"የተሻለ ህክምና እያገኘሁ ባለመሆኔ ለከፍተኛ ስቃይ ተዳርጌያለሁ ፤ ሕይወቴም አደጋ ላይ ነው" ሲሉ የተከበሩ ዶክተር ካሳ ተሻገር ገለጹ። (አውሎግሶን አንድነት ፣ መጋቢት 15/2018)
"ከልብ እና ከነርብ ጋር በተያያዘ ላጋጠመኝ የጤና ችግር የተሻለ ህክምና እያገኘሁ ባለመሆኔ ለከፍተኛ ስቃይ ተዳርጌያለሁ ፤ ሕይወቴም አደጋ ላይ ነው" ሲሉ የተከበሩ ዶክተር ካሳ ተሻገር ገለጹ።
የተከበሩ ዶክተር ካሳ ተሻገር መጋቢት 14/2018 በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድር ምድብ 2ኛ የህገ መንግስትና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት በቀደመ ቀጠራቸው መሠረት ከአባሪዎቻቸው ጋር ቀርበው ነበር።
ዶክተር ካሳ እንደገለጹት ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም ፣ የነርብ እና የግፊት ህመም አለባቸዉ።
የህክምና አገልግሎቱም የተንዛዝዛና ረዥም ቀጠሮ እየተሰጣቸው በመሆኑ እንዲሁም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትም ሰበብ እየፈጠረ ከህክምና ስለሚያስቀራቸው ለከፍተኛ ስቃይ መደረጋቸው ገልጸዋል።
"ሕይወቴ አደጋ ላይ ነው፤ ልጆቼ እንዳያጡኝ እሰጋለሁ" በማለት ቀልጣፋ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የገጠማቸውን ከፍተኛ የልብ ህመም በግል የህክምና ተቋም ገብተው ለመታከም እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የኦቲዝም ህመምተኛ የሆነ የ19 አመት ልጃቸው ጋር በልዩ ሁኔታ በስልክ እና በአካል በመገናኘት እንዲንከባከቡት በሚል ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ በማረሚያ ቤቱ ተፈጻሚ እየተደረገ አይደለም ብለዋል።
ማረሚያ ቤቱ ከቀናት በፊት ልጅህን እንድታገኝ ተፈቅዶልሃል በማለት ያገናኛቸው ቢሆንም አስር ደቂቃ ሳይቆይ ልጃቸው እያለቀሰ እንዲመለስ አድርጓል።
"ልጄ እያለቀሰ ሲመለስ እንኳ ምንም ዓይነት ሰብዓዊ መብት ርህራሄ አይታይባቸውም ፤ ይህ በጣም አሳዛኝ ነገር ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
በሌላ በኩል ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገባ የሚከለክለው መጽሐፍ "አማራ" የሚል ስም ያለበት ነው ብለዋል።
ማ/ቤቱ ለዞን 4 እና 5 ቤተ መጽሀፍት እንዳላዘጋጀ ገልፀው ቤተሰብ አስቸግረን ከውጭ የምናስመጣውን የአካዳሚክ መጽሀፍ
ሳይቀር ሰበብ እየፈጠረ እንዳይገባ ማድረጉ የመጻፍ እና የማንበብ መብትን የሚጋፋ ነው ሲሉ እንዲስተካከል ጠይቀዋል።
እኛ ብሔር እና ሐይማኖት የሚያጋጭ መጽሀፍ አናስገባም ፤ ይልቁንስ ማ/ቤቱ ራሱ በጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች የተጻፉ መጽሀፍትን አስገብቷል ሲሉ ፍትሃዊ አሰራር አለመሆኑን ተናግረዋል።
(አውሎግሶን አንድነት ፣ መጋቢት 15/2018)
No insights to show
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