ከቶ ዶር አሚን አማን ጤ/ ጥበቃ ሚር አድርጎ ማሾም ይሆን "ሌብነቱ?"
የት ላይ ነው ያለው „ሌብነቱ“?
ምንስ ላይ ነው ያለው „ሌብነቱ“?
„ከቁጣው ጢስ ወጣ ከፊቱም የሚባላ እሳት ነደደ:
መዝሙረ ዳዊት ፲፯ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Seregute©Selassie
09.01.2019
ከእመ ዝምታ ከሲዊዝ
የጠ/ሚር አብይ አህመድ ሆነ የዶር ገዱ አንዳርጋቸው
መንፈስ ለዚህ ስላበቃ መሰለኝ "ሌባ" ያሰኛቸው
ስለምን ይሆን በዚህ ቀን ብአዴን ለሰጠው
የተንጠራራ ያልተገባም ውክልና
ሌባ ያልተባለበት?
አሳቸውን የፌድራሉ የጤና ጥበቃ ሚነስተር ለማድረግ ነው
20ሺህ አማራ የታሰረበት? የተንኮላሸበት፤ ጥፍሩ የወለቀበትን ቤቱ ይቁጠረው
ያ ተጋድሎ በምን ያህል እጅ ትሩፋት የፖለቲካ ዕውቅናው?
አስገራሚ: የሁመራ ወጣቶች አብይንና ገዱን ሲሳደቡ የሚያሳይ ቪዲዮ
| Amazing : Humera youth insult Dr Abey and Gedu
· ህሊናን …
የዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና የዶር አብይ አህመድ „ሌባነት“ ይሄ ሳይሆን አይቀርም ዶር አሚን አማንን የጤና ጥበቃ ሚ/ር አድርጎ መሾም። የአማራ ታገድሎም የሚስጢር እርገት።
ጎንደር ከተማ ብቻ ከ20 እስከ 30 ሺህ የሚገመት ተጋሩ ይኖራል በሰላም በጤና ዘምኖ። ይህን የምፈልገው እዬታገሁበት ያለ ቢሆን ነገር ግን አዙሮ ማዬት የግድ ይሆናል። ህውሃት ያደራጃቸው ናቸው ያን ያደረጉት ... እና ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል ከሆነ ቻይም አስታገሽም አይኖርም ... በልክ መሆን ያስፈልጋል። በዬቤቱም እሳት አለ የሚንቀለቀለ።
ወሎ ከዚህ ቁጥር ቢበልጥ እንጂ ቢያንስ አይሆን ጎጃም ሽዋውም እንዲሁ ተቀማጥሎ ታገሩ ይኖራል። ዶር ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልላዊ አስተዳደር ሰው ጠፍቶ የተጋሩን ባላበት ብአዴን ወክሎ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር በማድረግ ዶር አሚን አማንን አሹመዋል። ይህን „ሌብነት ቢሉት የሰቲት የህውሃት ምልልሞች ያምርባቸዋል።“
ጠ/ሚር አብይ አህመድም የዶር አሚን አማንን ሳይቃወሙ ክልሉ ያቀረበላቸውን ተቀብለው አጽድቀዋል። እሳቸው ሌላም ዓለምአቀፍ ክፍት ቦታ የሚጠብቃቸው ናቸው። የዓለሙ ጤና ጥበቃ ሚነስተር የዶር ቴውድሮስ አድህኖም የህት ልጅ አይደሉምን? እንዴት ነው ጤና ጥበቃ ለህውሃት የተሸለመበት?
የሚገረመው በሁለተኛው የሚኒሰትር መ/ቤቶች ቁጥር ወደ 20 ዝቅ ባደረገው ሱናሜም ዶር አንባቸው መኮነን ኢንደስትሪ ሚኒስተር ተነስተው ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ሚነስተር ሲሆኑም አቶ ገዱ አንድርጋቸው ውሹ እንዲነሳ አይሹም። የሰነፎች ጥያቄ ነው ባይም ናቸው። በዛ የሁለተኛ ጊዜ የብወዛ ሂደት የጤና ጥበቃ ሚኒስተሩ ዶር አሚን አማን ግን በያዙት ቦታ ቀጥለዋል። ምርጥ ዘር ...
ስለዚህ የዶር አብይ መንግሥትም ሆነ የአቶ ገዱ መስተዳደር ይህን ማድረጉ" ሌባ" መባል ሲያንሰው ነው መወገሩ ስለቀረላቸው ይልቅ እንኳን ደስ አላቸው። መሳሪያ ቢይዙ አይቀርላቸውም ነበር … እነሱም በምስል የተቀመጠውን የብአዴን ውቅር ዕውነት አሳይተውናል። ትናንት ዛሬም ድገም ተብሎ ...
