#የሃቅ #ዓራት #ዓይናማ #አርበኞችም

 

ይህ ሁለተኛው ለዛሬ የመደብኩት ነው። በዚህ የሰቆቃ ማዕቀፍ ውስጥ ዕውነተኛ #ዕውነቶን የተጋሩ #የሃቅ #ዓራት #ዓይናማ #አርበኞችም እንዳሉበት በማስተዋል፤ ሚዛናዊ ሆኖ ማድመጥ ይገባል። የትናንት ሰቆቃ ዛሬ እንዳይደገም #የታረመ #የሰብአዊነት ፖለቲካዊ ጥንቁቅ #ውሳኔ ይጠይቃል። ፖለቲካ #ለሰው እንጂ #ለጉዑዝ አይደለም እና። 
 
 https://www.youtube.com/watch?v=jwe8odXj1oU
 
ለነገሩ ዶር ዳኛቸው ከሰሞኑ ከአንድአፍታ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ለጎንደር #ዘፈኑን ተሸልሟል" ሲሉ እኔ #አጠይመው የተናገሩት ቅኔ በውስጤ ነበር አድሮ የዋለው። በጣም ሴንሲቲብ #ጉዳዬ ነውና። ዶር ዳኛቸው በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ላይ #ልልት ያለ፤ በእርግጠኝነት የሚናገሩበት ሁነት አጥቼውም ነበር። ከብልጽግናው የደህንነት ሰው ከአንባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር የነበረው ቆይታም ዓላማው እና ግቡ እኔ በመደዴ አላየሁትም ነበር። ሚኒስትሮ ለጎንደር ያላቸው ምልከታ፤ ለህወሃት ካላቸው ፍቅር ጋር እንደሚላተምባቸው በቃለ ምልልሳቸው ላይ ፈጦ የወጣ ሃቅ ነበር። ዘልፈው እኮ ነበር። #ባለጊዜ ናቸዋ። 
 
ውዶቼ ዛሬን በዚህ፤ ነገን ደግም በተፈቀደልን #የመሆን ሩም ውስጥ የምለውን እላለሁኝ። ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ አመክንዮ በድፍረት እና በጭካኔ #ሲፈቀፈቅ፤ እንደ ከብት አሞሌ ሰጥቶ ማባበል የማይችለው የሰው ልጅ ክብር፤ ማዕረግ እና ሞገስ #ለለት ደራሽ፤ ፊርማው ላልደረቀ #የስምረታ ፓርቲ #እጅ #መንሻ ሲቀርብ፤ ዝምታ #በደል ነው። ዝምታ የንጹኃንን አጥንት ከመቃብር አውጥቶ #እንደማቃጠል እቆጥረዋለሁኝ። 
 
ቸር ሰንበት። ደህና እደሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉትሻ 01/2926

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።