ኢትዮጵያዊነት ስክነት ነው።
እንኳን ደህና መጡልኝ
ድልና ዲል።
„ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤
--- ምን ታደርጋለህ? አልኩት።“
መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ዛሬ ተዚህ ደመንመን ብሏለኝ።
ለነገሩ ሲዊዞች ሚያዚያ ወርን የፈለገውን የሚያደርግ እንደልቡ ነው
የሚሉት።
ድልና ዲል። ዲልም ድልም። ድልም ዲልም። ባለፈው ዓመት ሁለቱንም ተንበርክኮ
የዛቀው የትናንቱ ኦህዴድ የዛሬው ኦዴፓ ሌላ ድልና ዲል ያጋጥምው ወይንስ
ተስፋውን ይጋግጠው እንደሆን ብዬ አሰብኩኝ - ዛሬን ላስክነው ሳስብ ወይንም ስሻ።
ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ጥቅምት ወር በፈረንጆች ኢ ትደፈር ይሆን ብዬ ጽፌ ነበር።
የፈረደባት "ኢ" ትደፈር ይሆን?
02.10.2018
ከዛ ደግሞ ድንገት ተነሰተው በአጭር ጊዜ እንዋሃዳለን ሲሉ የጤና?
ብዬም አንድ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር።
የኢዴፓ እጩነት /አዲስነት ትልሞሽ/
25.02.2018
መቼም ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ሁሉ ነገር ቀላል ነው። ከራስ መተማመናቸው
የመነጨ ይመሰለኛል። ድርጅት የሰው መንፈስ ውህደት ስለመሆኑ እንዴት እንዳዩት አላውቅም። ብቻ እኔ ያን ጊዜ ያነሳሁት፤ በስፋትም የሄድኩበት ጉዳይ አሁን የሁሉም አጀንዳ የሆነ ይመስለኛል።
ኦዴፓ ድሉን አስገኘሁት እኔ ብሎ አስረግጦ እዬነገረ ነው፤ ለሚመራው ህዝብ
በኦሮምኛ ቋንቋ። የቄሮ ንግሥናም ርዕሰ መዲናውን ሳይቀር መንግሥት አልቦሽ
ስለማድረጉ ባለፈው ሰንበትገብ ዜናዎች ነገሩን። እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ብለናል።
በጠ/ሚሩ ከመጋቢት እስከ መጋቢት የሥነ - ግጥም ኪናዊነትም ተብስሮልናል
ይኸው የቡፌው ዐጤነት ዓይነት በዓይነት እንደሆነ። በሚሊዮንም አዳራሻ ምን
ታመጡ ተብሎም ሦስቱ ኮከቦች ነግሰው ዙፋን ደፈተው አዳምጠናል።
በልክ ቢሆን ከመቅሰፍት መዳን ይቻል ነበር። ለዚህም ነው ከንቲባው "እኔ ትልቅ
ሰው ነኝ እንዴት ከተራ አክቲቢስት ጋር እታያለሁ" ሲሉ አስረግጠው አንጋጠውም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አዋጅ ያስነገሩት። የጅብ ችኩል
ቀንድ ይነክሳል፤ የድል አጥቢያ አርበኛ ቢባሉ ምን ሊያመጡ እንደሚችሉ አይታወቅም።
ኦዴፓ የድል በኸር ስለመሆኑ ለሚመራው ህዝብ ብቻ ሳይሆን የውጭ ግንኙነቱም
