ስትዘነጣጠሉ ባጃችሁ አሁን ደግሞ ትቅቅፍ። የፖለቲካ ግሽፈት ( Inflation.)
ስትዘነጣጠሉ ባጃችሁ አሁን ደግሞ ትቅቅፍ። የፖለቲካ ግሽፈት ( Inflation.) "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።" #ምራቃቸውን ለዋጡ የአድማጭነት ፀጋቸው ኢትዮጵያን ቁም ነገር ዬማድረግ ዓላማ ላላቸው የዕንባ ሁነኛወች። ህግ መተላለፍ ቅጣቱ የምድር ይመስል ይሆናል። ወይንም ዳንቴል የእጅ ሥራ፤ ወይንም የፋንታዚ ግንብ አይደለም። ህግ መተላለፍ መንፈሳዊ ቅጣት ያመጣል። ከአቅም በላይ ቅጣት ያስመጣል። "ወግዱ፤ ጥርግ በሉ፤ እናሳያችኋላን፤ የቀን ጅብ፤፦ መጤ፤ ፀጉረ ልውጥ፤ ሰፋሪ፤ ወዘተ …" ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ዝልኝ ዕሳቤወችን የፈጠረች አገር አይደለችም። በዚህ ልቅ ሁነት አይደለም የጥቁር አብነቷ፤ የአፍሪካ አንከሯ ኢትዮጵያ የሦስት ጉልቻ ኩነትም አይፈጠርም። ህግ፤ ሥርዓት በባርኔጣ፤ በገበርዲን፤ በከረባት ወይንም በፋሽን እና በፎቶ ሸው አይተረጎምም። ይህንን "መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህን" የመሰጠሩ ብቻ ይኖሩታል - ህይወቱን። ምክንያቱም መሬትን ስትራመዱባት ተጠንቅቃችሁ ተብለው በዚህ ዝልቅ የመንፈስ ልዕልና በአርምሞ ልቅና ያደጉ ብቻ ያውቁታል። እኔ ሚዲያ ዬሚባለው #ኦሜኮ ምን አንደበት ኑሮት፤ ምን ልሳን ኑሮት የህወኃት እና የብአዴንን ትቅቅፍ እንደሚዘግብ፤ አብኖች ለዚህ ድልቂያ እንደምን እናሸብሽብ እንደሚሉ፤ ህወሃትን ብን አድርግልን ብለው አብይዝምን የከበከቡ መንፈሶች ሁሉ በዚህ ውስጥ መንፈሳቸው ተረጋግቶ ዕለታዊ መኖራቸውን እንደምን በተስፋ ማጣት እንደሚያሳቅሉት አስበዋለሁ። ለዚህ ነበር ጦርነት አያስፈልግም፤ በጦርነት አሸናፊ የለም፤ ፊታውራሪ ጦርነት አሸነፍኩ ካለም #በቀል እና #አመድ ያፍሳል በማለት የሞገትኩት። አሁን የጥንቱ ወዳጄ አቶ ...