እናትም አባትም ሆነው ላሳደጉ አባት አቶ ይርጋለም ይህ #ጥቁር ዜና #ማት ነው።
"የእግዚአብሄር ቸርነቱ ብዙ ነው እያልክ፤
በኃጢያት ላይ ኃጢያት አትሥራ።"
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭)
#የተባጀበት የወል አስጨናቂ የሰርክ መርዶ።
የሞዴል ሩት ይርጋለም እህት (ወ/ሮ ወት) ቅዱሳን ይርጋለም በሥጋ መለዬትን ዘሃበሻ ላይ ዜናውን ሰማሁኝ። የሁለቱ እህታማቾች #እናታቸውም፤ #አባታቸውም አቶ ይርጋለም እንደምን ሆነው ይሆን? ልጃቸው ሞዴል ሩት ቃለ- ምልልስ ስታደርግ ዕድምታውን የተረዳሁት ልጆቻቸውን እያሳደጉ ፈቅደው #በምናኔ የኖሩ፤ በሥጋ ለተለዮዋቸው የትዳር አጋራቸው ፍጹም ታማኝ፤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማቸው ልዩ አባት መሆናቸውን ተረድቼ ነበር። በጣም ቁጥብ። እንደ እነዚህ ዓይነት ተብዕቶች ቁጥብ ናቸው። በዘመናት መሃል ነው የሚገኙት።
ይህን መሰል ሰብዕና #የተለመደ አይደለም። ትዳር በህይወት እያለ የክት እና የዘወትር የሚያሻቸው ባሉበት ዓለም፤ ትዳር በሥጋ ሲለይ ለዛውም በወጣትነት በዚህን ያህል ጽናት ዕድሜ ሙሉ #በተዕቅቦ መኖር መመረቅ ነው።
እንዲህ እራሳቸውን ሰጥተው፤ መኖራቸውን ለፍጹም ታማኝነት እና ለባለቤታቸው አደራ ጠባቂ በመሆን ያሳደጓት ልጃቸው ስትታፈን፤ #ስትታገት ጭንቁን እንሰበው። ለወላጅ ምጥ ነው። የተባለውን ገንዘብ ማቅረብ ስላልቻሉ ይመስለኛል እንሆ እንደዛ በብቸኝነት ያሳደጓትን ልጃቸውን ያጡት። እግዚአብሄር #ያጽነወት። አሜን። ብርታቱን ይስጠወት። አሜን። ለማን ብለው በዓለም እየኖሩ መነኑ? ለልጆቸወት አይደለምን? አዝናለሁኝ።
ሞዴል ሩት ይርጋለም ይህን መሰል ሃዘን ስለገጠመሽ እግዚአብሄር ያጽናሽ። አሜን። እቅፍቅፍ ብላችሁ አድጋችሁ እንዲህ ባለ መራራ ስንብት ይከብዳል። በቀጣይ የነገ #የአዲስ አበባ ተስፋስ ምን ሊሆን ይችል ይሆን?
በጠቅላላ መታገድ፤ መሰወር፤ በጭካኔ መገደል #የክፋ ሃሳብ ቤተኝነት ነው። ክፋ ሃሳብ ሰብዓዊነትን፤ ሰዋዊነትን፤ መተዛዘንን፤ መከባበርን፤ መራራትን ወዘተ ይፃረራል። ዓለማችን ክፋ ሃሳብን የምትመክትበት #ተቋም የላትም። ዓለማችን ህግ የማህበረሰቡ ይሆን ዘንድ አልወሰነችም። ስለሆነም ክፋ ሃሳብ እና የወንጀል ተግባር የመኖር ተስፋችን እንዲህም ተጫነው።
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ህግ #የጥቂት ባለሙያወች ብቻ ነው። ለዚህ ነው እኔ መንግሥታት ህግን የማህበረሰቡ ያደርጉ ዘንድ እምሞግተው። መብቱን ያላወቀ ዜጋ ግዴታውን መወጣት አይችልም። ግዴታውን ያላወቀ ዜጋም ከወንጀል ጋር ሊቆራኝ ይችላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚታዩ የወንጀል ጉዳይ ካለማወቅም ነው። ህግን ቃሉን፤ ድንጋጌውን ማንበብ እንችላለን፤ አፈፃጸሙን፤ አተረጓጎሙ ግን መሃይም ነን። መፍታት አንችልም።
