉትሻ ወዘተ በሚል ድርቅ ካለ አገላለጽ ለዘብ አድርጎ በማቅረብ፤ አለስልሶ የማቅረብ ዘይቤም እጠቀማለሁኝ። አንዳንድ ጸሐፊወች ብልፄን አሁን አሁን አዘውትረው ሲጠቀሙበት አያለሁኝ። ጥሩ ነው። ሃይላቱንም እንዲሁ። መማርም ማስተማርም ዕድልን ሳያፈሱ ጥቅም ላይ መዋል የብልህነት ቤተሰባዊነት ነው። 
 
በተጨማሪም እኔ በፃፍኩት ጹሁፍ ላይ አክብረው የተለየ ሃሳብ የሚቀርቡ፤ ጥያቄ የሚጠይቁ፤ አስተያዬት የሚሰጡ ጥሞና ላይ ካልሆንኩ በስተቀር ጊዜ ወስጄ፤ ለተቃሞም፤ ለሞጋችም ይሁን ለሃያሲ ሃሳቦች ከምስጋና ጋር አመስግኜ መልስ እሰጣለሁ፤ ማብራሪያ አቀርባለሁኝ፤ ጥያቄወችን እመልሳለሁኝ። 
 
ሌላው እኔ ተደውሎልኝ ስልክ አላነሳም። ስልክም ለፌስቡክ ጓደኞቼ ስልክ አላነሳም፤ ስልክም አልደውል። ለዚህ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ አክባሪወቼን። ስልክ መደዋወል የእኔ አጀንዳ ስላልሆነ። ለቤተሰብም ይኽው ነው ባህሬዬ። ከዚህ በስተቀር ሁሉም የቤታችን ቅን #ቅኔወቼን አክብሬ፤ አቅርቤም ነው የማያቸው።
 
ከዚህ ቤት ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት፤ የትኛውም ተቋም፤ የትኛውም ሃይማኖት በእኩልነት ይስተናገዳል። ሌላው ቀርቶ ሳቅ፤ ማቃለል፤ ማጣጣል ይፈቀዳል። ሳቅ #የናፈቀን #ህዝብ ስለሆነ የእኔ ጹሁፍ ተቃሎ ግን ማሳቅ ችሎ ከሳቁልኝ ተመስገን ነው። እኔ ኮመዲያን ስላልሆንኩኝ። ከልጅነት እስከ ዕውቀት የእኔ ነገር ሁልጊዜ ቁም - ነገር ነው።
 
በሙሉ ህይወቴ አቅጄ ኮንሰርት ሂጄ አላውቅም። አገር ውስጥም ውጭም። ሙዚቃ ከፍቼ አዳምጬ አላውቅም። ፕሮግራሞቼ በተፈጥሮ ድምጽ ነው። በወፎች፤ በፏፏቴ፤ በዝናብ ወዘተ። አሁን አሁን ስለ አገሬ የምሰራበት የጸጋዬ ራዲዮ ለምን ይቅርበት የሙዚቃ ጥበባችን ብዬ መጠቀም ጀምሬያለሁኝ።
 
በነገራችን ላይ ቤተሰቦቼ ሙዚቃ በጣም ወዳጆች ናቸው። እናቴ እብዬ ሆዴ የአርቲስት ይሁኔ በላይ አድናቂው ነበረች። እህት ወንድሜ ስታሳድግም በነፃነት ነበር። ሙዚቃ ይደመጣል። ውዝዋዜም ነበር። በእኔ በኩል ሙዚቃም የጥበብ አካልነቱን አከብራለሁኝ። በተለይ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰሩ ከሆነ ግን #በአደብ አደምጣለሁኝ።
 
በጣም የሚስበኝ የሥነ - ጹሁፍ ውበቱ ነው። እሱን ካገኜሁ አነባለሁኝ። ከሙዚቃ ይልቅ ሥነ - ሥዕል በእጅጉ ይመስጠኛል። ይህ ጥበብ ቡርሽም ቀለምም ያለው ሁሉ የማይደፍረው ለተለዩ ባለጸጋወች የተሰጠ ይመስለኛል። ሙዚቃም ቅብዓን ይጠይቃል።
 
ልጅ እያለሁኝ ቅርጫት ኳስ፤ አለሎ ውርወራ፤ ቦሊቦል እወድ ነበር። ወጣት ሳለሁ ደግሞ ልቤ ወደ እግር ኳስ አደላ። በተለይ ኳስ እና መረብ የሚገናኙበት ቅጽበት በጣም ይመስጠኛል። የአሰልጣኞች አክሽን ፊልም፤ የተመልካቾች ሲቃ እምደነቅበት ሁነት ነው።
 
እኔ ኮንሰርት የሙዚቃ ድግስ ተገኝቼ አላውቅም። እና የምውደውን ኳስ በአሻኝ አቅም፤ በቤቴ ስሜቴን መግለጽ ሙሉ መብቴ ነው። የምፈልገውን የመደገፍ ሙሉ መብቴ ነው። በስፖርት ዙሪያ ለምጽፈው አስተያዬት የማንም ፈቃድ አልጠይቅም። እራሴን ሆኜ የእኔን ንጹህ መንፈስ ማቅረብ እችላለሁኝ። 
 
