የወልቃይት ጉዳይን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መልስ ሰጥተውበታል
https://www.youtube.com/watch?v=Z4vI8mHgxkI
“ተፈናቃይን መያዣ ያደረገ ፖለቲካ”
የወልቃይት ጉዳይን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ፍንትው ያለ መልስ ሰጥተውበታል። የመንግሥታቸውን #አቋም ገልጸዋል። "እኔ መብት የለኝም" ብለዋል። ወሳኙ እዛው የሚኖረው ህዝብ ነው ብለዋል። ይህን አቋማቸው አጽንተው ይቆዩ አይቆዩ የሚውቀው ፈጣሪ ነው። በሌላ በኩልም ከሌላው ጊዜ በተለየም #ጸጸትም አለበት በንግግራቸው ውስጥ የጤና፤ የትምህርት፤ የበጀት ጉዳይን አስመልክቶ መንግሥታቸው ሳያሟላ መቆየቱ #በደል መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ አንድ የሚዲያ ሰብእና፤ እንደ አንድ የአገሩን ፖለቲካ በትጋት እንደሚከታተል ሰብዕና በአንድም በሌላም ቤተሰብ ሳገኝ ስጠይቅ የፈለገ ችግር ቢፈትናቸውም #ከነፃነታቸው በላይ ሊሆን እንደማይችል፤ ሙሉ ነፃነት ላይ እንዳሉ ገልጸውልኛል። ትናንት እንደፃፍኩትም አካባቢው #ፍጹም ሰላም መሆኑ ብቻ ሳይሆን በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አመራር፤ በሠራዊቱ ላይም ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ያረጋገጥኩት ሃቅ ነው።
እኔ የሚገርመኝ ዘመን አልፎት እየነጎደ የሚገኜው አኞው የህወሃት ከፍተኛ አመራር ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ አዲረመጥ፤ ጠለምት፤ ማይጠምሪ፤ ሰቲት፤ ራያ እኮ #በእጁ እያሉ ነበር መብረቃዊ ያለውን #ጦርነት የጀመረው። "ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት" ሆኖ ነገሩ ዛሬ "የትግራይ ሉዓላዊነት" ካልተመለሰ በጅ አልልም ሲል አዳምጠዋለሁኝ። ቀድሞ ነገር ክልል ብሎ ሉዓላዊነት የለም።
ምን አልባት ገዢ ሳለ በዚህ ስሌት ሊሆን ይችላል የወቅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ዘውዱ ጎንደርን የተዳፈሩት በትዕቢት። ክብረ ልዕልናቸው ያከተመውም በዚህ በተንጠራራ፤ ልኩን ባልመዘነ ዕሳቤ ነው። አይዋ ህወሃት ምሬቱን ማዝነብ ካለበት በራሱ ሰው ላይ ሊሆን ይገበል። የዚህ ሁሉ ግፍ ባለቤት አቶ አባይ ወልዱ ስለሆኑ።
በጦርነቱ ከስሮ ነው የቀረው ህወሃት። "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣላች" ነው የሆነበት። እሱ የሚኒሊክን ቤተ መንግሥት መንበረ መንግሥቱን አለመ። #ከሸፈ። በዚህ ላይ እራሱ ለመረጠው ጠቅላይ ሚር መጠነ ሰፊ ንቀቱ ነው ከዚህ ያደረሰው። በመሃል የትግራይ እናቶች ተጎዱ።
አሁን ምክንያት ያልነበረውን አመክንዮ መሻቱን አዳምጣለሁኝ። ወልቃይት ካልተመለሰ ወዘተ የመነሻ ምክንያቱ ስላልነበረ፤ የመፍትሄ አመንጭም ሊሆን አይችልም። በዚህ በዛሬው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ንግግር ልክ እንደ እኔ ያዘኑበት የአማራ ክልልን ያወደመበት ጉዳይም ከውስጣቸው ፈልቆ ሃዘናቸውን ሲገልጹ አዳምጫለሁኝ። እኔ በጣም ለረጅም ጊዜ ዝም ብዬ፤ ህወሃትን ሳልናገር፤ ሳልሞግት ቆይቼ አፋር እና አማራን ሲያጠቃ፤ ሲበቀል ግን አዝኜ ነበር። የማይድን በቀል አምራች፤ #ቀናተኛ #ቅንቅን ድርጅት ስለመሆኑ ያረጋገጥኩበት አጋጣሚ ነበር። ቅን ልቦና ያላችሁ የቤታችን ቤተኞች ታዳምጡት ዘንድ እንሆ።
ውዶቼ እንዴት አደራችሁልኝ።
ሥርጉትሻ 03/02/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