እሺ አማራ ክልል ሆይ! ጃኬት መልበስ ካሰኜህ እንዲህም #ዘነፍ አድርገህ አስነካው።
"ነፍስ ካለ መንቀሳቀስ አይገድ።" ትል ነበር ጽግሽ። ማህበረ ኦነግ ለእኔ እንደዚህው ነው። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ ፓርላማ ከገባ ማስፈራሪያ ይሆናል። ይህን አቤቱ ብልጽግና ይፈልገዋል። ለምን? "እኔ እሻላችኋላሁን" ለማዘከር።
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፲፰።
አቤቱ የአማራ ክልል ብልጽግና ማህበረ ደጋፊወቹ ጃጌቷን ሹፏት ………
ኦነግ መንፈሱ ወጥ ነው። በመንፈሱ ውስጥ ያለውም እሱ እራሱ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በውስጡ ተፈጥራ ሳይሆን ጽንሰቷም ታስቦም አያውቅም። ኦነግ #የሚፎካከረው ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ነው።
አማራ ክልል ደግሞ ጽንሰቱም ትርታሙ ኢትዮጵያ ናት። አሁን አማራ ክልል ተሸከም የተባለው የገዘፈ ጫን ተደል #መከራ በጸረ ኢትዮጵያ መንፈስ የተቃኜውን፤ በጥላቻ የበቀለውን፤ በበቀል የተቃኜውን፤ በመጥላት - በመቅናት ኢትዮጵያን ሲፎካከር የኖረ ድርጅት ተሸከም ተብሏል። "በሬ ካራጁ" እንዲሉ የአማራ ክልል ፈቃዱን ሰጥቶ አሳርን እንደለመደበት በገፍ ይሸማምት።
ጃኬትን እንኳን አስተካክሎ ለመልበስ የተሳነው፤ ከእራሱ ፍላጎት በስተቀር በግሎባል ዘመን እዛው በራሱ ውስጥ መጠለያ ሠርቶ የኖረ፤ የሚኖርን ኩድኩድ ዕሳቤ የአማራ ክልል ተቀብሎ፤ ኃላፊነት ወስዶ፤ ጉንብስ ቀና ብሎ አደግድጎ፤ "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበትን" እንደሚያስፈጽም ለዛውም ካባ ሸልሞም ልብ ልክ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በአማራ ክልል ላይ ያለውን መሻታቸው የሚያስፈጽሙት "#ይሁነን" ብለን ያሉትን ብልጽግና ቦታውን ለቀቅ አድርጎ ትራጀዲውን ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል።
መከራ የማይሰለቸው፤ መሸከም #የማይጠግበው የአማራ ክልል በቃ! አይሆንም! አይደረግም! ብሎ በእጩ የማህበረ ኦነግ ተወዳዳሪወች ላይ፤ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ይወስናል ተብሎ አይታሰብም። መረማመጃነት፤ አንጋችነት የማይሰለቸው ጉደኛ ነው ያለው የአማራ ክልል አመራር። እንደ ሲዳማ፤ እንደ ሱማሌ ክልል ክህሎትም አቅም የለውም። ትናንት በህወሃት ዛሬ በብልጽግና ፍላጎት ሰግዶ ይገዛል። አሁን ከብልጽግናም አልፎ ተርፎ ኦነግን ለማስተናገድ በጉጉት ይጠብቃል። እርግማን።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ ፈታኙ ጉዳይ የኦነጉ መሪ አቶ #ዳውድ ኢብሳን ማድመጥ ነው። በህይወቴ ለማድመጥ የሚቸግረኝ የሳቸው ንግግር ነው። ፖለቲከኛ አንደበቱ ያዝ ጨበጥ ሳብ ሊያደርግ ይገባል። እሳቸው ገና አንደበታቸው አህዱ ሲል ሲናገሩ የሆነ አንዳች ነገር የሚጫናችሁ #ደመመን አለ። #ይጨንቃችኋል። #ይጫናችኋል። ያፍናችኋል ንጹህ አየር #ታጣላችሁ። መተንፈሻ ቧንቧችሁ ዝግትግት ይላል። ይህን መከራ ለተሸከመችው ኢትዮጵያ እጅግ ከውስጤ አዝንላታለሁኝ።