ከርችሞ ይዞት ስለባጀም ለነጮችም፤ ለአፍሪካውያንም ያንኑ እንደሚነግር ማሰብ ይቻላል። የጠ/ሚር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በራሳቸው ጉባኤ ላይ
ሲነግሩን የሃይማኖት አማባቶችን የማስታረቅ ክህሎቱ ልቅናን አበክረው ሲገልጹ ስምቻለሁኝ።
ያ ራሱ ራሱን የቻለ ተደሞ አለበት። ለዚህ ጉልበተኛው አብዮት የአማራ የህልውና
የማንነት ተጋድሎ ስለመሆኑ ልብ ያሉት አይመስልም። ያው ሁሉን እንጠቅልል
ባይነት የታሪክም ሽሚያ ነው ያለው ነገር። የአሁኑ የወጥ ፓርቲ እንድርቺ
እንድርቺም ተዚህ አንጻር ነው እኔ የማዬው።
በዚህ በፓርቲ ውህደትም ዛሬ አለባብሶ ቢታረስ ነገ ፈጦ የሚታዬው ከታሪክ ሽሚያ አንጻር በእኛ አቅም ተከወነ አይቀሬ ነው። ከተሳካላቸው ማለት ነው። ነገሩ ሲብላላ
የቆዬ ቢሆንም አሁን ዘመነ ኦዴፓ ስለሆነ ሁሉን ነገር በጥድፊያ በመዳፋቸው ካስገቡ በኋዋላ ቀጣዩ የታሪክ ማወራራጃ ያውን መሰሉን መኮፈስ እንዳምጣለን። ይኽንኑ የድርጅቶች ውህደትን ጨምሮ ማለት ነው - ከተሳካ።
ይህም ማለት የመንፈስ ወረራው በአንድ መንፈስ ሥር ይወድቃል እንደማለት ነው። ይሉኝታም፤ ማተብም እኛም አንጠብቅም እንሱም አይደፍሩትም። ስለ እውነት
ድፈረት አንሶ ነው ያዬሁት።
ግን አንድ የኮንዲሚኒዬም ቤት ያገባኛል ብሎ መግለጫ ለሚያወጣ ድርጅት፤
የአንድ አገር ርዕሰ መዲና፤ የአህጉሩን መናህሪያ እውርሳለሁ ብሎ ለተነሳ ድርጅት የኢትዮጵያዊነት አብነት የሆነ የፖለቲካ ድርጅት የማበጀት ክህሎትን ማሰብ
የሚቀፍ ነው የሚሆነው። በኦነግ የመንፈስ ወራሽነት መጪ እያለ ያለ
ኢትዮጵያዊነትን ያስቀርባል ተብሎ አይታሰብምና። ዜጋው ይከበር፤ ቤተ
እግዚአብሄሮችም አይደፈሩ! ቀዳሚው ጉዳይ ነው።
ይህንንም እኛ ከምናዬው ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ተንታኛቸው ዶር ብርሃነመስቀል
አበበ ገልጸውልናል። „አብይ የኦነግ ወራሽ ነው“ ብለው።
ሰሞኑን ማዕት አውርዱ የኦሮሞ ሊሂቅ የኦፌኮን ተቀዳሚ ም/ ሊቀመንበር
የዘፍጥረት ደምሳሽ የባቢሎን ግንብ በአላዛሯ ኢትዮጵያ መስራች አቶ በቀለ
ገርባም መንፈሳቸው የኦነግ መንፈስ ውርስ ቅርስነቱን ውህደቱ እስከምን
እንደሆነ ገልጠዋል ዋልታ ላይ።
እንደሆነ ገልጠዋል ዋልታ ላይ።
ዋልታ ራሱ እግዜሩ ይይለት እንጂ ሲኦል የናፈቅን ይመሰል፤ ሲኦልን ለአንድ
አፍታ ብለን ዲሞ የወጣን ይመስል ማመልከቻ ያስገባን ይመሰል ጉብ አደርጓቸው
ሰነባብቷል። የጥላሸት ሰሞናት። የሰው ልጅ እንዴት ጭካኔን አረመኔነትን እዩ ተብሎ ይገደዳል?
