#ልዕልቷ አዲስዬ #ሆይ ዘ - ረ - ክ - ረ - ክነት ከናፋቀሽ #እነሆት እቴጌ።

 

#ልዕልቷ አዲስዬ #ሆይ ዘ - ረ - ክ - ረ - ክነት ከናፋቀሽ #እነሆት እቴጌ።
 
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"
 
 No photo description available.
 
 
የዓይኔ አበባ ልዕልቷ፤
የእቴጌ ጣይቱ ከተማ የማትጠገቢው፤
የእኛ የሁላችን የህሊና ትርታ፤
የኢትዮጵያዊነት ማዕረግ እና ልዕልና መግለጫ #ርዕሰ - ተስፋችን፤
የወላችን፤ የሁላችን የውስጥነት አንባ ከተማችን፤
የዓለም የዲፕሎማሲ ፬ኛይቱ ተናፋቂ መዲና፤
 
የእማማ አፍሪካ ዕንቁ እናታዊ ከተማ እንሆ #ዘረክረክ ያለ፤ መላ ቅጡን ያጣ የአመራር፤ የአስተዳደር ሁነት እንዲያው #ትዝ ካለሽ ወይንም #ሽው ካለሽ፤ ወይንም #ን - ፍ - ቅ ካለሽ፤ ካሰኜሽም ዘመን ጠገቡ #ኦፌኮ ለማነው ባለተራ ላይ ተሰልፏል። ለ2018 ዓም ምርጫ ልክሽ እኔው ነኝ እያለሽ ነው። 
 
እና ውዷ ናፍቆት ውቢቷ ደጊቷ #እጀ - ረጅሟ ድንቋ አዲስ አበባ ሆይ! ምርጫው ያንቺ ነው። እንዳትረሺ የዕድሜ ጠገቡ ድርጅት አንዲት ብቁ፤ መካች የፖለቲካ ሊቅ የሆነች #ሴት ፖለቲከኛ ያላፈራ፤ ነገሽን አበጃለሁ ብሎ ከች በሏል።
 
ዕድሜ ጠገቡ ኦፌኮ እንደ ሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች ተቀናጅቶም፤ ተባብሮም፤ ህብረትን ፈጥሮም፤ መድረክን ሰርቶም ሰማዕትን ቤተሰቦቹ ከመቀበል በስተቀር ያዬነው #እሸት ከቶውንም የለም። ግን ቅኔውን ይዘርፈዋል። #አሽሙሩን ያስነካዋል፤ ይህም ካማረሽ እንሆት ……………
ሌላም ወጣት ፖለቲካ አፍርቶም ዘመኑን ለዘሙኑ ወጣቶች ለማስረከብም #ድብታ ጎዳናዬ ነው ያለ፤ ግን በቁንጮ የፖለቲካ ሳይንስ ሊቀ - ሊቃውንት የሚመራ የመጀመሪያው የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ዘመኑ ግን ያለ ምን ፦፦፦፦፦ የነጎደ ………
 
አደራ እናትዬ ከጠረጴዛ ሥር የወዳደቁት ቤተ - #አቧራን የፈቀዱ አሻንጉሊቶችን ቃኜት አድርጊያቸው። ለአጸደ ህፃናት ግንባታ ቅርስ እና ውርስ ናቸው እና። አንድ ቀን ሙዚዬም ተሰርቶላቸው የጎብኙኝ ጥሪ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ማን ያውቃል??? ለዛውም ከዘመን ጠገቡ ኦፌኮ በስጦታ የቀረበ ከበር ደልደል ባለው የህሊና ዓይንሽ ማትሪያቸው።
 
ክብርት አዲስ አበባ ሆይ!
 
ግን እስቲ እናት ሆዱ ገምች ይህን ቢሮ ፋይሉን በማቀፊያ በየጉዳዩ ለይቶ፤ አደራጅቶ በስሱ እንኳን፤ ዓይነ - ገብ ለማድረግ ስንት ጊዜ ይፈጃል? ይህም ወጪ ነው። #በጀት ይፈልጋል። ተቅዱ ደረብ አድርጊ እንደማለት። በኋላ መንደፋደፍ እንዳይመጣ ………
 
#መስቃውንስ ትችይው ----- ይሆን እናቱ ??? ጥናት መቀነቱን ይስጥሽ። አሜን።
 
መልካም ዕድል ለዕድሜ ጠገቡ - ለኦፌኮሻ። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
ግን ማህበረ - ትጉኃን እንደምን ሰነበታችሁ።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ፥
SerguteSelassie.
25/03/026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ ይሁን ጋራጅ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።