የፀጋዬ ራዲዮ የዕለቱ መሰናዶ ይህን ይመስል ነበር። 26.05.2022

·       የፀጋዬ ራዲዮ ችግር ገጥሞት ባጅቷል።

 የመኖሪያ ቤቴ ስልክ እዬከፈልኩበት ከዘጋሁትም መንፈቅ አለፈው።

መኖሪያ ቤቴን በጫና ለማስለቀቅ ከፍተኛ ዘመቻም አለ። ሥርጉትሻ ጠበቃ ይዛ መሞገት ትችላለች። ጠብ ሲኖር ዞር ነው የእሷ ተፈጥሮ። የጸጋዬ ራዲዮ መረበሽ የአፍሪካ መሪወች፤ የአርቲስት ቴወድሮስ ልቅና፤ የዬኔታ ጎዳና ያእቆብ እና የዲያቆን አባይነህ ካሴ ጥምር ስለ ኢትዮዽያ ያላቸው ጥልቅነት መግቢያ ስላደረግኩት ኦነግ ሁሉ ነገር ስለሚረብሸው ብዬ ተውኩት። ረብሻዉ ለሁለት ወር ጋፕ ብሉ ቀጠለ።

ያለፈው ፕሮግራም 12.05.2022 ሙሉው ነበር ቅስሙ የተሰበረው። እኔ ከቤት ሆኜ የፕሮግራሙ ኃላፊና ቴክከሩ ተከታተልነው። ህውከቱ የሚጠገን አልነበረም። ኢትዮጵያን የማፍረስ ያህል ነበር።

ዛሬ ፕሮግራም ነበረኝ። ልክ ረብሻው ተጀመረ ከዛ ቀጠለ። እንደ እኔ ቲሙ ይከታተለው ስለ ነበር 15.44 ደቂቃ ቀጣዩ ዝግጅት ለ5 ደቂቃ 15.49 -16.00  ቀጠለ ከ 16.00 እስከ 16.18 የተቋረጠው ሙሉው ዝግጅት ቀጠለ።

በሌላ ዝግጅት እንዲህ የለም። ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማው እንዲህ ዝልቅ ነው። ዘመኑ ያልገባውፖለቲከኛ «ተረኝነት» እያለ ልባችሁን ያወልቀዋል። መከራው ጥልቅ ነው። ለመከራው የሚመጥን ፖለቲከኛ የላትም ኢትዮዽያ እኔ የጸጋዬ ራዲዮ ቢዘጋ ጉዳዬ አይደለም። ከመጠን በላይ ሠርቻለሁ። ደክሜለሁ። አመሰግናለሁ ተብዬ አላውቅም። ደክሞኛልም። ብዙ ጊዜ አይሆኑ ሆኜ እማስገቸው ስኬቶች ሌሎች ሲወዳደሱበት ቁጭ ብዬ አያለሁኝ።

ሙሉ ዝግጅቱ እሰከ ኤዲቲንጉ 6 ሰዓት ይፈጅብኛል። በጥራት ነው የሚሰራው። እንደ ሰው ግድፈት ሊኖር ይችላል ቢባልም 15 አመት ሙሉ ልክ እንደ አራስ ልጅ ተጠንቅቄ የምሰራው ከ23 አመት በላይ የሠራሁበት ዘርፍም ነው ራዲዮ ጆርናሊዝም። 

 አዘጋጅ እና አቅራቢ
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።