ለነገሩ ፕ/ መራራ እኮ ናቸው የቦርዱ አራጊ ፈጣሪ። አሁን ያን የሲኦል
መንገድ አቅርቦ አወያይቷል ለዛውም በሁዳዴው እጬጌው ዋልታ። ምን
አድርገን ተገኘን ብለናል እኛም ግዑፋን። መቼስ እንደ ሰው መታዬቱ ካበቃ
እኮ ታይቷል ተመስከረም ጀምሮ።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን የአዲስ አባባ ህዝብ ህዝቤ አይደለህም ከእኔ ለምታገኘው ውሃ ሲያሻኝ ማቆም እችላለሁ የሚል ድርጅት እንዴት ለታላቁ አገራዊ ወጥ ፓርቲ
አዲስ ምስረታ ሊቅነት ይብቃል ነው ቁም ነገሩ? የአዲስ አባባ ህዝብ ለመኖርህ የእኔን ፈቀድ ጠይቀህ ነው? ስለምታቀደው ብቻ ሳይሆን ስለምትበላውም፤ ስለምትተነፍሰውም
እኔ ሳልፈርምበት ቅስቅስ የለም ያለ ድርጅት እንዴት አገራዊ ራዕይ አለው
ተብሎ ሃላፊነቱ ይሰጠው?
ይህን መሰል አገራዊ ተልዕኮን ዕሴታዊ ሚዛን ሊያስጠብቅ ይችላል ወይ ተዛሬ
ላይ ሆኖ ማዬት መመዘን ይገባል ኦዴፓን። ብዙውን ሰው ነው አንገት ያስደፋ
ይኽው ድርጅት።
ፓርቲ ለማለት እኔ አልደፈርም ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲን ሥነ - ምግባር
አሟልቶ የተደራጀ፤ ብረት መዝጊያ የሆነ የማይበገሩ ዲስፕሊን፤ የሞራል
ልዕልና ያላቸው አባላት ያሉት ድርጅት የለምና። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ
የጽዋ ማህበር አይደለም። በግለሰቦች ላይም የተንጠለጠለ አይደለም።
የሆነ ሆኖ የዛሬ ጉዳዬ ይሄ አይደለም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት አመሰራረት
እና ሂደት ንፋስ ገብ ድንገቴ ስለመሆኑ ጉዳዬ አብክሬ ማንሳት እሻለሁኝ። የኢሳቱ
ጋዜጠኛ አቶ ሲሳይ አጌና ከፕ/አሻግሬ ይግለጡ ጋር በነበረው ተከተታይ ውይይት
በርካታ ልባም ነገሮች ተነሰተዋል።
ፕ/አሻግሬ ይግለጡ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ
ጠዬቁ፤ የመደመር ፍልስፍናንም ፈቀዱት!
24.01.2019
አንዱ የኢህአዴግ አመሰራረት ነበር። የኢትዮጵያ መከራ አህዱ ያለበት
ጥላሸት ዋዜማ። ሰው አላስተዋለውም እንጂ ትልቅ ብሥራት ነበረው።
ሮም ላይ በነበረው ውይይት … አወያዩ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ሲያነሱ ጮሌው
ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጣልቃ ገብተው መልስ የሰጡበት አግባብ ትግራይን
ነፃ አወጣለሁ ብሎ ለተነሳ አንድ የነፃ አውጪ የዞግ ድርጅት ለመልሱ
አቅሙ የማይመጥን ስለመሆኑ አመላካች ነበር።
ብሄራዊነት ሆነ ኢትዮጵያዊነትን የተፋቀበት ድርጅት፤ እንጥፍጣፊ የሌለው