በቤቴ ገብቶ መሞገት ይቻላል። ቅሬታን ማቅረብ ይቻላል። ዘው ብሎ የለመዱትን ወይንም የሰለጠኑበትን ስድብን ማሰልጠን ግን አይፈቀድም። ስለ ኳስ የሚቆጨው ትውልድ #የራሱን ኮከብ መፍጠር ነው የሚቅመው። "የሰው ወርቅ አያደምቅምና።"
 
ኢትዮጵያ ከኩራሳኡ፤ ከኬብ ቬርዴ፤ ከሌሎችም አንሳ በማዕቀፋ ውስጥ አለመኖሯ ነው ቁጭት፤ እልህ ፈጥሮ ሁሉም ወደ እግር ኳስ በሚል የጋራ መርኽ መንቀሳቀስ የሚገባው። እንጂ ስለምን መሲ፤ ስለምን ክርስትያኖ ተነሳብኝ ብሎ በራስ ወገን ላይ ህግን መተላለፍ አይጠቅምም። ቅናቱ፤ ቁጭቱ እኛስ? መቼ? ለዚህ መሰል ክብር እንበቃለን የሚለውን ማሰብ፤ ማሰላሰል ጊዜ ሰጥቶ መወያዬት ይገባል። እናት አገር ኢትዮጵያ የጎደለባትን ወደ እራስ ወስዶ ውስጥን፤ አቅምን ራዕይን፤ ምኞትን መገምገም፤ መፈተሽ ይገባል። 
 
ዓለም ዓቀፍ ኮከቦችን ማድነቅ፤ ማክበር ይገባል። ትምህርት ቤትነታቸው በተግባር ስለሆነ። በኮኮብች መደገፍ የተነሳ ግን መጣላት አይገባም። ከሁሉም ስድብ አትራፊ መንገድ አይደለም። ኢትዮጵያ የተቀረጸችበት መርኽ መከባበር ነው። አክብሮ መሞገት፤ አክብሮ መጠየቅ፤ አክብሮ ማሄስ። እላፊ መሄድን ግን ቤቱ አይፈቅድም። ይህን እንደ መርኽ ስድብን ወደ ያዙ ክፍሎች ጎራ ማለቱ ይጠቅማል።
በስድብ፤ ለስድብ፤ ዘለፋ መቻቻል የለም። እኔ በጻፍኩት ጹሁፍ ብቻ ሳይሆን፤ የፌስቡክ ጓደኞቼ ሼር በሚያደርጉት ላይ ያልተገቡ ጉዳዮች ከኖሩ ጓደኞቼን የሚዘልፋ፤ የሚሳደቡ ተሳታፊወችን ካየሁ ምህረት የለም። መራራ ስንብት ይሆናል። የታረመ አንደበት፤ የተቀጣ ሰብዕና ነው አሳዳጊህን ይባርከው የሚያለኛው። 
 
ይህ ቤት ታዳጊ ወጣቶች፤ ወጣቶች ነፃነታቸውን፤ ክህሎታቸውን፤ መሰጠታቸውን፤ ሰው ሆነው መፈጠራቸውን፤ ተፈጥሯዊነታቸውን ጤናማ በሆነ አስተሳሰብ፤ ጤናማ በሆነ መግባባት ህግን ተከትለው፤ ሥርዓትን አክብረው ነገን ይቀበሉ ዘንድ እጅግ በጥንቃቄ ሥራ የሚሠራበት ቤት ነው።
 
አንዳንዳንድ በደራሽነት የሚፈሉ፤ ቋያ የሆኑ የሚጋረፋ ጉዳዮች ሲኖሩ #ረብ እስኪሉ ጠብቄ፤ ዕይታየን የማጋራውም በፍላሎት ስሜት ቢፃፍ የውስጤን ጤናማ ስሜት ሊጎዳው ይችላል በሚል ነው። ቀስ አድርጌ፤ አረጋግቼ አማርኛ ቋንቋ ዲታ ነው። አማርኛ ቋንቋ ጉልበታም ነው። በአቅሙ ልክ ሃሳቤን አስክኜ እገልፃለሁኝ። ሁሉ ነገር በረድ ካለ በኋላ። የረጋ፤ የሰከነ ምራቁን የዋጠ፤ ህግ አክባሪ ማህበረሰብን መፍጠር የሚቻለው በዚህ ቅናዊ ጎዳና ብቻ ነው። የሚሞገተው አካል፤ የሚታረመው አመክንዮን አክብሮ መነሳት ትውልን በተገባ የሞራል ልዕልና አልቆ ለማበጀት #ፏ ያለ መንገድ ነው። 
 
ቤተ - ሥርጉትሻ መድከም ካልቀረ፤ በተቻለ መጠን ባሰበለ ጉዳይ መትጋቱ ይጠቅማል። የሰው ልጅ ሊጸጽተው ከቻለ፤ ሊጸጽተው የሚገባው በትውልድ ጉዳይ ላይ መድከሙ ካልቀረ ጠንቃቃ ካልሆነ ጉዳቱ የትውልድ ይሆናል። በሌላ በኩል የእኛ ብሎ ለማስጠጋትም ከሰፊው የሃሳብ ገብያ ውስጥ ህሊና ጠገብ ተመክሮ ሊሆን ይገባል።
 
ቤተ ቅኖቼ፤ አዱኛወቼ እንዴት አድራችሁ አረፈዳችሁልኝ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergure©Selassie.
14/07/026.
#ትዕግሥት ሲያልቅ #ፍቅር ይሰደዳል።
#ፍቅር ሲያልቅም፤ #ትዕግሥት ይሰደዳል።
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።