ሌላው የሰቲቱ መሬታችን „መጣብን“ ጉዳይ „ተጠማኝ ሲጠግብ ባለርስት“ ብለው የቀደሙት ሊቃናት ገልጸውታል አያቶቻቸው ለሽቀላ ሥራ ነበር እዛ ሰቲት ይሄዱ የነበሩት። ሌብነት ወራሪነት ዝርፊያ ቢያሳፍር እንጅ እንዲህ ወጥቶ ሌቦችን አውድሶ ንጹሃንን ሌባ የሚያሰኝ ነገር ባላመጣም ነበር።
ዝም ማለት እኮ ለቀጣይ ትውልድ ገና ላልተጸኑስ ዕንቡጦች በግፈኞች ዕዳ የመኖር ዋስትናቸው እንዳይስተጓጎል በሰውኛ ስለምናሰበው ነው እንጂ ዛሬም ያላበራው የአማራ ጥቃት ምንጩ እና መሰረቱ የህወሃት ማንፌሰቶ መሥራቾች ስለመሆኑ ጠፍቶን፤ ሳናውቀው ቀርቶ አይደለም።
አንድም ሊሂቅ አላዬሁም ከተጋሩ አማራዊ መንፈስን ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ። እንዴት እንደሚጠሉን አሁን እራሱ ምን ዓይነት አውሌያ እንደተጫናቸው እያዬሁኝ ነው። የሰጡትን ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ ምን ያህል የተበደለ ዘመን እንደሆነ ይገርመኛል።
የንጉሦች ንግሡ የአጤ ዮሖንስ እትብተኛ ተሁኖ እንዲህ የተጋጠ ምልከታ ልጅ ካወጣ እምናዬው ይሆናል … ያው በወሊድም ሪከርድ ሰባሪ እንደሆኑ ይታወቃል … ለእነሱ አይደለም መመኮሪያ የዘር ምክንት ጣቢያ የሆነው አማራ ብቻ ነው።
በዚህ ዘመን እንኳን ባህርዳር ላይ ነው 300 ብር እዬተሰጣቸው ወጣት ሴቶች መሞከሪያ እንዲሆኑ ተደርጓል እነ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ፊርማቸውን ገጭ ባደረጉላቸው በዘመነ ዶር አሚን አማን …
አሁን ዶር አሚን አማን ወልቃይት ጠገዴ ራያ የማን ነው ብለው ቢጠዬቁ የሚሰጡት መልስ ይታወቃል። ጋዜጠኞች ለምን እንደማይጠይቋቸው አይገባኝም። ሊጠዬቁ ይገባል። ዘመድ ከዘመዱ ነው ... "ያልወለድኩት ልጅ ቢለኝ እባባ አፌን አለኝ ዳባ ዳባ" ነው። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እሳቸው የሚጽሙት የህውሃትን ማንፈሴቶ መንፈስ ነው። እምነት የለኝም እኔ ... ከታላቋ ትግራይ ህልመኝነት ይወጣሉ ብዬ ... ብቻ ይቀልዱ እነ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው። አሁን መቼም የሴክረታርያት ጽ/ቤት ሃላፊ ሆን ብለው እንደማይፎክሩ ነው ... እንደዛ ብለው ብቻ እንዳያስቁኝ ...
ብአዴን የሚገረመው አሁንም አዲስ ሌላ ቀልድ በሙት ዜማ አምጥቷል፤ ካደረሰኝ ዛሬ በሰተቀር ነገ ተነገ ወዲያ እምለስበታለሁኝ። አንድ የህውሃት ማንፌሰቶ ጥምቀተኛ አንደበቱ አድርጎ ሾሟል። የዛ ሁሉ የአማራ ተጋድሎ ርካብ ለማን ጥቅም ተብሎ እንደ ነበረ አጠያያቂ ነው አሁን በወዝኩኝ እያለ ሥልጣን የሚያሰጣቸው ነፍሶች ...ሲፈተሹ ...
· ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል ይላሉ ጎንደሮች።
የደንበሩ መከፈት ጉዳይ በዛለ - አንበሳ በኩል ተዘግቶ ስለምን ኡምንሃጀር ተከፈተም አግባብነት አይደለም። ይህ የፌድራል መንግሥቱ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን የኤርትራ መንግሥትን ሙሉ ፈቀድም የሚጠይቅ ነው። ያሰገናኛል ካለ የኤርትራ መንግሥት መቀበል ነው። በሂደት በጥሞና በበዛ የሃሳብ ፍትጊያ የሚሆን ስለሆነ። ስክነት ለነገሩ? እእ ...