በሌላ በኩል የፍቅር ተፈጥሮ በመደበኛ ትምህርት ቤት አይሰጥም። ስለሆነም ትውልዱ #ከጢስ ገጠመኝ ጋር እየተፋለመ ይገኛል። ይህ ሁሉ ጦርነት፤ ይህ ሁሉ መጨካከን፤ ይህ ሁሉ ዕንባ በየዘርፋ የሰው ልጅ የሚገጥመው ጨለማን ለመቋቋም ኤሌትሪክን የሠራች ዓለማችን፤ ክፋ ሃሳብን ለመቋቋም #ተቋም የላትም። #አጀንዳዋም አይደለም። የህግ ጥሰት፤ የሰብዓዊነት ረገጣ፤ የተፈጥሮ ጫና ምንጩን አጥንቶ ዘላቂ መፍትሄ ይሻል።
#ማቄም፤ መቅናት፤ መበቀል ሁሉም የክፋ ሃሳብ ቤተሰባዊነት ነው። የሰው ልጅ ለሰው ልጅ፤ የሰው ልጅ ለተፈጥሮ ሊሰጥ የሚገባው ሃዘን ሳይሆን፤ ምሬት ሳይሆን፤ ተስፋን መንጠቅ ሳይሆን ደሳትን ሊሆን በተገባ። ዓለም ዓቀፍ የጤና ድርጅት አለ። ይህ ጥሩ ነገር ነው። መሬት ግን በሚሊተሪ ሥልጣኔ እየነደደች ነው።
መሬት ላይ አዝዕርት ሲበቅሉ ጸረ ሰብ ኬሚካልን #ውጠው ነው። ነገ ትውልድ ሲመጣ የጤና ዕክል ይዞ ነው። ቀድሞ መከላከል ወይንስ ችግር ፈጣሪውን የቦንብ ናዳ ማስቆም የቱ ይሻላል? ዓለም ሊመክርበት ይገባል። ዛሬ እየነደደ ነው፤ ነገ ከመምጣቱ በፊት ደንግጧል፤ አሮም ሊመጣ ይችላል።
#ክውና።
ብዙ መታገቶችን፤ ብዙ የመደፈር አደጋወች፤ ብዙ የመሰወር ሁነቶች። ብዙ እንደወጡ የመቅረት አሳሳቢ ጉዳይ፤ ብዙ የመገደል ደራሽ ዜናወች በህፃናት፤ በሴቶች፤ በሃኪሞች ላይ አዳምጠናል። የወል በንጽህና #ጸሎት ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ጸሎት፤ ዱዋ ብዙ ነገር ያስታግሳል። መጽናናትን ይሰጣል።
የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ጉባኤ በሚካሄድባት የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፤ የአፍሪካ የመንፈስ ማረፊያ፤ የዓለም ፬ኛ የዲፕሎማሲ ርዕሳነ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ይህን መሰል የክፋ ሃሳብ #መተግበሪያ መሆኗ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። የዳሩ ካልዳነ // መሃሉ #ፈውስ አያገኝም። በጥልቀት ሊታሰብበት የሚገባ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ሰፊ ተግባር ይጠይቃል። ጭካኔ ሰብዕናን ያራቁታል። ይህን መሰል ተግባር ለሚፈጽሙም የሰው ልጆችም ፈጣሪ አምላክ ልቦና ይስጣቸው። አሜን።
ኃላፊነት የሁሉም ኃላፊነት ነውና፤ የሰው ልጅን ማፈን፤ የሰውን ልጅ መሰወር መብትም ግዴታም #እንዲህ መሆኑ ሊያሳስብ ይገባል። አቨውም ተግተው ቢጸልዩበት ስል በትህትና አሳስባለሁኝ።
አንዳንድ ጊዜ የታገሱ ሁነቶች ሳስተው፤ የሚፈሉ ጉዳዮች ተበራክተው ሳይ የተሰወረ ወይንም የተከደነ እርግማን ይኖር ይሆን እላለሁኝ? #ምርቃታችን መነሳት መተዛዘናችን አሰደደው። ሃዘን ለዛውም መራራ ሃዘን እንዲህ በዕቅድ ሲፈጸም እንደ ትውልድ አባልነት፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያማል።
ለአቶ ይርጋለም፤ ለሞዴል ሩት፤ ለመላ ቤተሰብ ለሁሉም ፈጣሪ አምላክ መጽናናቱን ይስጥልን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
27/07/026.

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