እሰቡት ይህ ሰብዕና ፓርላማ ሲገባ። መርገምት ነው የሚሆነው። #ፍዳ ነው የሚሆነው። ጭንቅ በገፍ ነው የሚቀናው። በብዙ ሁነት ለሰዋዊ ተፈጥሮ እጅግ ፈታኙ ገጠመኝ አቶ ዳውድ ኢብሳ የፓርላማ አባል ከሆኑ ብቻ ነው።
በኦሮምያ ቋንቋውን ስለማንሰማው የፈረደበትን የኦሮምያ ክልል ሊሸከም ይችላል። የግድም ነው። በአማራ ክልል፤ በኢትዮጵያ መጪው የፓርላማ ሂደት ግን እኔ የማስበው ከሰማይ የተላከ **#የጦሮ አለሎ ነው። ከሳቸው ውጪ ያሉ አመራሮች ዕድሉን ቢያገኙ ግድ የለኝም። እሳቸው ተወዳዳሪ ከሆኑ ግን ሙሉ ፭ ዓመታት ምጥ እና ዳጥ ይሆናል የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ።
አዲሱን የፓርላማ ውሎ ለሚከታተለው ሁሉ በሽታ በገፍ ይቀናለታል። ዕውነት ለመናገር ለፖለቲካ ንግግር ብቻ ሳይሆን፤ ለመኖርም ዬከብዳሉ እንደዚህ አንደበቱ ኪሎማንጃሮ ወይንም አላስካ የሆነ ሰብዕና። አቶ ዳውድ ኢብሳ #ይጨንቃሉ። ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሥነ - ልቦና መከራ ያስተናግድ ካልተባለ በስተቀር ይህ መስመር የከፋ ጊዜን ጠሪ ይሆናል።
የኦሮሞ የፖለቲካ ሊቅ ሆነው የተሰጣቸው፤ በማንስማማበት አቋም ቢሆን እንኳን ማድመጥን የምንፈቅድላቸው ሰብዕናወች አሉ። ለዛ ያላቸው፤ ግርማ ሞገስ ኖሯቸው ቅልል ያሉ፤ የጨመቱ፤ በብዙ ተዕቅቦ ሁነት ለመኖር የፈቀዱ እንደ #ዶር. ለማ መገርሳ የመሰሉ ጣዕም ያላቸው፤ የማይክለፈለፋ #ኦሮሞ ይቅደም የሚሉ አሉ።
የሚገርመኝ በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ እስከዚህች ዕለት ድረስ መሪነትን ያስቀጠሉት፤ የኦሮሞ ሊቃናት ለኦሮሞ ፖለቲካ በተለየም ለማህበረ ኦነግ ባለውለታ ናቸው። የትምም ሊያገኛቸው አይችልም። ያልታሰቡ ያልታቀዱ ስጦታወች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እያዘናጉ፤ እያዋዙ፤ እያለሳለሱ በኢትዮጵያ ሙሉ አቅም በግልጽም በስውርም የማህበረ ኦነግን መሻት ከ150% በላይ አሳክተውታል።
ከጥዋት ከማታ ያልታሰበ ሲሳይ ነበር የ2010 ዕድል። በብአዴን ትክሻ ኦህዴድ ያሳካው። ህልም ነው። የታምርም ያህል ነው። ተከብረው አገር ሲገቡ የነበረው ሸር ጉድ ይገርመኝ ነበር። ተቦላ ነው የደረሳቸው። ይህን ዕድል ማስቀጠል ብልህነት ነበር። ታጣቂ አደራጅተው የዕንባ መኽር አቅዶ ከማስፈጸም ይልቅ። አሁን ደግሞ በባዶ የሥራ ልምድ ፓርላማ ታጭቷል። መጥኔ ለማይደክምሽ ፈላስፊት፤ ሳይንቲስት፤ #ዩንቨርሷ ኢትዮጵያ።
