ምንድነው የተፈለገው? ዙፋኑ እስከ እልፍኝ አሰከልካዩ ከቢኦኤ አማርኛው ዝግጅት ጋር ጥድፊያ በግራ ቀኝ የያዘው።
እንኳንም
ወደ ቀንበጥ ብሎ በሰላም መጡልኝ።
ምንድን ይሆን የተፈለገው?
ሦስት ጣማራ ቅዬጣ …
ዝንጣይባል ፍጠጣ
ወይንም ፍለጣ
ወይንም ሽምጠጣ አይታወቅም …?
„ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፣
ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ
ከጌታ ምህረትን
እመክራለሁ። የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ምልዕክት
ወደ ቆርንቶስ ምዕራፍ ፯ ቁጥር
፮“
ከሥርጉተ ሥላሴ
Sergute Selassie
29.05.2019
ከ እመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
· መነሻዬ።
ልንወርድ ከነበረበት አዘቅት የማገገም ሁኔታ አለ - ጠ/ሚ አብይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት የአንድ ለአንድ ቃለመጠይቅ | Ethiopia
Published on May 28,
2019
የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ_ ከአቶ ንጉሱ ጥላሁን እና ከሆኑት አቶ ነቢያት ጌታቸው ጋር አጭር ቆይታ
May 27, 2019
“የለውጡ አካሄድ ወደ ትክክለኛው መድረሻችን ሊያደርሰን የሚችል ነው።” ስዩም ተሾመ – SBS
Amharic
May 27, 2019
በግርምታ ሰሞኑን ታደምኩበት። ግን እንዴት ናችሁ
የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ?
ሦስት ጣምራነት ብቻ ሳይሆን አራተኛውም አለ ዲሲ
ላይ የተጠመደ አዲስ ትዕይንት። ተከድኖ ለጊዜው ይቀመጥ። ሌላ ጊዜ ፈታ በል ይባላል … ወፊቱን ማመሳጠር ክህሎቱ ላላችሁ ግን የገጥ
ጉዳይ ነው፤ ሜዳ ላይ የተሰጣ እንደማለት።
ጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን አመቱን
ድገሙን ብለው አሜሪካ ላይ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አዬሁት።
ክብረቶቼ አዬሁት ነው ያልኩት አዳመጥኩት አይደለም። ኧረ ምን በወጣኝ ማድመጥ? የድምጽ አልባዎች ኢትዮጰውያን እናቶች
የተጣለባቸው ዕዳ ናቸው አብሶ ለአማራ እናት ድርብ ድቅድቅ አራጣ ናቸው?
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ሌላው ልማታዊ ጦማሪ
አቶ ስዮም ተሾመ ደግሞ ብርቅ ሆኖባቸው ይጣደፋሉ። የሚዲያ ፍቅር
ይህን ያህል ያለባቸው ነበሩ ብዬ አላስብም ነበር … አቴንሽ ሲከር ሆነው ነው እማያቸው … እሳቸው እንዳሻቸው በሚያዞሩት ሚዲያ
ራሳቸው ደግሞ ተጠያቂ ሆነው ነበር። የጠያቂው ምስል አይታይም ነበር … እስቲ ይህን ታዘቡት … ያው እያሳበዳቸው ያለው ነገረ ሚስጢር
አለ …
ጦማሪ ስዩም ተሾመ ከአንድ አፍታ ሚዲያ ጋር ያደረገው አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ!! | Ethiopia
ተዝች ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ልጅ እያለን አብሮ አደጌ ዳጊ አንዲት ልጅ በፍቅር
እብድ ብላ እሱ ደግሞ ኮራ በል ብሎ እሷ እኔን ሽምግልና ላከችኝ። „ልታነቅ ነው ብለሽ ንገሪው ብላ“ ታዲያንላችሁ ስነገረው እጄን
ያዝ አደረገና በይ አብረን ሱቅ እንሂድ ይለኛል። ስለምን ስለው? ገመድ ገዝቼ ልስጥሽና አድርሽልኝ ብሎኝ።
ይህን ቪዲዮ እኔ ሳዬው ዳጊ ነበር ትዝ ያለኝ … ገመድ ያሰኛቸው ይመስላል አዲሱ የ ኦዴፓ
ልማታዊ ካድሬ፤ አገርም ምድርም አልበቃቸው ብሏለኝ። ከቶ ተዚህ ተጭምቷስ አይገኝም ከጎረቤት አገር ጎራ ብዬ ገዝቼ ገመድ መሳይ
ልላክላቸውን ብያለሁኝ በወቅቱ።
ለነገሩ ራሳቸውን እንዳጠለጠሉ ነው የምቆጥረው። አቁነጠነጣቸው፤ አክለፈለፋቸው አዲሱ ስውር
የደህነንት ባለሙያነታቸው አደብ ነሳቸው። ይልቅ አደብ ተዚህ ከእመ ጭምቷ ደርቤ ልሰደድላቸው ይሆን?