ድርጅት ያን የቡና ፖለቲካ በባለቤትነት መመለስ እና መጪውን የድርድሩን
ውሳኔ ዝንባሌ ለመበወዝ የተገደደበት ለድሉም ለዲሉም ዋና ተርኒግ
ፖይንት ነበር።
የኢህአዴግ ጽንሰ ሃሳብ ከቡና ፖለቲካ ጋር ነበር የመጣው።
የዚህ ለውጥ የመንፈስ ቅልበሳም የሐምሌው ዝምታ የቡና ፖለቲካ ነበር።
በዚህ ዙሪያ ሀምሌንም ነሀሴም ባጅቼበታለሁኝ።
ብልጡ ህወሃት እሳቸው ፕ/ አሻግሬ ይግለጡ ብለጠትን የማጭበርብር የመጀመሪያ
ደረጃ ነው ያሉት ለዚህም አመሰግናቸዋለሁኝ፤ ከዛ በኋዋላ ነው ረጅም ቀጠሮ ወሰደው ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በግጥምጥሞሽ ኢህአዴግ የሚባል ግንባር እንደፈጠሩና እና
ድርድሩ ከእሱ ጋር ስለመሆኑ የተገለጠው። ልክ እንደ ጣናው ኬኛ ድባብ።
ከህወሃት መሪነት ወደ ኦህዴድ መሪነት እንደተሸጋገረው ማለት ነው።
የታሪክ ሂደቱ በጣም ተወራራሽነት አለው። አሁን የዛን የቡናውን ፖለቲካ
የኢህዴግ ፈጣሪ ትርክት በዚህ እኔ እንደማስበው ኢዴፓ /ኢትዮጵያ
ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ አድርጎ ለማውጣት እሳቤው የአንዱን ታሪክ ገድሎ
ሌላ ታሪክ የመጀመር ሂደት ነው። ለዜግነት ቢታሰብ ከጋዜጠኛ እስክንድር
ነጋ ጋር ጦር የሚያማዝዝ ምንም ነገር የለውም። „ባልደራስን አላምንበትም“
አይገባም ለቀደምት የህብረ ብሄር ፓርቲ አውራዎችም ቢሆን።
ለዜግነት ቢታሰብ ቦታውን ሁሉ በአንድ ዞግ ለሞሙላት መደበኛ ተግባር
ባልሆነ ነበር። ለዜግነት ቢታስብ አዲስ የዴሞግራፊ ምህንድስና ባልታቀደ
ነበር ለዛውም ለርዕሰ መዲና ላይ፤ ለዜግነት ቢታሰብ ህግ ተሽሮ፤ አዲስ ህግ ወጥቶ
ከንቲና ባልተሾመ ነበር። በዜግነት ውስጥ የሌለ አውራ ድርጅት ከነዝልቦው ወጥ
ድርጅትን ይፍጠር ብሎ ማሰብ በራሱ የፖለቲካ ትንታኔ አቅማችን ልፍስፍስፍነትን ያሳያል። ተፈጥሮው አይፈቅድም። መንፈሱ የዜግነት የለም።
ወደ ቀደመው የህወሃት ህልም ስንሄድ ከትግራይ ነፃ አውጭነት ወደ ብሄራዊ ገዢነት የተወጣበት በዛች እምርታዊ ነጥብ ህወሃት ከትግራይ ነፃ አውጭነት ወደ ብሄራዊ ተደራዳሪነት በቅጽበት ሁኔታ ተለውጦ ዲል እና ድል ተንዶልዱለው ይህን ያህል
ዓመት ገዙ። ያ የቡና ፖለቲካ ለዲልም ለድልም አበቃቸው።
ዓመት ገዙ። ያ የቡና ፖለቲካ ለዲልም ለድልም አበቃቸው።
የግንባሩ አመሰራረቱ ግን ገብያ ሄዶ እቃ ገዝቶ በዘንቢል ሰባስቦ የመምጣት
ያህል ነበር። የሚያሳዝነው ይህን ግጥምጥሞሽ የሚመከት ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/
ተቀናቃኝ ድርጅት በ28 ዓመት ሙሉ ለመፍጠር አቅመ ቢስ መሆናቸው ነው
