ለዝክንትለኛዋ ዓለም ፈውስ ትሆን ዘንድ የተመረቀች - የተመረጠች - ሴት!

መኖር እንዲያምርበት ….
„ልቤ በመናፍቅ ዝሏል።“
መጽሐፈ እዮብ ፲፱ ቁጥር ፳፯
ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selasssie
09.02.2014 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)



·       መግቢያ።
እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ይህ ብሎግ ሥራ የጀመረው በግንቦት 1 ቀን በ2018 ነው። ከዚህ ቀደም በስፋት የተሠሩባቸው ጉዳዮች በዘሃበሻ ወይንም በኢትዮ ርጅሰተር ነው። ቀደም ባለው ጊዜ በራሴ በጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮም ነው። እኛ እራሳችን ሲሞላብን እንደምንቀንሰው ሁሉ ዘሃበሻም ሆነ ኢትዮ ሪጅሰተር ሆነ ዘሃበሻ እነሱ ደግሞ አርኬቡ ሲሞላባቸው መቀነስ ግድ ይላቸዋል። ግሎባል ጉዳዮችን ስለሚያስተናግዱ ጫና ይበዛባቸዋልና።  

ስለዚህም ጹሑፎቼ ሊሠወሩ ይችላሉ። ታሪክ ነው። ታሪኩ የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል በአንዲት ዜጋ ዕይታ እንደ ዘመኑ ነው። ዛሬ በ2014 እንደምጸፈው ዛሬ አልጽፍም። ስለምን? ዘመኑ በራሱ የሚያመጣው ለውጥ ስላለው። 

ግን በዛ ዘመን የነበረው ዕይታ እና ግንዛቤ ዛሬን በሃሳብ በማገናኘት እረገድ ምን ድርሻ አበርክቷል የሚለውን ያሳያል፤ በሌላ በኩል ግን የአንባቢያን ዕይታም በዛ ዘመን በነበረው ንቃተ ህሊና ልክ የተሠራ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል። ስለሆነም ከጻፍኳቸው ወዘተረፈ ወጎች ውስጥ በዚህ ብሎግ እንዲቀመጡልኝ የምፈቅዳቸውን በተከታታይ ፖስት ለማድረግ አስባለሁኝ። www.tsegaye.ethio.info ያለው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው።

·       እንዲህ ነበር የተጀመረው በ2014 ጡሑፈ …

አዳም እንደተቆለፈ ነው …. ለገርገብም .. እእ -
ግን አዳም እንዴት ነበር ለህያውን ዕውቅና የሰጠው እንደ መሰጠረው አለፈ ማለት ነው …. አዋቂ ነገር ዬት ይገኝ ህም!

ያለፈው ሰንበትን ከአህዱ በፊት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንድል ፈቀደ አባቴ ….. እሱ እራሱ ለሰጠው ሥጦታ ጊዜን ተመኙ ባለሙሉ ባለሥልጣኑ ክርስቶስ ነውና እኔም ፈቃዱን ደስ ብሎኝ ተቀበልኩ። ጥበብ እራሱን ፈልጎ ያገኛል። በጮሪት ወይንም ቀን - እኩል ላይ ወይንም ከብት ግባት ወይንም በግርማ ሞገስ ታጅቦ ድንግዝግዝን ተገን አድርጎ እረፍት በሚሰጠው ….. ብቻ በአሰኘው ቅጽፈት  ከአክባሪው ጋር ከቸች ...
·       ሴት።
ስትፈጠር --- በተጨማሪነት ወይንም በማሟያነት አልነበረም፤ በክፍት ቦታ ሸፋኝነትም አልነበረም፤ እንዲያምርብን - እንድንዋብ - ሰውነታችን አወንታዊ ኃይል ኖሮት የኑሮን ዝክንትል ሳይቀር ደስ ብሎን እንሸከም ዘንድ፤ የተቆጣጠሩ ችግሮችንም ለመዳኘት ነው የተፈጠረቸው - ሴት።