የሆነው ሆኖ ከሰከነው ራዲዮ ዝግጅት ሲቤኤስ
ጋር ቃለ ምልልስ አደርገዋል አቶ ስዮም ተሾመ። ለእኔ ከአውራንባ ታይምስ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ለይቼ አላያቸውም። ይገርሙኛል
ለሳቸው ሽፋን ሰጪዎች፤ ሰብዕና እንዲህ ካለጥንቃቄ ይገነባል ነገ ደግሞ ሲጨነግፍ አብሮ ድንኳን መቀመጥ …
የሚገርመው የዚህ መሰናዶ ባለሟልም ናቸው ጃዋርውያኑ
አቶ ንጉሹ ጥላሁን ሊንክ ናቸው ብዬ በቀደመ ጊዜ ጽፌ ነበር
… እሳቸው ናቸው ያሰናዱላቸው፤ ለራት ግብዣው ትኬቱን ገዝተው ሲሰጡ ይኽም ደግሞ አለበት። እሳቸውን ለማወቀው መጣር መታከት ነው … ድንብልብል ናቸው። የራሳቸውም
ብቻ ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድ አገር ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የአንድ ለአንድ ቃለ ምልልስ ከዚኸው ቢኦኤ ጋር አድረገዋል።
ምን አደረገ ቢኦኤ እንዲህ ውጥር ያደረጉት። ሌላም ሰው ያላስተዋለው ቀደም ብዬ ያነሳሁት በመዳፍ ኃይሉን ለመቆጣጠር ዲሲ ላይ የተጣደ
አህትዮሽም አለ … የቤተ መንግሥት ባለሟል። ግን አስተውላችሁታልን
የኔዎቹ?!ዘመቻ ምን እንበለው ይሆን? ዘመቻ ሥምየለሽ ይባል ይሆን?
ግን ሻታው ምንድን ነው? ምንድን ነው የሚፈለገው?