ከማህበረ ኦነግ አንዳቸው ይህን ዕድል አገኝተው ቢሆን ኖሮ፤ ዕድሉ #ከመንፈቅ አያልፍም ነበር። ጨንግፎ ለሙሉ ዘመኑ ከወደቀበት እንዳይነሳ ሆኖ ይከስም ነበር የኦነግ ፖለቲካ። ማፎካከር፤ ማወዳደርም የሚቻለው የሚመጣጠን ነገር ሲኖር ነው። አሁን ከአቶ ዳውድ ኢብሳ መሪነት ችኮ ገጠመኝ እንጅ ምን ሊመረት??? ህይወታቸውን ከመሩ በቂ ነው። ኢትዮጵያን ለመምራት አይደለም፤ ሃሳቡን ለማሰብ ወርዱም፤ ቁመቱም የለም። በውነቱ ፖለቲካዊ ህይወት ለሳቸው የተሰጠ አይደለም። #ቅብዓውም የለም። አንዲት ቃል ከሳቸው ለማድመጥ የምጥ ጊዜ ነው።
አብሶ መስዋዕትነቱ በምንም ለተወራረደው የኦነግ ፖለቲካ መልክ ያስያዙ፤ ኦነግ ከጠየቀው፤ ከሚፈልገው በላይ ብቻ ሳይሆን፤ ከህይወት ልምዱም ይሁን በመንግሥት ሥርዓተ - አመራር ለስኬት ላበቁት #ንቀታቸው፤ ዘለፋቸው፤ ማጣጣላቸው ሁልጊዜ ይገርመኛል።
በማህበረ ኦነግ ሊቃናት ከልምድ ነፃ ሆኖ፤ አንዲት የበቃ ሃሳብም፤ ድርጊትም ማሳየት ያልቻሉ፤ ከዛ ተስፋ አጥ ኑሮ በብአዲን በጎ ፈቃድ ሙሉ ዕድሉን ለኦህዴድ አስረክቦ፤ በውጭ ያለውም የአማራ ልጅ ዕድሉ ለኢህዴግ ወጣቶች ይሰጥ እና ይፈተኑ ተብሎ በተገኜው ዕድል የማህበረ ኦነግ ወላዊ መታበዩ #ከልክ በላይ ነበር። መስቃው፤ ትርፍ ንግግሩ ደንበር አልተሰራለትም። ለአማር ህዝብ የተቀናለት ዕንባ እና ንቀት ነው።
ይህን ስል በየዘመኑ የኦሮሞ ልጆች መስዋዕትነት አልከፈሉም እያልኩ አይደለም። እስሩም፤ ሞቱሙ ብዙ ዋጋ በየዘመኑ ከፍለዋል። ስኬቱ የተቋጨው ግን በአማራ ልጆች እግዚአብሄር ከፈጠረው ቅንነት በላይ በተከወነ የጨመተ በሳል የተግባር ዓውድ ነበር ማለት እችላለሁኝ። ድካም ይኖራል። ልፋት ይኖራል። መገበርም ይኖራል። ጥረት የሚሳካው ግን በቅብዓ ነው። በመሰጠት። ሰጩ ደግሞ የላይኛው አማኑኤል አባቴ ነው።
ማህበረ ኦነግ የተሰውት ለኦሮምያ መገንጠል ነው። በታሪኩ ኦነግ አሳከ አኗ ደቂቃ ድረስ አሳካሁ ብሎ የሚናገረው ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ኩነት የለም። ወደፊትም በኩድኩድ ዕሳቤው ፈቅ የሚል ዕድል ይኖረዋል ብዬ አላስብም። ይልቅ "ለኢትዮጵያ ሱሴ" ጥንስስ እና የእኛ መጃጃል ክብር ሊሰጠው ይገባ በነበረ። ለዚህ ያበቃነው እኛው ነን።
አሁን ደግሞ አማራ ክልል እወዳደራለሁ ሲል ኦነግ #ተሸከመኝ ነው። ሸክሙ የማይሰለቸው የአማራ ክልል ደግሞ ተሸካክሞ አዲስ መከራ እና ፍዳ እንደ አመሉ ለአማራ ህዝብ ይሰንቅ። ትናንት አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው። ዛሬ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አረጋ ከበደ በአዲስ የተሃድሶ አቅም ካባ አዘጋጅተው በሽልማት አንቆጥቁጠው ጭነቱን ያስተናግዱ።
#ክወና።
የሞኝነትም፤ የጅልነትም ዓይነት አለው። ሁልጊዜ በባዶ እጅ አጨብጭቦ መጎተት ግን አለመታደል ነው። በኪሳራ ዕድልን ማባከንም የምርቃት #መነሳት ምልክት ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
25/06/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻም ይሁን ጋራጅ አያስፈልገውም።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