ስለ ድርጅት መፈጠር ስናስብ እስትንፋሳዊ የድርጅት ሰቅ አድርጎ የፈጠራት ሴትን ነው አባታችን። የመጀመሪያው የህይወት ባለሙሉ ሥልጣን የመፈቃቀድ ድርጅተ ጥንስስ ሚስጢር ናት - ሴት። ህይዋን ባትፈጠር ዓለም ወላቃ ትሆን ነበር። ትተረተርም ነበር። ምክነት ይጨፍርባትም ነበር። ዓለም ያዳልጣትም ነበር። ትውልድም አዳም ላይ ያቆም ነበር። ለነገሩ ትውልድ የሚባልም ቃሉ እራሱ  አይኖርም ነበር። ጭጎጎትን ተላብሳ ዓለም በአንድ እግሯ ተንጠልጥላ ቁሞ ቀር በሆነች ነበር። ወጣ ገቧ ዓለም ቀን ተሌት የማይለይባት ድቅድቅ አጥንታም ግጥ ገድል በሆነችም ነበር - ።


·       ጡት።

የጡት - እትብትነቱ መገለጫውም ሴት፤ የእናቷን መክሊት ፈጻሚ አድርጎ ትውልድን ልጅ ሆና ብቻ ሳትቀር እናት ሆናም እንድታዬው ማደረጉስ ይህ ሰማይና ምድርን በሥልጣነ ክህሎቱ - በእስትንፋሱ የፈጠረው አምላክ የጥበቡን ዲካ ለተሰጣቸው ብቻ እንዲለኩት ፈቀደ። ፍሬ ዘሩ የማይነጥፍ፤ ሰው ሰራሽ መገጣጠሚያ ሳያስፈልገው ቀጥ ብሎ በጥበቡ ይጓዛል ….  በኃያል ጥበቡም አሳምሮና አስመችቶ ገነባ … እሱ ባለው …. ለእሷ ሊሰጥ የሚገባው የላቀ አክብሮት ይህ ብቻ በበቃ ነበር። እንኳንስ ዕልፍ ክህሎቷ ታክሎ ….

ይህ ልዑቅ የመኖር ሰማያዊ ኪነ ጥበብ መኖር እንዲያምርበት ብቻ ሳይሆን መኖርም እንዲኖር እራሱን መኖር የፈጠረበት ታላቅ ሚስጢር ነው። ከዚህ አንጻር ገባ ብሎ እልፍኙ ሲፈተሽ የመኖር ማለቴ ነው፤ የደም ጋኑ ሥር ያለው ከሴት ዕንቁ ልቅ ስለመሆኑ ያለምንም አስተርጓሚ ማግኘት ይቻላል።

„እመ ብዙኃን፤ እመ ብርኃን፤ የመዳህኒት እናት፤ የሰላም መገኛ፤  የብሥራት ምንጭ“ እነዚህ ንዑዳዊ ኃይለ ቃሎች ሁሉ ውክልናቸው ለሴት ነው። „እመ ብርኃን“  የብርኃን ውድ እናት ጨለማ - የተገፈፈበት፣ ጨለማ - የተሸነፈበት፣ ጨለማ - የተገረሰሰበት፣ ሰው እንደ ሰው ህሊናው በርቶ ፍጥረተ ነገሩን ይመረምር ዘንድ ብልኃት የተቀዳጀበት ዓይኑ ፏ ፍንትው ብሎ የተከፈተበት፤ ቀንና ሌሊት - ጽድቅና ኩነኔ፤ እሳትና ውሃ፤ መደመርና መቀነሱ፤ ክፉና ደጉ፤ ሀዘን ተፍሰኃው፤ ሞትና ህይወት የተለዩበት፤ ላቅ ያለ ሥነ ህይወታዊ ሆነ ሥነ - ፍጥረታዊ  -ትርጉምን ይሰጣል። የዚህ ሃዲድ ጭብጥ ማዕከል ደግሞ ሴት ናት - ጉልላት። የመኖር ርሰተ ጉልቱ - ብልቱም እሙዬ ናት። 

„እመ ብዙኃን“ የብዙሃን ማህጸን፤ የአዲስ ጥንስስ አብሳይ ፍሬ ብቻ ሳይሆን ለአደራ ተረካቢነት የተፈቀደች፤ ለፍጥረት ሙሉዑነት ያታመነች ብቸኛና አስተማማኝ ፍጡር እንደ ማለት። ለዝክንትለኛዋ ዓለም ፈውስ ትሆን ዘንድ የተመረቀች - የተመረጠች - መዳህኒተ - ፍጡር እንደ ማለት …..፤ ለብዙኃኑ ድህነተ - ሥጋና ነፍስ በወጥነት እንድትከሽን የተሰጠች፤ ተፈጥሮን ለመፍጠር ፍጽምና ያላት ሙቀታዊ ሥጦታ …. እንደ ማለት፤ ታድላ - ደልዳላ!