የዛሬ ዓመት ሐምሌ ላይ አሜሪካ አገር ያን የመሰለ የገዘፈ አቃባበል፤ ምሰጣ፤ ተደሞ ዕድምታ ጥድፊያ ነበረበት። በምልሰት ስቃኘው።
ዘንድሮ ቢታስብ ሩቡን ያህል ደጋፊ አይገኝም ነበር። ጥድፊያውን ሳስበው እንዲሁ በጥድፊያ ኢትዮጵያን ኦሮማይዜሽን ለማድረግ ፍንጭ ከመውጣቱ
በፊት አቅም ማጠራቀም ይገባ ስለነበር ነው። አሁን ላይ በጥልቀት ሳስበው ሚስጢሩ ያነ ነው።
ነፍሳቸውን ስተው ነበር የተጣደፉት አሜሪካ ላይ በአዲስ ሰብዕን ለመቀወጥ
… ያን ጊዜ በቅንነት፤ በአውንታዊነት ነበር ያዬሁት … አሁን ሳሰላው ግን እምል ነው።
ከዚህ ስነሳ አሁን ያ የኢትዮጵውያን ቀን በስሜን
አሜሪካ ተሃድሶን ለማስከበር ዲሲ ላይ የሚሰራ ስልስልና ልሙጥ የፖለቲካ ቅብጠት ነው ብዬ አሰባለሁኝ። „የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ“ እንዲሉ …
አሁን ስለሰብ ግድ የሚላቸው ከእኛ ያልተፈጠሩ ነፍሶች
የአብይወለማ ሌጋሲን በጥንቃቄ እዬተከታተሉት ስለሆነ ያን ግርዶሽ ለምዕራባውያን መስራት ታስቦ ነው።
ሌላ ሥራ ጠፋ እያንዳንዱ ቀን ዜና አብይወለማ ብቻ ሆነ …
መቼ ወንበሩ እንደሚሰራበት አላውቅም። አልገባኝ ያለው
አገር መመራት የአክቲቢስት ሥራ ነውን? የካድሬነት ሥራ ነው? የተጋዳላይ ሥራ ነውን? የኪኖ ፕሮጀክት ነው? የልማታዊ ጋዜጠኛ ሥራ ነውን?
አልገብቶም።
አሁን እኮ በኢትዮጵያ የሚዲያ መስክ ወለል ሌላ ነፍስ ያለው፤ ህይወት ያለው የማይሰለች ነገር ማዬት እኮ ራቀ … 24 ሰዓት አጀንዳ አብይወለማ
ብቻ። ስለችት ግልምት ነው ያለኝ። እውነት ቢሆን ጥገት ይሆን ነበር። በድርቅ
ምት ግን ናፍቆት ቃር ነው።
ራሱ የሥነ - ጥበብ ሰዎች ሌሎች በተለያዬ ሙያ ያሉ
የተጽዕኖ ፈጣሪዎች ነፍሶች እንዲከስሙም ነው ጥረቱ … ፉክክር ይዘዋል። ይቀኑበት ነበር ማለት
ይሆን? ብቻ ይመሰለኛል።
አሁን የአንድ ሰው መንፈስን የሚያራግቡ ዓይነ ርግቦች ብቻ እንዲኮፈሱ ነው የሚፈለገው … ሁለመናውን እርሰተ
ጉልት ማድረግ … መታመም።
በዚህ የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ጥሪት እና ትውፊት
እዬተመነጠረ፤ እዬነደደም አይሆኑ እዬሆነ እንደ አማራ እዬተሳደደ ሲሆን… በሌላ በኩል በኢትዮጵያዊነት ሥም አለሁኝ የሚለው
„የኦነግ ወራሽን“ መንፈስ፤ እኔ አይደለም ያለኩት አሁን ቆንሲላ ሹምነት አሜሪካ ላይ ያገኙት ዶር ብርሃነመስቀል አበበ ነው ያሉት … አሁን ላይ ሳስበው ልክ ናቸው መጀመሪያ ግን ጠ/ሚር አብይም አያድርግባቸው፤ እኛም አያድርግብን
ብዬ ሞግቼ ነበር። ይህ መከረኛ ቅንነት እና አዎንታዊነት እኮ አሰጠቃኝ።
ብቻ ስለመኖሩ አቅሙ ያን የቅድንብ ጸጉር መንፈስ
ያዘለው አብይወለማ ሌጋሲ በቀጥታ ኢትዮጵያን ከውስጣቸው የተቀበለ ድርጅት ወይንም ሰብእና ያለውን ነፍስ ለማፍለስ እዬተጣደፉ ነው
… በግራ በቀኝ።
