ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የፖለቲካ እስረኛ እንዳይኖር ጽኑ ምኞቴ ነው። ሳልሞት ይህን ባይ፤ እረፍቴ ሰላምን ሰንቆ በሆነ ነበር።
#ኑሩልን። አሜን።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
#አይዟችሁ! እንደሚናፍቃችሁ አውቃለሁኝ እኔም ካቴናውን አውቀዋለሁና፤
#መጽናናትም እንደሚናፍቃችሁ አውቃለሁኝ በዘወትር የፈተና ቡፌ አስተናግጃለሁና፤
ጠሐዮዋ #ብርቅ ልትሆንባችሁ ትችላለች፤ የቁም እስረኝነቱንም የመኖሬ መልክ ነውና፤
እናትን #እቅፍ አድርጎ መሳም፤ ውስጥን ገልጦ ማሳየት ትዝ ሊላችሁ ይችላል፤ መከራውን አውቀዋለሁና፤
#ወገኖቼ ሆይ!
ጽናታችሁ፤ ብርታታችሁ፤ ጥንካሬያችሁ ይገርመኛል።
በተለይ በዘመነ ህወሃትም እስረኛ እንደ ነበሩት እንደ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፤
እንደ አባት ጸሐፊ ታዲዮስ ታንቱ ዓይነት አሳር የማያልፈው ግን በተፈጠረበት
ልክ ለመቆም፤ ለመዝለቅ የቆረጠ ሰብዕና ይመስጠኛል። እራስን ጎድቶ መኖር
ብዙም የማይፈቀድለት ገጠመኝ ነው። እናንተ ግን ኖራችሁበት። ቤተሰብም ተጎዳ።
እኔ ፈላስፊትኢትዮጵያ በግርማ ሞገሷ፤ በማዕረጓ ልክ፤ በአቅሟ በተፈጠረችበት miracle
ኦርጋኒክ ተፈጥሮ ልክ አለች ብዬ አምናለሁኝ። መናድን ለሚመኙ፤ ስብራቷ
ለሚናፍቃቸው አሻም ያለው እዮራዊ ሽልማቷ ነውና። አወን ኢትዮጵያ አለች።
ለልጆቿ ሙሉ የመኖር ነፃነት የመገብ አቅም በፖለቲካ ሊቃናቷ በመሆኑ እንደ እናት፤
እንደ እምዬ ለመሆን #ዘመን ፈተናት።
#ብቻ ብቻ ……
አይዟችሁ! ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ለቤተሰቦቻችሁ ስንቅ ለማቀበል በማይቆጠቡ፤ አቅም፤
ጥንካሬ ፈጣሪ ይሰጥ ዘንድ እመኛለሁኝ።
#ቸር ዜና ሁልጊዜ እጠብቃለሁኝ። ቸርነቱ የማያልቅበት አማኑኤል ስቃይ፤ ሃዘን፤ በቅቶ አዲስ ዘመን
የትቅቅፍ የክብርብር የመፈቃቀድ፤ የይቅርታ፤ የምህረት፤ የአንተ ትብስ የአንቺ የድግግፍ ዘመን
በአገር #የመተንፈስ አቅም ሙሉ እንዲሆን እመኛለሁኝ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የፖለቲካ እስረኛ እንዳይኖር ጽኑ ምኞቴ ነው። ሳልሞት ይህን ባይ፤
እረፍቴ ሰላምን ሰንቆ በሆነ ነበር።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ከኑሩልኝ በፊት ግን እንዴት አድራችሁ፤ እንደምን አረፈዳችሁልኝ? ሰንበትን በወገን ዕሳቤ ትፈቅዳላችሁን?
የእስረኛ ቤተሰብ በአገር አያኮርፍም እና #በ2018 ዓም የምርጫ ሁነት ትጋቱ እንደሚኖር አስባለሁኝ። ቢያንስ ይሄ
ከግምት የሚገባት ማስተዋል ቢኖር።
ሥርጉተሥላሴ።
SerguteSelassie.
13/06/026.
#ፍትህ!
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