„መዳህኒት“ ከበሽታ - ከድውይነት - ከጭንቀት - ከችግርም - ልትታደግ የምትችልበት ቁልፍ የተሰጣት …. እንደ ማለት … ግን ስንቶቻችን ፈተሽነው፤ ስንቶቻችን ሰማይ ላይ ከማፍጠጥ ችግሮቻችን - መከራዎቻችን - አሳሮቻችን - ሆነ ስንጥቆቻችን ለመፍትሄነት በኃብታችን ተጠቀምንበት?! ….. ለመሆኑስ በዚህ አምላካዊ አምክኖያዊ ሥጦታ ሰማያዊ ቋንቋ ስምምነቱስ አለን?! መግባባት እንችላለን?! ለማድረግ ቀርቶ ለማድምጥ ፈቃዱ አለን?! ለአዳም ልጆች ጥያቄውን በጥያቄ ሳይሆን መልሱን እራስን በውስጥነት አርሞ ድርጊት ማሳ ላይ እንዲሆን ትጠበቃላችሁ …. እነ - አዳም። - ህ።

ግን ዕንባ ምንድን ነው - የጥያቄ ምልክት። ዕንባስ ከዬት ይመጣል - የጥያቄ ምልክት። የዕንባ ተፈጥሮስ ምንድን ነው -የጥያቄ ምልክት። የእንባ ክፈለ አካላት አወቃቀሩ - አደረጃጃቱ - ስምሪቱ እንዴት ይሆን - የጥያቄ ምልክት። ዕንባ ገባር ወይንስ ውቅያኖስ ወይንስ ሃይቅ - ወይንስ ምንጭ ወይንስ ማህጸን ምንድን ነው - የጥያቄ ምልክት። ዕንባና ስኬቱ፣ ዕንባና መቼቱ፤ ዕንባና ፍቅሩ፤ ዕንባና ሰርጉ፣ ዕንባና ድግሱ፣ ዕንባና ድንግልናው፣ ዕንባና ጫጉላው፣ ዕንባና ተስፋው፣ ዕንባና ልማቱ፤ ዕንባና ሚስጢሩ፤ ዕንባና ምህረቱ፤ ምንና ምን ናቸው - የጥያቄ ምልክት። ይህንም ጥያቄ የአዳም ልጆች እንዲመልሱት ልባቸውን ዐሻቅዬ ሽው ልል ወደደድኩ ….. አትይዙኝ ነገር የዋዛ ዬት ስገኝ ….

ግን ዕንባ አድማጭ - ተናጋሪ - ተዋናይ - የጭብጥ አናት፣ ተራኪ፣ ትራጀዲ፣ ኮሞዲ፣ ስሜት፣ ሃሳብ፤ አይዲያ፣ ዓላማ፣ ቋት፣ ቀለም፣ ውስጥ፣ ውጭ፣ ገር፣ ቁጡ ወይንስ የበቃ ባህታዊ … ወይንስ ሐዋርያ … ነብይ ---- ቀንዱ ማን? ለምን ተልዕኮ? ምን ለማሳካት ትልሙ፤ ምን ለማጣራት- መንሹ? የምርምር ማዕከሉስ ምን? ግን ዕንባ ዐይን አለውን …. ከዓይን ብቻ ነውን ተፋሰሱ - የላቀ - የመጠቀ - ትውልድን የመገንባት ስበት አለውን? …. ለአዳም ልጆች ፈተና ይሰጥ …. መኮረጅ አይፈቀደም። ቾኩም ሰሌዳውም አፋጧልና - ተፋጠጡ። ራስን ችሎ መመለስ …. ወኔን ይጠይቃል ….