በሌላ በኩል እነ ተጋሩ የህውሃት አውራነት ማክተሙን ስለማያውቁ ወይንም ለመቀበል ስለማይፈቅዱ እንደ ቀደመው አገር ገዢነቱ ያለ ስለመሰላቸው ነው። „አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ" መሆኑን ወጣቶቹ አልተረዱትም። ተቸግረዋል። እንኳን ኢትዮጵያ ላይ እኔ ጀርመን ፍራንከፍት ላይ ታገሩን አቶ ጌታቸው ረዳ ሰብስበው ነበር ባዶውን አዳራሽ ነበር የሰበሰቡት። ጊዜው አልቋል።
በታምር ከእንግዲህ ህውሃት እንደ ድርጀት አገር የመምራት ሥልጣን ያገኛል ብሎ ማሰብ ጸሐይ መሬት ወርዳ ትቀመጣለች የማለት ያህል ነው። ራሱ የህውሃት ማንፌሰቶ መሥራቾችን አረመኔያዊ ተግባር እንደገና ዕድል ይሰጥ ብለው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢፈቅዱ እንኳን አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ ዓለምም በጅ አይልም። ህውሃትን ዓለም እንዴት እንደሚጸዬፈው ማን በነገራችሁ? መጠላት እኮ መከራ ነው። ይልቅ ለዚህ ድንኳን ቢጣል ጥሩ ነው፤ ዕንባ አዋጡም የአባት ...
ነገር ግን ዛለ አንበሳም ይከፈትልን ብሎ መጠዬቅ የተገባ ነው። የተዘጋበት ምክንያት ይገለጽልን ብሎ መጠዬቅም የተገባ ነው። ወጣቶቹ ያልገባቸው ያልተረዱት ነገር አሁን በአብይ መንግሥት ቸርነት ነው የበደለ፤ የዘረፈ፤ የወረረ፤ ግፍ በመጠነ ሰፊ ደባ የፈጸመው ሁሉ ምንም ሳይደርስበት በነበረው ሁኔታ የቀጠለው።
ሚ/ሩ ተቀምጦ ዘበኛ የሆነው ተጋሩ ነበር አማላጁ ወሳኙ። ራሱ የተጋሩ ሹርባ አዬር መንገድ ላይ ልዩ ይለፍ ነበረው። ቋንቋ መቻልም አንዱ የማመላጃ ጉዳይ ነበር። ሌላው ቤት ሠራተኛ አድርጎ ማስቀጥርም ሌላው ድራማ ነበር።
ለአዲስ አባባ የቄራ ሃላፊነት ታጋሩ ነው። ለቤተመነግሥት ጠባቂነት ተጋሩ ነው። አንባሳደሩ ሌላ ቢሆን ቢሮው በሙሉ ተጋሩ ነው። VOA እንውሰድ አማርኛ ዝግጅት ተጋሩ፤ ትግረኛው ዝግጅት ተጋሩ ነው፤ የኮርስፖንዳስ ሠራተኛው ተጋሩ ነው። ዶቼ ቬሌም የኢትዮጵያ የክርስፖንዳስ ሰራተኛው ተጋሩ ነው የነበረው።
አገር ቤትም ባሉት የመንግሥት ሚዲያዎች ሁሉ ቃለ ምልልስ አድራጊው ታጋሩ፤ ቃለ ምልለስ ተደራጊው ተጋሩ፤ ዜና አቅራቢው ተጋሩ፤ ዘጋቢው ተጋሩ፤ አሳሪው ተጋሩ፤ መርማሪው ተጋሩ፤ አቃቢ ህጉ ተጋሩ፤ ዳኛው ታገሩ ደብዳቢው ተጋሩ፤ የእስር ቤት ሃላፊዎች ሠራተኞች በሙሉ ታጋሩ ነው።
