ልጥፎች

#ሌላው …

ምስል
    #ከእናት ይሆን የተፈጠሩትን?   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ። " አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰     የአንድ ከተማ ህዝብ #ምጥጥ ያደረገውን አረመኒያዊነት ከሴቶች በላይ ማን ግንባር ቀደም ተሟጋች ይሁን? በዘመነ ህወሃት እታገልበት የነበረው ሞቶ የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ሊቃናት ከፖለቲካ ሥልጣን ስለተገለሉ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ አባሽ አጡ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ የገበርዲን እና የከረባት ያደረገው ሁነት ሊቀየር ይገባል ነበር ሙግቱ። ይህም ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን የህወሃትን መንበረ - ሥልጣን የነቀለ ጉልበታም አመክንዮ ነበር።   ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም 50% ካቢኔያቸው በሴት ሊቃናት የሆነው የዛን ጊዜ ከወንዝ ዳር የታፈሰ ዝቀሽ ጉዳይ ሆኖ አልነበረም። ለስልጣነ - መንግሥታቸው የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡን ቅቡልነት፤ ቀልብ በመሳብ የዓለም ተጽዔኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የተረጋጋ #ታማኛዊ መንፈስ እንዲቀልቧቸው አስበው የፈጸሙት ጉዳይ ነበር። ከለወጡ ከሚፈለጉ መሰረታዊ ጉዳዮች የሴት ፖለቲከኞች ዕውቅና እና የፖለቲካ #ውክልና በእጅጉ ያስፈልግ ነበር።   ዕውነት ለመናገር አሁን እንዲህ ዓይነት ሙግት አላነሳም። ከላይ እስከ ታች በሴት የፖለቲካ ሊቃናት ተሞልቷል። ነገር ግን አንድም ሊቅ #እናትነታዊ ጥሪው አነሳስቶት ከቅርባቸው ያለውን የደብረብርሃን #የተፈናቃይ ማዕከል ሄደው አይተው አያውቅም። በሌሎችም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምንም ዓይነት ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ድርጊት ላይ ሲገኙ አላስተውልም። አቤቱታ ሳቀርብም አያዳምጡኝም። ትንሽ ዶክተር ሊያ ታደሰ የቀድሞዋ የጤና ሚር ያዳምጡ ነበር።    እኔ ቀን ከሌት "አብይ፤ አብይ" እያልኩ አልባንንም። ካቢኔ አለ። ህግ አውጪ፤ ህግ ተርጓሚ ...

#ይሁንታ

  የህዝብን #መታመን #የሚደፋ የአገር መሪ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ #ሰላማዊነትም የሚረብሻቸው ይመስለኛል።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፯። ነገረ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ጠቅላዩን ህልማቸውን ያሳካ መንፈስ ያለበት ነው። ጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች? እንዴት አደራችሁ ዋላችሁ?   ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊን #አሳቻ መሪ ናቸው ማለቴ ከትናንት በበለጠ ዛሬ ትርጉሙ እየበራ ነው። በደርግ ዘመን ቅኔው ጎጃም #የሰላም በዓት ነበር። በጠቅላይ ሚር አብይ ዘመን ህወሃት አቅዶ ሰቆቃ ያልፈጸመበት በዓት #ጎጃም ነበር። እንደ ማዕከላዊ ጎንደር፤ እንደ ሰሜን ተራራም ሴራ ህወሃት አላደራጀበትም።    ምንም ዓይነት የህወሃት በቀል በሁመራ ከተማ አልተፈጸመበትም። ተመስጌን ብዬ ብዙ ጽፌበታለሁኝ። ጠለምት፤ አዳርቃይ፤ አዲረመጥ፤ ማይጠምሪ እንዲሁም ራያ እንደ ጥንቸል የሰቆቃ መሞከሪያ ጣቢያ ናቸው። የሆነ ሆኖ ቀለሜዋ ጎጄ ዛሬ ግን ከጎንደር ሰቲት ሁመራን ሳይጨምር፤ ከወሎ እና ከሽው ጋር የሰላሙ መታወክ ሁነት በቅኔው ጎጃምም #እኩል ሆኗል። ስንት ፈላስፋ፤ ስንት ሳይንቲስት ሊያፈራ የሚችል ባለተሰጥዖ በዓት ነው ጎጄ።።።።።።   ከዚህ ሃሳብ ስነሳ የሰቲት ሁመራ የወልቃይት እና ጠገዴ ዞን ብቸኛው በአማራ ክልል ካሉ ዞኖች #ፍጹም ሰላም የሰፈነበት፤ ለኢትዮጵያ ሠራዊት #ቅንነቱን በአክብሮት የሚመግብ ብቻ ሳይሆን፤ የአገር መከላከያውን #የእኛ ሠራዊት ብሎ ደፍሮ የሚናገር፤ በየትኛውም የፋኖ ንቅናቄ ቁጥብ የሆነ፤ #ነፍሱን አድምጦ፤ ከችግር - ተምሮ፤ #ማስተዋልን ውጦ ሁሉንም ዓይነት የፈተና ወጀብ ችሎ በጸጥታ፤ በእርጋ...