ግርም እያለኝ ሌላም ሰሞንኛ ወግ ቢጤም አዳምጥኩኝ
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጉልበቴ
ገበሬ ነው ሲሉ ተደምጠዋል ተሰሞናቱ። ከትከት ብዬ ነበር የሳቅኩት።
ስለምን ብትሉ እኔ „አብይ ሆይ“ በሚለው አቤቱታዬ የኢትዮጵያ ገበሬ 27 ዓመት ሙሉ ከፖለቲካ ማዕቀፍ ተለይቶ መገኘቱን አበክሬ
ጽፌ ነበር። ያን ጊዜ ጉዳያቸውም፤ አጀንዳቸውም አለነበረም። ስለምን አሁን ብትሉ …
አንደኛው የምርጫ ሁኔታ መልክ ከተሳካ ኮሮጆ ለቀማ ነው፤ ያው ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ የተወረሰ መንገድ ነው። ውርሰ ሄሮድስ መለስ ከተሜን አያምኑትም ነበር።
ልዩነቱ ቋንቋው አገላለጡ ነው የሚለዬው ባጣ ቆዬኝ ያ መከረኛ ገበሬ …
እራሱ እሳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከገበሬ ቤተሰብ
መፈጠራቸው እጅግ የረካሁበት ጉዳይ ነበር። ነገር ግን እሳቸው በውስጡ
የሉበትም። በገበሬ ቤተሰብነት ህይወት። አሁን አሁን አባታቸውን ያራቁበት መንገድ ራሱም በዚህ ተደሞ ተከድኖ ይደመም።
… እኒያ የሚወዷቸው እኛም እሳቸው በነገሩን ታሪክ
ተመስጠን ከውስጣችን እንደ ጽላት ያስቀመጥናቸው እናታቸውን ክብርትና ቅድስትን እንኳን ረስተዋቸዋል።
መርሳታቸው በእዮር አደባባይ ዕንባን እንዲፈስ አስደርጓል ብዬ አስባለሁኝ። እኔ በአምላኬም አምናለሁኝ ተስፈኛም ነኝ።
ጸረ አማራ መንገዳቸው በጉልህ ጎልብቶ ልዩ ስኳድ እሰከማቋቃም አድርሷቸዋል …
ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ማስረሻ ሰጤ እና ዘመነ ካሴ ሊታሰሩ ተወስኖባቸዋል በሚል በሰሞናቱ የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ
May 28, 2019
በዬቀዬው አማራን ማሳደድ ዋንኛ ፕሮጀክታቸው ነው። ግን የእምዬ ማህጸን እንዴት ይታዘባቸው …? መሰል ኢሰባዕዊ ድርጊት ከዛ ሲከወን እፎይ
ይላሉ … ስለምን ፉክክሩ ከአማራ ፖለቲካ ጋር ነውና። አሁን ጥፋትን አደራጅቶች አቻነት ምኑ ይመስጣል? ረቂቅ ነው ጉዟቸው ግን
አሉታዊ …
ሌላው ሁለተኛው ወደ ገበሬው መንፈስ ምን ምልሰት
አሳኛቸው ስለምን ለሚለው የዴያስፖራ ፈንድ እንደተፈለገ አልሆነም፤ የአገር ባለሃብት
አዲስ አባባን ለማዘመን በሚመለከተም ብዙም የአገር ውስጥ ባለሃብት እንደተጠበቀው አልሆነም ብለውናል … አዬ የሳቸው ነገር። ይህን
መቼም ልበ ብርሃን ስለሆኑ አያጡትም ብዬ አስባለሁኝ።
እሳቸው ስለፍቅረ ንዋዩ ነው የሚያስቡት ነፍሳችን፤ መንፈሳችን ከሳቸው ሩኽ
ምን ያህል ከእኛ እንደራቀ አላወቁትም። መለኪያው አብስትራክት ነው። ስለምን አለም ሞራልን፤ ሥነ ልቦናን፤ አስተሳሰብን
የሚያነብ መሳሪያ እለሰራችም እንደ ጤናው ጉዳይ እንደ ኤክስሬይ እና ራዲዮሎጂ ….
እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ያን ያህል ያልምኳቸው፤ ሌት እና ቀን የጸለይኩላቸውን፤ ሚዛን ሊወጣለት በማይችለው
ሁኔታ የሳሳሁላቸው ባተሌዋ ብቸኛዋ አንስት እህታቸው እንኳን እሳቸውን ከሌሎች የሴራ ፖለቲከኞች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች
ዛሬ ላይ ለይቼ ላያቸው አልችልም። ፈጽሞ። አዘናጌ አደናግሬ ናቸው …
እሳቸው ጠ/ሚር ቦታ የተሰጣቸውም በዴሞግራፊ ፍልስፍና
አዝለኝ ቅዬሳውን እስኪበቃን አይተናዋል። ይህን ራሱን እያፈረሰ
ለሚገኘው ለአማራ ሊሂቃን ያሸከሙት፤ በተጨማሪም ጠፍጥፈው እንደ አዲስ ለሰሩት ግርባው ብአዴን።
እኔን በግሌ ልክ ለሌሎች መስክሬ ውሃ የበላው ቅል
እንዳደረጉኝ ሁሉ እስኪበቃኝ ድረስ ደብደብውኛል// ከትክተውኛልም።
… እሳቸውን ብቻ አይደለም ጓዳቸውን የመከላከያ ሚ/ሩ አቶ ለማ መገርሳን አክሎ ህሊናዬ ፍቀት ገጥሞታል በእነሱ ምክንያት። የባቢሎን ግንብ አናፂውን አቶ በቀለ ገርባንም ጨምሮ። ያደክማል የኦሮሞ
ሊሂቃን ፖለቲካ …
እዬፈረስ ለሚስቀው፤ መፍረሱ ለሚያፍነከንከው ብአዴን ግን ማዳበሪያው ነው። ለዝለኙ የኦሮሞ ፖለቲካ … ያሸብሽብ እንደለመደበት ከአመድ ትርፍ
አገኛለሁ ብሎ ከበዬነ ዘንዳ… ዝብንል … ዝንብል … ዝንብል …
ኢትዮጵያን ለአዲስ የሙከራ ጣቢያ እንዳሻቸው እያደረጉት
ነው ሁለቱ ጠ/ሚራት ዶክተር ለማ መገርሳ እና ዶክተር አብይ አህመድም። ይበቃት ነበር መከራዋ
እምዬ እናት አላዛሯ ኢትዮጵያ።
ይበቃት ነበር ፍደዋ። ይበቃት ነበር ዕንባዋ።
ይበቃት ነበር ሰቆቃዋ። ተረማመዱባት። እውነት መሆን ተሰናቸው። እውነትም
አይደሉም።
እህ!!!! .. ዴሞግራፊ? የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞግራፊ
ፍልስፍናን በዝምታ ነው እያዬው ያለው። ስለአልገባው። 100ሚሊዮን ህዝብ አደባባይ መውጣት ነበረበት። በዝምታ በዬቀዬው በበቃኝ መትመም ነበረበት በጸጥታና በርጋታ። በቃኝ ብሎ!