ዕንባ መፍትሄ - ጸሎት - ጥያቄ ወይንስ - ሳቅ ወይንስ ድርሳን ወይንስ ሐተታ ወይንስ፤ ድንገት፤ እ - ምን?  ድርሳን የጥያቄ ምልክት። ግን እኮ ዕንባ ስለምን ነው ሙቅ የሆነው ፍቹን ታውቁታላችሁ? ዕንባና ብርድ አይተዋወቁም አይደል?  ዕንባ ግን በማን ያምራል? ግን በዕውን ያምራል? ውበት አለው ዕንባ? ጸዳልስ? የደም ገንቦ ነውን? ግፊቱስ  ስንት ዋት
? … መስፈር ይቻላል … ስፋቱ በጋሻ ወይንስ የበሬ ግንባር ታክል …. ግን ጠብታ ህይወት ሰጪ …. ይባል ምን ይባል?
·       እቴጌ ሴት?

ተከታይ ናት መስራች፣ ተለጣፊ ናት ወይንስ ደም፣ ጥገኛ ናት ወይንስ ራስ፣  ኑሮ  ---- ሴት፣ ስለምን ተፈጠረች፣ ስለምን መጣች፣ ስለምን ታዬች፣ ስለምን በቀለች፣ ለላንቲካ፣ ለፎቶ፣ ለምስል …. የጥያቄ ምልክት። ለአዳም ልጆች …. ምንድን
ናት ለመሆኑ ሴት?!? ዕቃ ---- ክክክክክክ ~___~  የመንፈሰ - ህሊና፣  የመንፈስ ልብ፣ የመንፈስ ክናድ፣ የመንፈስ ጥርኝ፣ የመንፈስ ማዕዛ፣ የመንፈስ ወዝ ምን ትሆን ይህቺ ብልኃት …. ማስተዋልን ጠይቁት የአዳም ልጆች።


እናንተዬ አዳም እንደ ተቆለፈ ነው ግን አያሳዝናችሁም። ደንዳና አትሁኑ ትንሽ አዘኔታ - በመቁንን ሳይሆን በገፍ ለራሳችሁ ብትሉ። በስተቀር በብረት በሩ ክርችም አቤት! አቤት! ጭካኔ …. ይህ ቢሆን ዓለሙን ድብልቅ ታደርጉት በነበረ …. በሆነና አንድ ቀን በታያችሁ። ለአንድ ቀን አይደለም እኔ እመሻው ለ30 ወርዳም ቀናት …. ሽንጠ ሸበላ ቀናት።

ለፍሬ - ዘከረን - አዝምረን ቆዬን አብረን። በጥያቄ ሳጣድፋችሁ … ይቅርታዬ ከልብ ምስጋናዬ ከቅኑ ንጡህ መንፈስ
ይደረስልኝ ….

ይቋጭ --- ሳልጠግበው። እሱ እራሱ ቀጥ አደረገኝ። መሰቀለኛውን ስለሰጠኝ ጽናነ - አድህነነ - ሆነ ይደለዎ አልኩኝ።
ተመሰገን። የአዳም መፍቻ ቁልፍ ጠፍቶበት አብሬ ስባትል ሳፈላልግ፤ ጥሎብኝ እኔም በማረፊያዬ ጊዜ ስማስን ዘጭ  ዘጭ ስል ስባዝን  ደከመኝ፤ እናንተንም አደከምኩኝ። አይዞን ቁልፉ ሲገኝ አብረን እናርፋለን። እስከዚያው ናፍቆቴን ሰንቄ እጅ ነስቼ በክብር መስጋናዬን በሐሤት ላኩላችሁ … እኔ ካለእናንት ምንም ነኝና … ክብሮቼ ደህና ሰንብቱልኝ - የኔዎቹ። ቁልፉ ሲገኝ አብረን እንርፋልን የዛሬ አራት ዓመት አልኩን ዛሬ 50% ካቢኔ የሴት ሊሂቃን ነው፤ ፕሬዚዳንት፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ ምርጫ ቦርድ ህያውያን ድንቅ ዘመን የታምር ያህል … ተመስገን!

ጠብታ የፍጥረት ቅምረት
ሙቀት ~~~__~~~ ለፍውስት
እርቀት--------------------------------------------------------------~-------------------------------------------------
ስንቅ በቅነንት
ቀደምት
ስኬት - በብልሃት
ሴት
ናት
ኣናት
ው - ስ  - ጠ  - ት

የመኖር ፍጠረቱ ሴት!
የመኖር ውበቱ ሴት!
የመኖር ምቾቱ ሴት!
የመኖር ብልቱ ሴት!
የመኖር ቅኔ ሴት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ኑሩልኝ የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።