#የሃቅ #ዓራት #ዓይናማ #አርበኞችም

ምስል
  ይህ ሁለተኛው ለዛሬ የመደብኩት ነው። በዚህ የሰቆቃ ማዕቀፍ ውስጥ ዕውነተኛ #ዕውነቶን የተጋሩ #የሃቅ #ዓራት #ዓይናማ #አርበኞችም እንዳሉበት በማስተዋል፤ ሚዛናዊ ሆኖ ማድመጥ ይገባል። የትናንት ሰቆቃ ዛሬ እንዳይደገም #የታረመ #የሰብአዊነት ፖለቲካዊ ጥንቁቅ #ውሳኔ ይጠይቃል። ፖለቲካ #ለሰው እንጂ #ለጉዑዝ አይደለም እና።     https://www.youtube.com/watch?v=jwe8odXj1oU   «የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!» (ፀሐፊ አቶ ቢኒያም መስፍን) ለነገሩ ዶር ዳኛቸው ከሰሞኑ ከአንድአፍታ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ለጎንደር #ዘፈኑን ተሸልሟል" ሲሉ እኔ #አጠይመው የተናገሩት ቅኔ በውስጤ ነበር አድሮ የዋለው። በጣም ሴንሲቲብ #ጉዳዬ ነውና። ዶር ዳኛቸው በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ላይ #ልልት ያለ፤ በእርግጠኝነት የሚናገሩበት ሁነት አጥቼውም ነበር። ከብልጽግናው የደህንነት ሰው ከአንባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር የነበረው ቆይታም ዓላማው እና ግቡ እኔ በመደዴ አላየሁትም ነበር። ሚኒስትሮ ለጎንደር ያላቸው ምልከታ፤ ለህወሃት ካላቸው ፍቅር ጋር እንደሚላተምባቸው በቃለ ምልልሳቸው ላይ ፈጦ የወጣ ሃቅ ነበር። ዘልፈው እኮ ነበር። #ባለጊዜ ናቸዋ።    ውዶቼ ዛሬን በዚህ፤ ነገን ደግም በተፈቀደልን #የመሆን ሩም ውስጥ የምለውን እላለሁኝ። ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ አመክንዮ በድፍረት እና በጭካኔ #ሲፈቀፈቅ ፤ እንደ ከብት አሞሌ ሰጥቶ ማባበል የማይችለው የሰው ልጅ ክብር፤ ማዕረግ እና ሞገስ #ለለት ደራሽ፤ ፊርማው ላልደረቀ #የስምረታ ፓርቲ #እጅ #መንሻ ሲቀርብ፤ ዝምታ #በደል ነው...

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሙግት ሽው ይላቸዋል። ይነፍቃቸዋል። ፎቷቸው ተለጥፎ ሲሞገቱ ማዬት ደስታ የሚሰጣቸው ይመስለኛል። የሚዲያ ዓውራነታቸውን ስለሚያደምቅ ይሆን? #ካሰኛቸው ይሞገታሉ።

ምስል
   https://www.youtube.com/watch?v=-_dT5na0L18   የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬ15 11 2022 በወልቃይት ጉዳይ ዬሰጡት መግለጫ እና የሥርጉተ ሥላሴ ዕድምታ።   ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሙግት ሽው ይላቸዋል። ይነፍቃቸዋል። ፎቷቸው ተለጥፎ ሲሞገቱ ማዬት ደስታ የሚሰጣቸው ይመስለኛል። የሚዲያ ዓውራነታቸውን ስለሚያደምቅ ይሆን? #ካሰኛቸው ይሞገታሉ።    ከዚህ ቀደም በፓርላም ተረብ ቢጤ አምጥተው እንዲህ ተሞግተዋል። ወደፊትም #ከናፈቃቸው ይሞገታሉ። #ማንነት #በገብያ #ህግ #ስለማይተዳደር ። ማንነት #ሸቀጥ አይደለም እና። በሌላ በኩል ወጣትነትን የነፃነት ትግል ቅርምጥ አድርጎ ይበላው ዘንድ የተወሰነበት ት የውስጥነት ጉልላታዊ ጉዳይ በአዘቦት ፖለቲካ ለስጦታ ሲቀርብ፤ ዝምታ አሻም ይባላል።    ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲያሰኛቸው የጎንደር #ሸኔ ይላሉ፤ ማርሻላቸው የወሎ እና የጎንደር ሽፍቶች ይላሉ። ሲያሻቸው ደግሞ ዶር አብይ አህመድ ከገዛሁት ምግብ ውጭ በእርጎ ጭማሪ ተስተናገዱ እና #የትዳር ሁነቴን ወሰንኩበት ይላሉ። የኦሮምያ የከተማ ቢሮ ኃላፊ ሳሉም የጎንደር ብቸኛው ጠበቃ፤ ስለ ጎንደር ግድ የሚላቸው ስለመሆኑ ንግግራቸውን አዳምጫለሁኝ። ቃልን ማጠፍ ብረትን የማጠፍ ያህል ቀላል አይደለም።    የሆነ ሆኖ በሌላ ጊዜም አቅጣጫችን ወደ ጎንደር ነው "እናንተ ጥላችሁ ብትሄዱ እኛ እንኖርበታለን" ሲሉም አድምጫለሁኝ በመቶ ቀናቸው የመጀመሪያ ጉብኝት ጊዜያቸው። የሆነ ሆኖ #በማይቀለደው #አይቀለድም ፤ #ተረብ #በማያሰኜው አመክንዮ #ገባወጣዊ ስላቅ አያሰኜውም።  ዝምታው በኢትዮጵያም...