የፖለቲካ ሊሂቃኑ በሙሉ። እከሌ ተከሌ ሳይባል።
እኔ እንዲያውም ኢህአዴግ እድለኛ ነው ባይ ነኝ። በአንድ አደራዳሪ የውጭ ዜጋ
አስተያዬት በሌላ ብልጥ መልስ አሰጣጥ የተወለደው ኢህዴግ ይህን ያህል ዘመን
በተለያዩ ቨርዥኖች ልማታዊ፤ ጥልቅ ተሃድሶ፤ ከፍታ ወዘተ እያለ መቀጠሉ
በውነቱ ዲል ያለ ድል ነበር። እስከ ‚ጣና ኬኛ‘ የብልጠት ፍልስፍና ድረስ።
እንደ ፓርቲ ይሁን እንደ ግንባር አመሰራረት ታስቦበት፤ ዓላማ ኑሮት፤ አይዲኦሎጂ
ኑሮት አልነበረም ኢህአዴግ የተመሰረተው እንደ እውቁ እርጉ የፖለቲካ ሊሂቅ እንደ
ፕ/ አሻግሬ ይግለጡ ትንታኔ እኔ እንደተረጎምኩት። እኔም ከውስጤ አዳምጬ
እንደገባኝ።
በሄሮድስ መለስ ዜናዊ ቅጽበታዊ እምርታዊ ግንዛቤ የተፈጠረ ድርጅት ነው ኢህዴግ
ማለት። ያ ኢትዮጵያ የቡና ቀደምት ባለታሪክነቷ ለትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት
አንገዋሎ ወንዝ ዳር አሽቀንጥሮ ነበር የጣለው። አንደበቱም እስር ነው የነበረው።
እና መልሱም የግንባሩ ግምጥሞሽም እንደ ደራሽ ፈረሰኛ ውሃ ሙላት ከላይ
የተዶለ ነው። ይህም ሆኖ ይህን ያህል አመት ቀዳደውን እዬወታተፈ፤ እንደ ሰነፍ
ቡሆ እቃ የተዝረከረከውን እዬጠራረገ በጉልቤ በህወሃት የማንፌስቶ አንጡራ
መንፈስ እዚህ ደርሷል።
የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ገድለኝነትም ሊታይ የሚገባው ከዚህ
አንፃር ነው። መሰረቱ የኢህዴግ የትግራይ ነፃ አውጭነትን በውስጡ አምቆ ግን
ብሄራዊ ካባ ተላብሶ ስለነበር ያ ተጋድሎ አናቱን አስኳሉን አናጋው። ለዚህም
ነው ለውጤት የበቃው።
የህወሃት ስልጣን መሰረቱን ያጣበት መሰረታዊ አመክንዮ ይኸው ነው። ይህንን
አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ፤ አንድም የፖለቲካ ተንታኝ፤ አንድም እኔ ነኝ ያለ
ጋዜጠኛ አይደፍረውም። ስለምን ስትሉ አማራ የሰራው ገድል ስለሆነ።
ቅርፍራፊው፤ ሽርፍራፊው ላይ ነው የሚያተኩሩት።
አሁን ኦዴፓ ነፍሱ እስኪጠፋ ቄሮን ዘውድ የሚደፋለት፤ ኦነግን በሎጅስቲክስ
ድጋፋ ንጠቱን እንዲያጠናከር የሚያደርግበት ከጠ/ሚር አብይ አህመድ
ሹመት ማግስት ም/ ጠ/ሚር ደመቀ መኮነን ራሳቸውን ስተው „ቄሮ ጀግና“
ያሉበት ፍልጥ ፍልስፍና ሁሉ የዛ ኢንፈረሪቲ ኮንፕሊክስ የፈጠረው መከራ ነው።
የሰሞናቱ የአቶ ለማ መገርሳ ዲስኩርም ከሞት አዳናችሁ ትርክትም ይኸው ነው።
ይህን አይዋ ብአዴን እንደለመደበት ለሽ ብሎ ታሪኩን አሳልፎ ይሸኛል። የሥልጣኑም
ይሁን ተብሎ ጠርዝ ላይ ወድቆ እዬተጠቀጠቀ፤ እመራዋለሁ በሚለው ህዝብ የደም
ታሪክ ላይም ጭምርም ትራሱን ከፍ አድርጎ ይደራደራል?