በደላ ጊዜ ሁሉ ቦታ ከተሆነ በዛ በደላ ጊዜ ለተበደለው በደል ደግሞ ተጠያቂ መሆን ግድ ይላል። ግድ የሚለው ሰው ስለፈለገ ስላልፈገ ሳይሆን ዕውነት ነው ግድ የሚያደርገው። በዬክልሉ አብሶ ጎንደር እና ወሎ እና አዲስ አባባ በታጋሩ መረብ የተጠረነፈ ነበር። አሁንም ያልተነዳው ያልፈረሰው ጉዳይ ይኸው ነው።
የግል ቤት ራሱ ነፃነት አልነበረውም። ሰው ጥላውን አያምነውም ነበር። አዬሩ ለተጋሩ መዘመር ነበረበት፤ ወፎቹ ለታገሩ ማዘመር ነበረባቸው። ወንዞቹ ለታጋሩ መቃንቀን ነበረባቸው። እስኪ የውጭ ዜጎች በ27 ዓመት ሙሉ የጻፉትን መጻህፍት ቤተ መጻህፍት ሂዱና ውዶቼ ፈትሿቸው። ቡና ማፍላት፤ አራስነት፤ ክርስትን፤ እልባሳት፤ ሃዘን ተፍስሃ ባህሉ ወጉ' ልማዴ፤ ሃይማኖቱ ሁሉም የታገሩ ነው። በቃ ኢትዮጵያ ማለት ተጋሩ ብቻ ማለት ነው።
ተጋድሎውም እኔ ስጽፍ እንደነበረው በታላቁ ትግራይ ኢትዮጵያዊነትን ጨፍልቆ በማለፍ ላይ እንደነበር ነው። የአሁን ኩርፊያም ይኸው ነው። ያልተዘረፈ ትውፊት ትሩፋት ቅርስ እና ውርስ የለም። ያልተጫለው ደግሞ አንቦጭ አረም። ጭኮው የእነሱ ነው። ኩትኩቱ የእነሱ ነው። ክትፎው የእነሱ ነው። ልብ ያላችሁ ወደ ቤተ መጸሐፍት ጎራ በሉና እዬት አንብቡት። ሳር ቅጠሉ አዬሩ ራሱ በተጋሩ የተከሰዘን ነበር።
ሌላ ሃይል ሥልጣን ቢያገኝ 27 ዓመት ዘውድ ደፍቶ የኖረው የህውሃት አባል እና ደጋፊ ሁሉ ድራሹም አይገኝም ነበር። 27 ዓመት ሙሉ ያ ሁሉ ሰቀቅን ሲያልፍ ስለምን አልጮኹም። ሌባን ተሸክሞ እዬኖሩ ባለማፈር አደባባይ ወጥቶ ንጸሃንን ሌባ ማለት ራስን የመስደብ ጉዳይ ነው። መከላከያ እንኳን ተሽሎት ከሆነ ነው እንጂ ራሳቸው በአካል አምሳላቸው ያደራጀት ስለነበር ራሳቸውን ነው በቅኔ የሰደቡት።
የሚገርመው በኩር ኮንስትራክሽን አማራን የጨፈጨፈ ሠራዊት ትግራይ ላይ መቆጣት አልተቻለውም። ህዝቡ የለበትም የሚባለው ነገር አይገባኝም እኔ። ወጣቶች እኮ የህዝብ አካል ናቸው። ወላጆች ደግሞ አላቸው። ወላጆች ሳይፈቅዱላቸው ልጆች ምንም ሊያደርጉ አይችሉም። ለዛውም ትግራይ እንደ ጎንደር ወግ አጥባቂ ነው። ስለዚህ በፈቃድ በኩል የስምምነት ሂደት የተፈጸመ ነው።
ለመሆኑ ወጣቶች የትግራይ ክልልን ሚሊሻ የማዘዝ ምን ስልጣን አላቸው? የተጋሩን ሚሊሻ አምነው የመከላከያ አባላትን አለመማንም የሁለት ዓለም ሰወች መሆናችን አሳይቶናል። ብቻ ይህ መታበይ ሆነ ጥጋብ የሚያርድ ጥበበኛ ዘመን ስለመጣ እንደ ጎርፍ የሚታይ ነው … እነሱ ይህን ሲያደርጉ ሌላውም ቀጣዩን እርምጃ ለመውሰድ የሚያግደው ያለው መስሏቸዋል። ፈጣሪም አለ ... ቁጣው የመጣ ዕለት ወዮ ነው!