ይህ የዴሞግራፊ ፍልስፍና እኔ ለማውቃቸው ወተቶች
የኦሮሞ ህዝብንም አይወክልም። ወልገዳው የአብይወለማንጉሱ ጉዟቸው ሆነ ንድፋቸው። አርሲን ጢቾን አውራጃ አሳምሬ አውቀዋለሁኝ። እንዴት
እንደሚናፍቀኝ ፈጣሪዬ ብቻ ነው የሚያውቀው …
ናዚዝም አውሮፓን አይደለም አለምን እንዴት እንደናጠ
ይታወቃል። ይህ የዴሞግራፊ ክልፍልፍ አጥፊ ፍልስፋና ምልክት አፍሪካንም ለስቃይ፤ ለሰቆቃ የሚዳርግ፤ ፓን አፍሪካን የሚያፈረስ ነው።
ግን ብዙ ሰው ከልቡ አላሰበውም። አፍሪካም ዎህ ብላ
እንቅልፏን እዬለሸለሸቸው ነው … ዕዳው ዓለምን ያካታል። አብሶ ስደትን እንደጦር የሚፈራው የአውሮፓ ህብረትም አልተረዳውም … ሚሊዮኖች
ኢትዮጵውያን ብቻ ሳይሆን በቃኝን የማያውቀው የኦሮሞ ፖለቲካ ለአፍሪካም አንጡራ ጠንቅ ነው። መርዝ ነው ፍልስፍናው።
ዴሞግራፊ የሰውን ሥነ - ልቦና ሰብዕና ሰርጀሪ
የሚያደርግ ነው። ከፈጣሪ/ ከአላህም የተጣለ። ሰውን በተፈጠረው ሰብዕና ራሱን አጥቶ ቀፎ የሚያደርግ ነው።
የጭንቅላት ካንሰር ነው።
ይህን በአደባባይ እያወጁ ነው በኢትዮጵውያን ትክሻ
ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ቀጥሎ ለኦነግ ወራሽነታቸው ጽላት መሆንን የሚሹት።
ደግሜ ደጋግሜ መናገር አምፈልገው ቢያንስ ለቀሪ ጊዜያቸው ህሊናቸው እዬባተተ ከሚኖር እውነት ለመሆን ይጣሩ … ጠ/ሚር አብይ አህመድ። መለበጥ ለሰባራ
ማድጋ እንጂ ለሰው አልተፈጠረም። የሰው ልጅ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የመፈጠረው።
ለበጣ፤ ፌክ፤ ማስመሰል፤ ማማለል የመሪነትን ሰብዕናን
ዝቅጠት ይልካዋል። ይልቅ ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሚኒሶታ ቢሄዱ አይሻላቸውም ነበርን ከዲሲ ያ ይቀርባቸዋል?
የአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አንባሳደር ኦዴፓ፤ ሌላም
ሁለት ቆንሲላ ኦህዴድ፤ በአማራ ትክሻ ኦሮማይዜሽን ለማስፋፋት የተጫኑበት መርግ ለአማራ ህዝብ ቢኖሩ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው…
የጭቃ እሾኽ።
አሁን ሌላም አብቅለዋል ዲሲ ላይ አንድአፍታ ሚዲያ
ላይ እንዳበቀሉት ማለት ነው። የሴራው ሊኳንዳ ቁርጥ በቁርጥ አመሳጥሮልን። በጥዋቱ ስለገባን ግን ሁሉንም በሚዛን ማዬት ግድ ይላል
… ምንግዜም ከድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ድምጽ ጎን ናት ሥርጉተ ሥላሴ። በዚህ ድርድር የለም።
ብቻ እንዳሰቡት ትናንትን አፈረሱት … በርብርብ።
ፍቅርን ነጣቂ ለእኔ ሳጥናኤል ነው … ያ ሁሉ የፍቅር ሞገድ የዶግ አመድ አደረጉት። ያ የፍቅር ሞገድ በራሱ አይደለም ኢትዮጵያን
አፍሪካን እንደገና ያታምራት ነበር … ነገር ግን ፍቅር ባልበቀለበት ድርቀት የለመደበት ነው።
በድምጽ።
ምንድነው የተፈለገው? ዙፋኑ እስከ እልፍኝ አሰከልካዩ ከቢኦኤ አማርኛው ዝግጅት ጋር ጥድፊያ በግራ ቀኝ የያዘው።
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤
ፍቅርም ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል።
ጅልነት አንድ ጊዜ ብቻ ነው!
የጅልነት ቢከፋኝ ብመለስ ማት አይቻልም!
የኔዎቹ ብርቱዎቹ እንበርታ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