ጭራሽ ቄሮ መንፈሱ አዲስ አባባ ሊሰጥ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ የሚያስቆምበት፤ ገስግሶ መጥቶ ስብሰባ እንዲያግድ የሚያደርገበት ምክንያት የተፈጠረውም ከዚህ
አንጻር ነው።
የገዘፈ፤ የማይጨበጥ፤ የማይዳሰስ ረቂቅ መንፈስ አድርጎ አንድ የአገር መንግሥት
ስንት አለም አቀፍ ድርጅቶች፤ ስንት ዲፕሎማቶች ባሉበት አገር እቃ እቃ ሲጫወት
ባሊህ ባይ አላገኝም። ግንባሩ ሊወያይበት የሚገባው አመክንዮ ይህ ሊሆን ይገባል።
108 ሥልጣኑን ሲሰጡ ለቄሮ ንግሥና ስለመሆኑ መልስ ሊያገኙበት ይገባል።
በውነቱ ይህን ሳስብ ኢትዮጵያ ሰው የነጠፋበት አገር ስለመሆኗ እዝናለሁኝ።
የጎረምሳ ስብሰብ ፌድራልን ጥሶ ይህን ያህል አቅም፤ ጉልበት፤ እወቅና እንዳለው
አድርጎ ማውጣት ቁልጭ ያለ አናርኪዝም ነው። አናርኪዝም በህግ ተደግፎ
አገር ሲመራ ደግሞ የሁሉም መሞከሪያ የሆነችው አላዛሯ ኢትዮጵያ
የመጀመሪያ ናት።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ የወታደሮች ኩዴታ ላይ መንግሥታችን ተደፈረ ብለው
በአዲስ አባባ ዙሪያ ያሉት ወገኖች ሊመጡ ነበር ሲሉን፤ የኦፌኮው አቶ ደጀኔ ጣፋ
ደግሞ በሰዓታት ቄሮን መሰብሰብ እንቻላለን ሲሉን፤ የጠ/ሚር የፕሬስ ሰክሬታርያት
ደግሞ አደጋ ሊደርስ ስለነበር ለደህነነቱ ስንል ነው የባልደራስ ጋዜጣዊ መግለጫ
እንዲቀር ያስደረግነው ሲሉን፤ ኢትዮጵያ የማን? ኢትዮጵያ የት ማለት ልብ
ላለው ዜጋ ወሳኝ የህልውናው ጉዳይ ይሆናል። በዚህ ትርትር፤ በዚህ ዝብርቅርቅ፤
በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ አገር የሚመራ ወጥ ድርጅት ለመፍጠር ማን ታምኖ?
በምን ስሌት ሌላ የታሪክ በለቀ ነው ለእኔ።
ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ የህወሃት መሰረታዊ የመታገያ አርማ „የሽዋ አማራ ትግራይን ጨቁኗል“ ብሎ ነው የተነሳው። ግንባሩም ሲመሰረት በዚህ ፍልስፍና ነው፤
ህገ መንግሥት ፖሊሲም የተረቀቀው በዚህ መንፈስ ነው።
ይህን ተፃሮ የተነሳው ብቸኛው ተጋድሎ የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ
ብቻ ነው። ይህን መንፈስ ገርስሶ ለመጣል ተፈጥሯዊ አቅሙ የሚፈቅደውም
ለዚህው ተጋድሎ ብቻ ይሆናል።
በልኩ፤ በቁመናው፤ በይዘቱ ላይ ያተኮረው ተጋድሎ ዲል ላለ ድል የበቃበት
እውነተኛ አምክንዮ ይሄው ብቻ ነው። ይህን መሞገት የሚፈለግ ይምጣ እና
እኔን ይሞግተኝ። ህወሃትን ማንፌስቶ የገረሰሰው የአማራ የህልውና ተጋድሎ
እንጂ ሌላ ማንም ምንም ሃይል አይደለም። ስለምን? የሌላው ተፈጥሮው
ስለማይፈቅድ። ኦሮሞ ጨቆነኝ ብሎ አይደለም የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት የተመሠረተው።