"ገዱን አብይን ሌባ" ብለህ የትም የሚኖረውን ታገሩ ዋስትና ይጠበቅልኝ የሚቻል አይሆንም። ሌላውም ደም አለው ይንተከተካል ደሙ፤ ይቆጣል ደሙ። ሰሞኑን አንድ የትግራይ ወጣት አቶ አምዶም ከናሆ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። ስክነታቸውን ወድጄዋለሁኝ ወጣትም አይመስሉም። ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ብለውናል።
እስኪ የታሠሩት ምን ያህል ናቸው ሲባሉ? ሦስት። ሦስቱ ጥቂት ስለሆኑ ሥማቸውን ብሎ ጋዜጠኛው ሲጠይቅ ዘረዘሩት። ባዶ 6 ላሉት ለወልቃይት፤ ለራያ አማራዎች ግን ጉዳያቸው አይደለም አረናዎች ራሳቸው።
በሌላ በኩል ተፈናቀለ ስለሚባለውም ቢመጣ 700 ሺህ ነው ጅጅጋ ላይ በእነሱ ሲኦሎች የተፈናቀለው ለእነሱ ይህ ቁጥር ነው በህይወቴ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ እንዲህ ዓይነት ስግብግብንት አይቼ አላውቅም። ማዕቱ ጭካኔው በሌላው ላይ ይዝነብ እኛ ግን ዝንባችን እሽ አይባል … ሁልጊዜ አይጉደልብን። ሲያማራቸው ይቅር ያ ዘመናይነት የተቃጠለ ካርቦን ሆኗል። እንደማንኛውም ዜጋ እኩል በቃ … የክትነቱ አክትሟል።
· ምድር ያልቻለችው ጉድ የለም …
ነገራቸውን ሳስበው ምድር አትችላቸውም እነሱን አንድ ቀን የምትተፋቸው ይመስለኛል … መሬት እራሷ። ዕምነት የሚባል ነገር አድራሻው የት ነው ቢባል አድራሻ ቢስ ነው … እንደ ሰው ለማሰብ እንደ ገና መፈጠር ይኖርባቸዋል
… የተጋሩ ገበሬው ምን ሊያስብ እንደሚችል አላውቅም ገበሬ ገር ስለሆነ፤ የተጋሩ ገበሬ ከዚህ መሰል ይሉኝታ ቢስነት ይወጣል ብዬ አስባለሁኝ። የእነሱ አምላክ ምድሪቱን ይታደጋት እንጂ የእነሱማ እያዬነው ነው …
በትግራይ የበላይነት ተፎካካሪዎች አይደለም በህውሃት የተበደለው ተጋሩ ሁሉ የሚስማማባት መንገድ ነው። ከዚህ ተነስተን ነው መፍረድም መዳኝትም የሚኖርብን። የትግራይ የበላይነት የጨለማ - የጭካኔ - የአረመኔነት ዘመን ስለነበር በሰው ጥንካሬ ሳይሆን በእዮር ጥበብ ተገላግለናል። ዕድሜ ለዚህ ሰውኛ ዘመን ክሶናል። መካሱ ቁጭ እንዳሉ ነው ከበላያቸው ላይ የተናደው የ100 ዓመት ህልማቸው። ተመስገን!
· ማተበቢስነት።
ሌላም ነገር ይቅረብ …. ጎንደር ባመዛኙ የህክምና ፋክልቲ ስለነበር የጎንደር ልጆች ምን ትሆናላችሁ ስንባል የህክምና ዶክተር ነበር የምንለው። እኔም በኬሚስትሪ እና በባይወሎጂ ቶፕ ተማሪ የነበርኩት ያ ተጽዕኖ አሳድሮብኝ ነው እንጂ ጄኦግራፊም ሂስትሪም እኩል ችሎታ ነበረኝ። ስለሆነም በጣም ብዙ የጎንደር ልጆች ዶር ሆነዋል።
ጎጃም የተለዬ ነው በቀለም ትምህርት። እንደ ሲዊዞች ዓይነት ባህል ነው ጎጃም ያለው በትምህርት ጉዳይ። መማር ለቅኔው የጎጃም ሰው የህይወት ግቡ ነው። ሽዋም ሽዋ ነው እንደሚታወቀው በቤተስብ አመራር እና አስተዳደር አክብሮት ጨምሮ ሽዋ የተለዬ ነው ለጋብቻ እራሱ የሽዋ ሰው ትርጉምኛ ነው።
ይህ ሆኖ እያለ ሰው የጠፋ ይመሰል የጎንደር ዩንቨርስቲ ዲን ጋይንት ተወልደው ያደጉት አቶ ደሳለኝ መነጋሻ ቤተ ተጋሩ ናቸው። ሰው ጠፍቶ¡ ይህን ሁሉ ገመና ችሎ የተቀመጠ የገዱ መንፈስ የክብር አክሊል ቢደፋለት እንጂ እንደዛ በአደባባይ „ሌባ“ ሊባል ባልተገባ ነበር። ሞራሉ የለም ከቦታው መቼ ተፈጥሮ አብሶ በዚህ 27 ዓመት።
አሁን ሺ ተጋሮች በእሱ እጅ ውስጥ ናቸው በገዱ መንፈስ። እሱ ቢተወው እንኳን ይህን የሰሙ ወጣቶች ደማቸው እንደሚንተከተክ የታወቀ ነው። ተዉ እያልን እዬተቆጣን ነው እንጂ … ጥቃትን ተቀብሎ ለሽ የሚል ልጅ የአማራ እናት አትወልድም። ለዚህ ነው በማንኛውም የትጥቅ ትግል አማራ በስፋት እና በጥልቀት ለሞት የሚሰለፈው። ለዛውም ጠረኑን ለማስጠጋት አይደፈረም።
በነፃነ ት ትግሉም ጎልተው ገፍተው በጽናት ነው የሚታገሉት አማሮች። በዬጊዜው ተደራጀን በትጥቅ ትግል የሚሉት ሁሉ ግንባር ላይ አማራን አሰለፍው እነሱ ዞር ነው። በገፍ ነው አማራ የሚያልቀው ቅን ስለሆነ 50 ዓመት ሙሉ።
ያለፈውን ዓመት የወልድያን የአዲግራትን የአክሱምን የመቀሌን የኦሽቲዝም መከራ ገዱን የመሰለ ቻይ መንፈስ ታግሶ ነው ያለፈው። ስለምን የሰቲት ወጣቶች ያን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ አልወጡም?
