ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሙግት ሽው ይላቸዋል። ይነፍቃቸዋል። ፎቷቸው ተለጥፎ ሲሞገቱ ማዬት ደስታ የሚሰጣቸው ይመስለኛል። የሚዲያ ዓውራነታቸውን ስለሚያደምቅ ይሆን? #ካሰኛቸው ይሞገታሉ።
https://www.youtube.com/watch?v=-_dT5na0L18
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሙግት ሽው ይላቸዋል። ይነፍቃቸዋል። ፎቷቸው ተለጥፎ ሲሞገቱ ማዬት ደስታ የሚሰጣቸው ይመስለኛል። የሚዲያ ዓውራነታቸውን ስለሚያደምቅ ይሆን? #ካሰኛቸው ይሞገታሉ።
ከዚህ ቀደም በፓርላም ተረብ ቢጤ አምጥተው እንዲህ ተሞግተዋል። ወደፊትም #ከናፈቃቸው ይሞገታሉ። #ማንነት #በገብያ #ህግ #ስለማይተዳደር። ማንነት #ሸቀጥ አይደለም እና። በሌላ በኩል ወጣትነትን የነፃነት ትግል ቅርምጥ አድርጎ ይበላው ዘንድ የተወሰነበት ት የውስጥነት ጉልላታዊ ጉዳይ በአዘቦት ፖለቲካ ለስጦታ ሲቀርብ፤ ዝምታ አሻም ይባላል።
ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲያሰኛቸው የጎንደር #ሸኔ ይላሉ፤ ማርሻላቸው የወሎ እና የጎንደር ሽፍቶች ይላሉ። ሲያሻቸው ደግሞ ዶር አብይ አህመድ ከገዛሁት ምግብ ውጭ በእርጎ ጭማሪ ተስተናገዱ እና #የትዳር ሁነቴን ወሰንኩበት ይላሉ። የኦሮምያ የከተማ ቢሮ ኃላፊ ሳሉም የጎንደር ብቸኛው ጠበቃ፤ ስለ ጎንደር ግድ የሚላቸው ስለመሆኑ ንግግራቸውን አዳምጫለሁኝ። ቃልን ማጠፍ ብረትን የማጠፍ ያህል ቀላል አይደለም።
የሆነ ሆኖ በሌላ ጊዜም አቅጣጫችን ወደ ጎንደር ነው "እናንተ ጥላችሁ ብትሄዱ እኛ እንኖርበታለን" ሲሉም አድምጫለሁኝ በመቶ ቀናቸው የመጀመሪያ ጉብኝት ጊዜያቸው። የሆነ ሆኖ #በማይቀለደው #አይቀለድም፤ #ተረብ #በማያሰኜው አመክንዮ #ገባወጣዊ ስላቅ አያሰኜውም።
ዝምታው በኢትዮጵያም ውጭም ያለው የእኛነት ጉዳይ ብዙ ውጣውረድ በዛ እና ሁሉንም #ተግ ብሎ ማድመጡ ይበጃል በሚል እንጂ ሙግቱማ ተኖረበት እኮ። የብሄራዊነት ጉዳይ በዙሪያ ገባው ተሰቅዞ ሲያዝ ቅድሚያ መስጠት ያስፈልግ ነበር። አገር ስላለች ነው ብልጽግናም ተንፈራሶ ሰርግ ግብረ ሰላም፤ ምቹ ጉዞ የሚያደርገው። እኛም ከጠበለ ጣዲጉ ባይደርሰንም መጠሪያችን እንዳይከፋት ጥንቃቄ ማስቀደም ይገባ ነበር። እንዲህ ፋክትን የሚያዳልጥ የቅልጣን ፖለቲካ ሲመጣ ግን ቸልታ አይገባም። ማይካድራን ብቻ ሳይሆን ከዛ ቀደም የነበሩ ጭካኔወች ከልጅነት ጀምሮ ተኖረበት እኮ።
የእኔ ቅኖች እንዴት ነን? አውዲዮው አብዝቶ #ትዕግሥትን ይጠይቃል፤ ግን አክብሮታዊ፤ ትህትናዊ ፋክቶችን እያዋዛሁ የሞገትኩበት ስለሆነ ጉዳዩ የእኔ ለሚለው ወገን የሚበጅ ይመስለኛል። እኔ ዩቱብ ቻናሌ ላይ ሠርቼ ካስቀመጥኩት አንዱ ይህ ነው። ሁለተኛውም ይቀጥላል። ሦስተኛውም ይሰለሳል። ለማዋዣ ግን #መቅድሙን እንሆ። ………
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉትሻ 01/02/2026

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