ልጥፎች

እናትም፤ ሚስጢርም፤ ትርታም ኢትዮጵያ።

ምስል
 

የቀጣይ የጠቅላይ ሚር #እጩነት ከወደ ጋንቤላ።

ምስል
  የቀጣይ የጠቅላይ ሚር #እጩነት ከወደ ጋንቤላ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።     #ጠብታ ። በቅድሚያ ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? እንዴት ነን??? ዘለግ ያለ ሃሳብ ነው ያለኝ። በተለይ በአውራው መሪ ፓርቲ በብልጽግና ላይ። ከምርጫ በኋላም ብልጽግና ኢትዮጵያን የመምራት ዕድሉ 50+ ነው። ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱም በእሱ ላይ ጠንከር ይላል። ትዝብቴ ሁለገብ ነው። ዕይታይም ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት የአመራር እና የፋክክር ሁነት ጋር የተገናዘበ ነው። ሁለተኛ ሴት እጩ ጠቅላይ ሚኒስተር የመሻት አዝማሚያውም ትኩረቴን ሳብ አድርጎታል። ብዙ ጊዜ ዩቱብ ቻናል ላይ አንባሳደር #ሬድዋን ሁሴን ብቅ ሲሉ ሚዲያ ላይ፤ ወይንም ከጠቅላዩ ጋር ጉዞን ሲጋሩ፤ ከሥር የተሰጠውን አስተያዬት ሳነብ ቀጣዩ #ጠቅላይ ሚኒስተራችን የሚል አነባለሁኝ። በተደጋጋሚ ይህን ገጠመኝ አያለሁኝ። ከዚህ አንፃር ከወደ ጋንቤላ መሻቱን ለዛውም ከአንስት ፖለቲከኛ በቅርቡ አስተዋልኩኝ። በፊት ጊዜ የኢህፓዋ ጸሐፊ ወይዘሮ ደስታን ነበር ያዳመጥኩት። ከሰምኑ ጠይም ዕንቁዋ ከወደ ጋንቤላ ከደቡብ መሻቱ ከች ብለዋል። #መሻት - መፈለግ - መመኜት መብት ነው። የ2018 የምርጫ ክርክር በEBC ተከታተልኩት። አራት የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፋበት ነበር። ብልጽግና፤ አብን፤ ነፃነት እና እኩልነት እና ትብብር ለኢትዮጵያ። ጭብጡ ወጣት ተኮር ነበር። አራት አንስት የፖለቲካ ሊቃናት ተሳትፈዋል። ሁለቱ #ከብልፄው ፤ አንድ ከትብብር፤ አንድ ከነፃነት እኩልነት። አብን በልሙጥነት። አንዲት ሴት የፖለቲካ ሊሂቅ ለማብቀል ያላጣረ፤ ያላሰበለም፤ ብዙ ተጠብቆ በብዙ አመክንዮወች የልብ ሳያደርስ የቀረ ነው። ለምስረታው ጉዝጓዙ ግን ትንታግ ...

#ልዕልቷ አዲስዬ #ሆይ ዘ - ረ - ክ - ረ - ክነት ከናፋቀሽ #እነሆት እቴጌ።

ምስል
  #ልዕልቷ አዲስዬ #ሆይ ዘ - ረ - ክ - ረ - ክነት ከናፋቀሽ #እነሆት እቴጌ።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"       #ምዕራፍ ፲፰   የዓይኔ አበባ ልዕልቷ፤ የእቴጌ ጣይቱ ከተማ የማትጠገቢው፤ የእኛ የሁላችን የህሊና ትርታ፤ የኢትዮጵያዊነት ማዕረግ እና ልዕልና መግለጫ #ርዕሰ - ተስፋችን፤ የወላችን፤ የሁላችን የውስጥነት አንባ ከተማችን፤ የዓለም የዲፕሎማሲ ፬ኛይቱ ተናፋቂ መዲና፤   የእማማ አፍሪካ ዕንቁ እናታዊ ከተማ እንሆ #ዘረክረክ ያለ፤ መላ ቅጡን ያጣ የአመራር፤ የአስተዳደር ሁነት እንዲያው #ትዝ ካለሽ ወይንም #ሽው ካለሽ፤ ወይንም #ን - ፍ - ቅ ካለሽ፤ ካሰኜሽም ዘመን ጠገቡ #ኦፌኮ ለማነው ባለተራ ላይ ተሰልፏል። ለ2018 ዓም ምርጫ ልክሽ እኔው ነኝ እያለሽ ነው።    እና ውዷ ናፍቆት ውቢቷ ደጊቷ #እጀ - ረጅሟ ድንቋ አዲስ አበባ ሆይ! ምርጫው ያንቺ ነው። እንዳትረሺ የዕድሜ ጠገቡ ድርጅት አንዲት ብቁ፤ መካች የፖለቲካ ሊቅ የሆነች #ሴት ፖለቲከኛ ያላፈራ፤ ነገሽን አበጃለሁ ብሎ ከች በሏል።   ዕድሜ ጠገቡ ኦፌኮ እንደ ሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች ተቀናጅቶም፤ ተባብሮም፤ ህብረትን ፈጥሮም፤ መድረክን ሰርቶም ሰማዕትን ቤተሰቦቹ ከመቀበል በስተቀር ያዬነው #እሸት ከቶውንም የለም። ግን ቅኔውን ይዘርፈዋል። #አሽሙሩን ያስነካዋል፤ ይህም ካማረሽ እንሆት …………… ሌላም ወጣት ፖለቲካ አፍርቶም ዘመኑን ለዘሙኑ ወጣቶች ለማስረከብም #ድብታ ጎዳናዬ ነው ያለ፤ ግን በቁንጮ የፖለቲካ ሳይንስ ሊቀ - ሊቃውንት የሚመራ የመጀመሪያው የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ዘመኑ ግን ያለ ምን ፦፦፦፦፦ የነጎደ ……… ...