ወልድያ እኮ ሽንት በኮዳ ተደፍቶበታል ህዝቡ። ወሎ አስተሮዬ በኤልኮፍተር የተደገፈ ጭፍጨፋ ተካሄዶበታል። የአቶ አባይ ወልዱ ትዕቢት ክልል ጥሶ በግለሰብ ቤተሰብ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የኮ/ ደመቀ ዘውዱ ጉዳይም ጦርነት የሚያስከፍት ነበር ዶር ገዱ ግን በበበዛ የሰማይ ትእግስት ነው ያሳለፉት። እኛን ቅጥል ንድድ እያደረጉ…
ራሱ አቶ አባይ ወልዱ ለሰላም ጉባኤ ተብሎ ጎንደር ሲሄዱ የጎንደር ወጣት ወጥቶ „ሌባ“ አላለም። በዘረፋ ባይጠረጠሩም። በመንፈስ ወረራ ግን ዋንኛው ናቸው። በሙሉ ህውሃቶች ጎንደር ነበሩ ባለቀ ሰዓት በኦህዴድ ጣና ኬኛ ድብን ብለው ስለቀኑ። አንዱ ያደረገውን ካላደረጉ ቁንጣን ይገለድላቸዋል። ትልቁ ችግራቸው ደግሞ ይኸው ነው። የበታችንት ስሜት መለያ ታርጋቸው ነው። ሰሞኑን ጽዮን ላይ ያዬነው ያን ድራማ ነው ...
ወደ ቀደመው ምለስት ሲሆን ያን ጊዜ ጎንደር ሰብሰብ ብለው ሲሄዱ ሞት እንደሆን አይፈሬ ነው ጎንደሬ፤ ከግንጫ አብዮት በፊት አቶ ሞላ አስገዶም ትጥቀቸውን ፈተው ሲገቡ „የፈራ ይመለስ“ ብለው 500 ወጣቶች በራሳቸው ቲሸርት አሰርተው አደባባይ ወጥተው ፈሪዎችን ሞግተዋል። የደረሱበት አያታወቅም እንዛ የመይሳው ልጆች። በኋላም ታይቷል ስንት ታስሮ የኖሩ ብህራዊ የዕውነት ማህደሮችን ሉላዊ ጉዳዮችን አደባባይ ወጥቶ በደሙ ይህን ቀን አዋላጅ የሆነው።
ቢፈልግ ጎንደር ያደርገው ነበር። መሳሪያ ያደገበት ነው፤ ድፍረትም ደሙ ነው። ግን እነዛን የዘመን ጥቅርሻዎች ማህበረ ደራጎን ተቀብሎ አስተናግዷል። አቅል አለ አማራ ቤት። አደብ ተፈጥሮው ነው … እግዚአብሄር ዘፈን ሲያመረው አልፈጠረውም እና …
እንዲያውም ትህትናው ልክ ገደቡን ጥሶ ስላለፈ የዶር ገዱ አንድርጋቸው ነው እኛ ማዕቱን እምናወርድባቸው። ህውሃት ማተበ ቢስ ስለሆነ ነው እንጂ ብአዴን እኮ በተጋሩ ነበር ሲመራ የኖረው 27 ዓመት ሙሉ። እነ ሳጅን አዲሱ እነሳጅን አለምነህ ወዘተ ግን ህውሃት የሚባል ድርጅት እና ዶክተሬኑ ማተብ የሚባል አልሠራለትም። ተፈጥሮውም አይፍቅድለትም። ጭላጭ የሆነ መንፈስ ነው ያለው በሰውኛ ሲተረጎም … አዙሮ ማዬት የለም። ሁልጊዜ ይሞላልን …
