ልጥፎች

ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ ሕይወት!

ምስል

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

  https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html ዛሬ ያለው ነገር „ ፈረቃም፤ ተረኝነትም “ አይደለም። https://www.youtube.com/watch?v=-yWKYUC_9iA&t=165s ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውድቀት እንጂ የዴሞክራሲ ተስፋ የልቅና ምህንድስና አይደለም። https://www.youtube.com/watch?v=ipRpgkxgioU&t=22s አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው። { የወግ ገበታ 08.06.2019} https://www.youtube.com/watch?v=ZvYbH35esVk&t=49s አሉታዊ ዴሞግራፊ የቂም ደም ነው። https://www.youtube.com/watch?v=JSlvGahMtwg&t=527s አሉታዊ የዴሞግራፊ ምህንድስና የበታችነት ስሜት ደዌ ነው። { የወግ ገበታ } https://www.youtube.com/watch?v=xFrQuu3qjyg&t=520s የአሉታዊው የዴሞግራፊ ዕሳቤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዎሎጂ ነው። { የወግ ገበታ 17.06.2019} https://www.youtube.com/watch?v=myaY01aP4pg&t=278s የኦሮሙማ ጠቀራዊ የዲሞግራፊ ፋሽስታዊ ጉዞ ከአቶ ለማ መገርሳ አንደበት።  

አብን እና የሥርጉተ ዕይታ ትናንትና ዛሬ።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።   አብን እና የሥርጉተ ዕይታ ትናንትና ዛሬ     እኔ በተፈጥሮዬ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ሲፈጠር እንደ ገናም ፖለቲካ ድርጅቶች ተጣመርን፤ ተዋህድን ሲሉ አይደንቀኝም። ብዙም አልደክምበትም። ሲመሰረት በብዛት የጸፍኩበት አብን እና ባልደራስን ብቻ ነው። ምክንያቱም የህልውና ተጋድሎ የፈጠራቸው ስለሆኑ ብቻ። ስለሆነም አብን ሲፈጠር የጻፍኩት፤ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም እና ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማን የሞገትኩበት ሊንኩ ተቀምጧል። በውጭም አብን ወጀቡ ሲበዛ ዕውቅና እንዲያገኝ ተደክሞበታል። አብን በተነሳበት መክሊቱ መዛነፍ ሲያሳይ ደግሞ ሊነገረው ይገባል። በቂ አጀንዳ አለው። በራሱ አጀንዳ ውስጥ ሰክኖ ለተልዕኮው መትጋት ይኖርበታል። ኦህዴድን ልተካ ብሎ መገልገል አይገባውም። ኦህዴድ የስሜን ፖቲካ እንዲደቅለት ይፈለጋል። የሰሜን ጥንታዊ ከተሞች እና ቅርሶቹ ከተሞች በጦርነት እንዲወድሙ ይሻል። በጦርነት የአማራ ህዝብ እንዲጎሳቆል ይሻል። በጦርነት የትግራይ እና የአማራ ህዝብ በቅራኔ እንዲወጠሩ ትውልድ እንደሚመክን ይሻል። የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ትቢያ እንዲሆን ይሻል። ከተሞችን እኮ ፕሮቴስታንቶች እንዲመሩት እዬተደረገ ነው። ዕድሉን ባገኝ አገር ልመራ እችላለሁ ያለ ፓርቲ በዚህ መሰል የአብይዝም ትሪኪ ገብቶ መማገድ አይገባውም። አቅሙን አውቆም መንቀሳቀስ ይኖርበታል። የኃይል አሰላልፉን መረዳት ይገባዋል። አብን ኦነጋዊው ኦህዴድ ለፈጠረው ፈንቅል መግለጫ ማውጣት፤ ህወሃት በሽብርተኛ እንዲፈረጅ መጠዬቅ፤ በአማራ ክልል የሌሉ አቤቱታ የቀረበባቸው የአማራ ርስቶችን ምርጫ አያካሂድ ብሎ ማገድ የማይሆን አካሄድ...