እሺ አማራ ክልል ሆይ! ጃኬት መልበስ ካሰኜህ እንዲህም #ዘነፍ አድርገህ አስነካው።

ምስል
  እሺ አማራ ክልል ሆይ! ጃኬት መልበስ ካሰኜህ እንዲህም #ዘነፍ አድርገህ አስነካው።     "ነፍስ ካለ መንቀሳቀስ አይገድ።" ትል ነበር ጽግሽ። ማህበረ ኦነግ ለእኔ እንደዚህው ነው። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ ፓርላማ ከገባ ማስፈራሪያ ይሆናል። ይህን አቤቱ ብልጽግና ይፈልገዋል። ለምን? "እኔ እሻላችኋላሁን" ለማዘከር። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፰።   አቤቱ የአማራ ክልል ብልጽግና ማህበረ ደጋፊወቹ ጃጌቷን ሹፏት ……… ኦነግ መንፈሱ ወጥ ነው። በመንፈሱ ውስጥ ያለውም እሱ እራሱ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በውስጡ ተፈጥራ ሳይሆን ጽንሰቷም ታስቦም አያውቅም። ኦነግ #የሚፎካከረው ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ነው።    አማራ ክልል ደግሞ ጽንሰቱም ትርታሙ ኢትዮጵያ ናት። አሁን አማራ ክልል ተሸከም የተባለው የገዘፈ ጫን ተደል #መከራ በጸረ ኢትዮጵያ መንፈስ የተቃኜውን፤ በጥላቻ የበቀለውን፤ በበቀል የተቃኜውን፤ በመጥላት - በመቅናት ኢትዮጵያን ሲፎካከር የኖረ ድርጅት ተሸከም ተብሏል። "በሬ ካራጁ" እንዲሉ የአማራ ክልል ፈቃዱን ሰጥቶ አሳርን እንደለመደበት በገፍ ይሸማምት።   ጃኬትን እንኳን አስተካክሎ ለመልበስ የተሳነው፤ ከእራሱ ፍላጎት በስተቀር በግሎባል ዘመን እዛው በራሱ ውስጥ መጠለያ ሠርቶ የኖረ፤ የሚኖርን ኩድኩድ ዕሳቤ የአማራ ክልል ተቀብሎ፤ ኃላፊነት ወስዶ፤ ጉንብስ ቀና ብሎ አደግድጎ፤ "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበትን" እንደሚያስፈጽም ለዛውም ካባ ሸልሞም ልብ ልክ ነው።   ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በአማራ ክልል ላይ ያለውን መሻታቸው የሚያስፈጽሙት " #ይሁነን " ብለን ያሉትን ብልጽግና ቦታውን ለቀቅ አድርጎ ትራጀዲውን ይፈጽማል...

ክብርት ሆይ! እጩ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ከወደ ጋንቤላ #ሃሳቡን እና ሰብአዊነትን እንደምን ሊያስታርቁት አሰቡ?

ምስል
  ክብርት ሆይ! እጩ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ከወደ ጋንቤላ #ሃሳቡን እና ሰብአዊነትን እንደምን ሊያስታርቁት አሰቡ?   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"       #ምዕራፍ ፲፰።   #ክብርት ሆይ!   እንዴት ሰነበቱልን? የፎቶ ቅደም ተከተል ግር እንዳይለወት። እኔ በጋሜዬ ጊዜ ነበር ህይወቱን የፖለቲካውን የጀመርኩት። ስለሆነም እያንዳንዱን ቅንጣት ሁነት ከውስጤ በአትኩሮት ነው እምከታተለው። ስለሆነም በፖለቲካ ህይወት ውስጥ #ሲነሪቲ የሚባል የፕሮቶኮል ጥያቄ አለ።   ስለሆነም እጅግ የማከብረው አቶ ኦባንግ ሜቶ ከእርሰወ የቀደመ የፖለቲካ ተሳትፎ ስላለው፤ በሲነሪቲ እንደሚበልጠወት ስለማውቅ ነው እሱን ያስቀደምኩት። በዚህ አጋጣሚ ሁለት ጠይም #ዕንቁ የአገሬን ልጆች ላፈራችው ጋንቤላ ምስጋናዬ ከልብ ነው። #መቅድመ የፖለቲካ ውሳኔ።   የህወሃት ሥርዕወ - መንግሥት ፍፃሜ ሲጠናቀቅ የቀደመ ውሳኔ ያሳለፈ አቶ ኦባንግ ሜቶ ነበር። ምን ብሎ ይመስለወታል ክብርት ሆይ! ያ ውሳኔ ከእርስወም ተሳትፎ የሚቀድም ይመስለኛል። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን " #የእኔ ጠቅላይ ሚኒስተር" ያለ የመጀመሪያው ሰው ነበር። እኔ እንዲያውም በዘርፋ ትጉህ ስለነበርኩ ጽፌበታለሁኝ።   ከዛ ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ፤ የመኢሶኑ ዶር ነገደ ጎበዜ በተጨማሪም ታላላቅ ቀደምት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስተራችን አብይ አህመድ ሲሉ ተደመጡ። ታላላቆቼ በአደባባይ ወጥተው ድምፃቸውን ሲሰጡ እዬተከታተልኩ እኔ እጽፍ ነበር። በሩን #ቧ #ፏ አድርጎ የከፈተው ግን አቶ ኦባንግ ሜቶ ነበር።    እኔ ከኢንጂነር ስመኜው ህልፈት በኋላ እማልወ...