ሌላም ከጣና የተሰባው ኤሌትሪክ እኮ የአማራ ገበሬ ሌት እና ቀን ዘብ ሆኖ ቁሞ እያበላ እሱ ጨላማ ውስጥ ነው ያለው። ካሳ ሳይጠቅ ለተፈጥሮ ሃብቱ፤ ለዛውም እንቦጭን የመሰለ አረም ገጸ በረከት ተሰጥቶት፤ ብቻ ያ የኤሌትሪክ መስመር አንድ ቀን ቀጥ ቢል ቀጥ ነው። አንድ ገበሬ ይበቃዋል ይህን ለማድረግ። ጥጋቡም ይተነፍሳል። የወሎም የጎንደርም መስመር ቢዘጋም እንዲሁ … አማራ ታጋሩን እድሜ ልኩን ተሸክሞ ነው የኖረው በመቻል … እዬተገረፈ እየተሰደበ እዬተገፈተረ …
አንገት የሚባል ያልሰራላቸው ወጣቶች ነው የተፈጠሩት ትግራይ ላይ። ሌብነትን ወረራን መታበይን ጭካኔ አረመኔነት እንደ ጀብዱ እንደ ጀግንነት የሚዩ ወጣቶች። ይህ ነገን አያስቀጥልም እንዲያውም ማግስት ከመምጣቱ በፊት ያቃጥለዋል።
ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግሥት ባይችለው እንኳን ትልቁ የኢትዮጵያን መከራ የጃርቱ ሥርዓት ስለተወገደ ከእንግዲህ በመሰረታዊ የለውጥ አምጪ ምክንያቶች ላይ በብርታት ይሰራበታል። የዚህ ለውጥ እንብርት የወልቃይት የጠገዴ ጉዳይ ነው። አንተኛም። ፈጽሞ።
ድርድርም የለም በርስት እና በትዳር።
የማያቆም ነው ተጋድሎው። ለነገ ለሚፈጠሩት የአማራ ልጆች የመኖር የዜግነት ዋስትናቸውን የሚያስጠብቅ ሥራዓት ማስበጀት ግዴታችን ነው። አሁን በዬትኛውም ዩንቨርስቲ እዬታደኑ በአዲስ ስልት በባህር ውስጥ ሳይቀር እዬተጣሉ መሆኑን፤ ግፍ በበዛ ሁኔታ እዬተፈጸመባቸው ስለመሆኑ እዬታዬ ነው፤ ነገም ቢብስ እንጂ አይሻልም የአማራን ተጋድሎ ተጠናክሮ እና ደርጅቶ ካለቀጠለ። የዶር ገዱ አንዳርጋቸውም ክብር ሊዘለቅ የሚችለው በዚህ ተጋድሎ ብቻ ነው።
ይህን አለርም ደግሞ ለውጭ መንግሥታት ትጥቃችን ሳንፈታ እናስተውስው አለን። የአማራ ልጅ አባቶቹ ባበጇት አገር ባይታወርነት በእኛ ዘመን ማቆም ይኖርበታል። የአማራ ርስቶች ወደ ቦታቸው መመለስ ይኖርባቸዋል። መተከልን ጨምሮ።
„አይምጣብን?¡“ እንዴት ተቀለደ?! እንዴትስ ተደፈርን?! እንደ ዜጋ መሆን ሲችል ብቻ ነው እነሱም መኖሪያችን ማለት የሚችሉት እንጂ ባለርስቶችን መጤ ቃሉ እራሱ ሰማይ ተቆርሶ ይወድቃል።
የአባ ፊታውራሪ መለሰ ሃይሉን ዘመን ጠገብ ተጋደሎ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ሳይመለስ የሚያንቀላፋ የአማራ ልጅ አይኖርም። የአማራ ልጅ ትውልድ የማይተካቸውን የጎንደሬ በጋሻው ጸሐፊን የአባ ገሪማን ታፈርን መጸሐፍ ያንብብ።
ይልቅ የጤና ጥበቃ ሚኒሰተሩ ዶር አሜን አማን ውክልና የተገባ ስላልሆነ ይህ የሚስተካከልበት ሁኔታ ይፈለግ ብአዴን መቼም ገና አዴፓ አለመሆኑን እራሱም ያውቀዋል። እነሱ እንደሆን እናመሰግናቸው ርግማን ነውና ...
