ነገረ መሠረት ቋሚ #ብራንድ ሊሆን ይገባል።።
ነገረ መሠረት ቋሚ #ብራንድ ሊሆን ይገባል።። "የብልህ ሰው ልቦና ምሳሌን ይተረጉማል፤ የአዊቂ ሰው ጆሮም ጥበብ መስማትን ትወዳለች።" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፯) #ምዕራፍ ፲፱። #እፍታ ። እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ሰሞናቱ በአገረ ምክክር ላይ አጀንዳወች በርከትከት ብለዋል። ስለሆነም በጥቂት ጉዳዮች ላይ ሰሚ እንደለለ ባውቅም ግን ውስጤ የሚለውን ባጋራ መልካም ነው። የነፃ አውጪ ግንባር መንፈስ ሁሉ #ቀደምትነትን ይሸሻል። #አዛውንት ታሪክን እንደ ጦር ይፈሩታል። ትውፊት እንደ ደመኛ ያዩታል። መቅድመ ሥልጣኔ ጸጉራቸውን ያቆመዋል። የማንነት ቀውስ ሲኖር እንዲህም፤ እንዲያም ያደርጋል። የነፃ አውጪ ግንባር መንፈስ ተስንሳፎ፤ እርሾ አልባ ከሌላ ዓለም የመጣ ዓይነት ዘመናይነት፤ ቅልጣንም ብዙ ጊዜ ይታይባቸዋል። አጥብቀው ከሚጠሉት በኽረ ጉዳይ #ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማውን ነው። አፍሪካውያን አክብረው የሚነሱት ደግሞ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላምን ነው። ብዙ አገሮች እሱን መሠረት ያደረገ መለያቸው አድርገውታል። ለአፍሪካውያን፤ ለቡኒያውያን፤ #ለጠይማን ዕንቋቸው የምንጊዜም ዕንቁ ነው። ብሄራዊ ሰንደቅ ዓለማችን ወደ ጋድም አረንጓዴ፤ ቢጫ ቀይ ሲሆን ሦስቱም በስፋት ይሁን በቁመት #ተመሳሳይ ናቸው። አረንጓዴ ከቢጫው አያንስም አይወፍርም፤ ቢጫው ከቀዩ አይቀጥንም አያጥርም። አቀማመጡም ከላይ ወደ ታች አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ ነው። አንዳንድ ድርጅቶች አረንጓዴን ከሥር ያደርጋሉ መሠረትን በሚሉት ድርጅት ውስጥ ያ #ዝበት ነው። ግድፈቱ ግዙፍም ነው። ...