ልጥፎች

#ሲቃ ስለ ህክምና ዋርካው፤ ፍቱኑ፤ ርትሁም ክቡር ፕሮፌሰር ዶር፤ ማለደ ማሩ።

ምስል
  #ሲቃ ስለ ህክምና ዋርካው፤ ፍቱኑ፤ ርትሁም ክቡር ፕሮፌሰር ዶር፤ ማለደ ማሩ።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"   #ምዕራፍ ፲፰።       ክቡርም፤ ልዑልም፤ ንጉስም ብለው የተገባ ነው። ተማሪ እያለሁኝ የኬሚስትሪ እና የባይወሎጂ ባለ100% ተማሪ ስለነበርኩኝ የህሊናዬ #ጽንስ የዚህ ታላቅ ሰው ጥረት እና ህይወት ነበር።    ያን ጊዜ በዛች ትንሽዬ ወጣት ህልም የነበረው በዘርፋ ገፍቶ #ሳይንቲስት የመሆን የተልዕኮ ስንቅ ነበር። ግን የእቴጌ ጎንደር የአቀማመጧ ሁነት የከፋኝ ቤተኞችን ጋበዘ እና ባዕቴ የጦርነት ቀጠና ሆነች። ቤተሰብ ተሰደደ። ኃላፊነት በዛ ለጋ ዕድሜ ላይ ተጫነ። ህልሙም ተረሳሳ። ታናሽ እህቴን ተክቼ ትምህርቴን ለመቀጠል ሳስብ #ህወሃት ሥልጣን ያዘ። በቃ የትምህርት ናፍቆት ጋር መራራ ስንብት ሆነ። በስደቱም ታለመ ግን ፍጹም የማይቻል ሆነ።   ጋሼን ተማሪ ሆኜ የህይወቴ #ሞዴል እንዳደረኩት አልቀረሁም። የሥራ ትጋቴ፤ ቅልጥፍናዬ፤ ሥራን ባዕቴ ማድረጌ፤ በዛ የወጣትነት ዕድሜዬ ወጣትነቴን ተላልፌ እራሴን ከርክሜ፤ ከብዙ ነገር ቆጥቤ መባተሌ እድገቴን ፈጣን አደረገው።   ሥራዬ ከዚህ ታላቅ፤ ቅን፤ ጨዋ፤ ትሁት፤ ሰው አክባሪ፤ የጥረት #አብርኃም ጋር አገናኜኝ። በአካል ተገናኜን። የዕውነት የመማርን ልቅና በልዕልና ያዬሁበት ታላቅ የተግባር ዓራት ዓይናማ፤ ቅኔም ሰው ሆኖ አገኜሁት።   ለዛች በዕድሜ፤ በተመክሮ፤ በዕውቀት፤ በሥራ ልምድ አናሳ ለሆነች ለግላጋ፤ ቁመቷ ዘለግ ያለች ወጣት የአገር ጉልላቱ ታላቅ ሰው ይሰጥ የነበረው አክብሮት #ዩንቨርስቲ ነበር። ከህሊና በላይ ነበር።   ታናሽነቴን ስለማውቅ ከተቋሙ ጋር በሚያገናኙን የወጣት ማ...

Die Erde will Frieden. Auch der Himmel will Frieden.

  ·        Die Erde will Frieden. Auch der Himmel will Frieden. ·        Die Menschheit will Frieden. ·        Die Natur sucht Ruhe. ·        Die Philosophie sucht den Frieden. ·        Die Wissenschaft strebt gerne Frieden. ·        Fact will Frieden. ·        Die Wahrheit sucht den Frieden. ·        Kinder lieben Frieden. ·        Haus- und Wildtiere suchen Ruhe. ·        Die Luft des Lebens braucht Frieden. ·        Die Berge wollen Frieden. ·        Die Flüsse wollen Frieden. ·        Der Boden selbst will nicht durch Bomben verbrannt werden. ·    ...

#ራስጌ፤ #እግርጌ፤ #ቁርጭምጭሚትን ያላገኜም ተገኜ --- በዘመነ #ብልፄው።

ምስል
  #ራስጌ ፤ #እግርጌ ፤ #ቁርጭምጭሚትን ያላገኜም ተገኜ --- በዘመነ #ብልፄው ።   የቤት ልጅ፤ የእዳሪ ልጅ። "አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።         #ምዕራፍ ፲፰።    ዘለግ ያለ ዕይታ ነው ምርጫ ሂደቱን በዚህ ብከውነው ፈቃዴ ነው ግን ብዕሬ ከፈቀደች ብራናዬ ይሁን ካለ።   #እፍታ ።   የአፍሪካ ግርማ ሞገስ፤ የዓለም ዲፕሎማሲ ፬ኛ ከተማ፤ የኢትዮጵውያን እኩል የተስፋ አንባ በሆነችው ውብ፤ ድንቅ፤ ለጋስ፤ ሩህሩህ፤ ህብራዊት፤ ተደሟዊት #ማንጠግቦሽ በሆነችው የእኛይቱ እቴጌ አዲስ አበባ ላይ ብልፄው ግልጽ የሆነ አቋሙን ሰሌዳው ላይ ለጥፎ አነበቡኩት፤ ተርጉሙት፤ አመሳጥሩት እያለን ነው።   እኔ እንኳን የብልጼው ለቀቀቅ ያለው መጠሐፋ ከመቅደሙ በፊት በዚህ ዙሪያ በጣም የቀደመ ዕይታዬን ማጋራቴን ድፍን የቤታችን ቋሚ እና ጽኑ ታዳሚወች ያውቃሉ። አዲስዬ ከመስከረም 5/2011 ዓም ጀምሮ በኦሮምያ ክልል ህግ ነው የምትተዳደረው የሚል አቋም ነው ያለኝ። የሂደቱ ሁሉ ግብረ መልስ ያን ስለሚያመለክት።   #አቅላይነት ።   በኢትዮጵያ ፖለቲካ አንዱ አቅላይነት የተለመደ ነው። ገዢው ብልፄውም ይሁን ተደማሪ፤ #ተቀላች ፤ ተመጋጋቢ፤ ተፎካካሪ፤ ተቃዋሚ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉም አንዱ ሌላኛውን ሲያቀል፤ ሲያጣጥል ውሎ ያድራል።   ግርም ይለኛል። በማጣጣል፤ በማቅለል አቅምን መገንባት አይቻልም። አቅም አቅም ፈጣሪን፤ አቅም አክባሪን፤ ለአቅም ዕውቅና ሰጪን፤ አቅም አድራጊነትን ይጠይቃል።   ምንም ሳይኖር የደከምክበት፤ እራስህ - የምታዝበት፤ አንተው የምትመራው ወይንም የምታስተዳድረው የተደራጄ አቅም በሌለበት ቀን ቆርጠህ፤ ጊዜ ወስነ...