ዶር አሚን አማን ቀስ ያሉ የተረጋጉ ወጣት መሆናቸውን ባውቅም ይሉኝታ ለሌለው ማህበረሰብ ግን ይህን መሰል እርምጃ መውሰድ ግድ ይሆናል። የጎንደር ዩንቨርስቲም እንዲሁ … ወደ ባዕተ መንፈሱ ይመለስ። የትግራይ ወጣቶች ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ቢያገኙ አንጠልጥለው ነው የሚሰቅሏቸው። ስለዚህ መጠንቀቅም አለባቸው ለህይወታቸው።
· ክብር ከሰፈጣሪ እንጂ ከሰው አይደለም።
ሌላው ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሚመለከት እግዚአብሄር ያከበረውን ሰው የፈለገ ቢያደርገው ከጫፉ አይደርስም። የሳቸው ከእግዚአብሄር የሆነ ስለሆነ ጥበቡ ሊያስቀጥል የፈለገበት አመክንዮ እንዳይቆራረጥ የፈለገበት ምክንያት ሞቆ በመቀዝቀዝ፤ ቀዝቅዞ በመሞቅ እንዳይቆራረጥ የፈለገበት የራሱ የአማኑኤል ጥብብ ስላለው እንጂ ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ይሆናሉ ብሎ ያሰበ አንድም ነፍስ አልነበረም። ቢሆኑም ዶር ለማ መገርሳን ነበር የሁሉ ዕሳቤ የነበረው።
ነገር ግን ሁለቱም መንፈስ ቅዱስ የቀረባቸው ስለሆነ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ተመርተው የፈጹትን ፈጸሙ። ስለዚህ በመከራ ውስጥ ለበቀሉ ቅዱሳን ወንጌላውያን እንደ ቅዱሳን ቀደምት ሐዋርያ አባቶቻችን ተወግረው ተቃጥለው እንደ ተሰወቱ ፈጣሪም አንደ ገጠመው ሃሞታዊ ዘመን ዛሬም ሰቲት ላይ ያ ቢገጥም ከቶውንም ለበረከት መሆኑን ስለምናውቀው ከመጤፍ አልቆጠርነውም።
ብቻ ለእነሱ ለተጋሩ ነፍሶች አላግባብ ተንጠራርተው ፈጣሪን ለመውጋት ማስብ ሰበሰብ ሆኖ ንጹሃን የተጋሩ ወገኖቼ ቅጣት እንዳይመጣባቸው ያስፈረኛል፤ የመሬት መራድ፤ ድርቅ ተባይ ወዘተ … አብሶ ለህፃናት እና ለነፍሰ ጡር ሴቶች።
· ሲከወን፤
ይሉኝታ ላልፈጠረለት ነፍስ ገነትም ሲዖሉ ስለሆነ ብዙም መጨነቅ፤ ብዙም መጠበብ አይገባም። ብዙ ማግነንም ብዙም ማጣጣልም አይገባም። ምክንያቱም ዘመኑ ራሱ በንፈስ በጅራፍ እዬገረፋቸው ስለሆነ ግፈኞችን በገናቸው የሶቆቃ ቤተ ሙከራ አድራጊዎችን።
ቁመው እያዩ እዬሰሙ ነው ዓለም እራሱ በድንቁ ተግባር ከጫፍ እስከቨጫፍ እዬተደመመበት ነው ያለው ይህን ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ዘመን።
ዓለም እኮ የተባረከው የኢትዮጵያ ዘመን እያለው ነው በ27 ዓመት ወስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እስር ቤቶች ነጻ ሲሆኑ በተቀደሰው በአብይ መንግሥት ታዬ …
"እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድን ሰው ናቸው ብዬ ነው እማምነው" ብለውናል ሊቀ ሊቃውነቱ ዶር/ ሻ ዳዊት ባለ ስድስት ክንፉ አቡነ ተክላሃይማኖትም ሰው ሆነው ነው የተፈጠሩት፤ እናታችን ቅደስት ድንግል ማርያምም ሰው ሆና ነው የተፈጠረችው፤ እናታችን ክርስቶስ ሰምራም ሰው ሆና የተፈጠረቸው፤ አቡዬም እንዲሁ ሰው ሆነው ነው የተፈጠሩት፤ 9ጠኙ ቅዱሳንም ሰው ሆነው የተፈጠሩት፤ አብርሃም ሙሥላሴም ሰው ሆኖ ነው የተፈጠረው፤ በ እስልምናም ነብዬዩ መሃመድ ሰው ሆነው ነው የተፈጠሩት።
ግን ተባርኮ መፈጠረም የሰው ሥራ አይደለም የፈጣሪ ነው። በዬዕለቱ የሚሰሙት ሰብዕዊ ተግባራት የተጎዳውን ህሊናችን እንደገና አይዟችሁ እያለን ነው። ሁሉም የፖለቲካ ሊሂቅ አሜሪካ ነበር አንድ ቀን ግን ቅዱሱን አባታችን አቡነ መርቀሪዮስን ሄዶ የጠዬቀ፤ ችግሩን እንደ አጀንዳ ያዬ የለም። አብዩ ግን አሜን!
"ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው“
መዝሙር ፲፮ ቁጥር ፯
መሸቢያ ጊዜ ክበረቶቼ - ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