የአሁኑ የጥገናዊ ለውጡ ውጥንቅጥ መከራም ይኸው ነው። ለውጡን
ያስገኘውን መሰረታዊ አንኳር አመክንዮ ስቶ በሌላ መንገድ መጪ ስላለ
ጠግኖም፤ ከልሶም፤ አስታሞም ሊሻገር፤ ሊያሻግር አልተቻለውም።
እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በቃልኪዳን ሰነዱ ፍርርም ላይ „ለአንድ ሰፈር
ተብሎ ህገ መንግሥት አይሻሻልም“ ሲሉ መወደቃቸውን ያበሰሩበት ታላቁ ቀን
ያ ነበር። ምክንያቱም ህውሃትን ከአናቱ ከመሰረታዊ ዶግማው የነቀለው የዛ የጎንደር
ጎጃም የአማራ የህልውና አብዮት ስለመሆኑ አመክንዮዊ ወሳኝ አቅምን ነበር
የተረገጡት።
እንዲያውም እኔ ለውጡ የተገኘበትን፤ እሳቸው ጠ/ሚር የሆኑበትን አመክንዮ
ራሱ የገባቸው አለመሆኑን ተረድቸቤታለሁኝ። ፖለቲካዊ ነፍሱን ገና አላገኙትም።
ወይንም ሆን ብለው ለመጫን ያሴሩበት ጉዳይ ነው። ለነገሩ ልባቸው ምድር ነው።
ህወሃት በስልጣኑ ለማቆዬት በሁሉም መስክ ማንፌስቶው ገዢ ሆኖ መውጣት
ነበረበት? አሁን አለ … ማለት አይቻልም። እውነቱ ይሄ ነው። የአማራን ተጋድሎ ከመነሻው ተቃውመው ነው የተነሱት ጠ/ሚር አብይ አህመድ። እኔም ግንቦት ላይ ሞግቻቸዋለሁኝ። እርግጥ ነው ጎንደር ሲሄዱ በአፍ ወለምታ ብለው አለባሶ
ሠርተውበታል። ግን እሳቸው ስንት ሰው ናቸው?
አንድ ህመም ፈውስ የሚያገኘው በአንቲፔን አይደለም። አንቲፔን ህመሙን
ለጊዜያዊነት አስታጋሽ ብቻ ነው። የህመሙ ፈውስ በትክከለኛው መዳህኒት
ብቻ ነው። ኢንፌክሽን በአስፕሪን ሳይሆን በአንቲባይወቲክ ነው መፈወስ
የሚችለው። ለዛውም አንድም ቀን ሳይዛነፍ ከተወሰደ ብቻ ነው ፈውስ
የሚገኘው። ለለውጡ ኢንፌክሽን ነው የፈጠሩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
ያን አክማለሁ ብለው የሄዱበት መንገድ ራሱ አደብ ስለጣ አቅም አጣ
ወይንም ሳሳ። ግማሽ ሹርባ አገር ነው አሁን እዬመሩ ያሉት።
እሳቸው ኢንፌክሽኑን ደግሞ በአስፕሪን ለማስታገስ ነው ያሰቡት። አልጋባቸውም
ለውጡ እንዴት እንደመጣ። ማስተር ፕላን ሳቢያ ነው። የህወሃትን ማንፌሰቶ ከስር የሚነቀል አይደለም- አልነበረምም። ይህ ችግር የሳቸው ብቻ ሳይሆን በ2008 የነበሩ የሊሂቃን ውይይትም መከራ ነበር። እንዲያውም እኔ አንቀጽ 17 የውጫሌ ውል ሳቢያ ነበርን? ብዬ ሁሉ ሞግቻለሁኝ።
ይባስ ብለው የአማራን የህልውና ታገድሎ ማንፌስቶው ላልሆነ ድርጅት
የሸለሙበት ፖለቲካዊ ብወዛ በራሱ ሴት ሆኖ ተፈጥሮ ወንድ የመሆን፤
ወንድ ሆኖ ተፈጥሮ ሴት የመሆን የሆርሞን ለውጥ አብዮት ነው ያካሄዱት።
ግንቦት 7 አቅም የለውም የአማራ የህልውና የማንነት ጥያቄ የመሸከም።
ተፈጥሮው አይደለም።
ይህን ስንመለከተው የጭንቅላት ካንስር ለላበት ሰው የኮሶ ቁርጠት መዳህኒት
የመስጠት ያህል ነበር። በዚህም ወድቋል የጠ/ሚር አብይ የአመራር ልቅና።
ይባስ ብለው የአማራ የህልውና ተጋድሎን ለመጫን ዓመቱን ሙሉ ሲያካሂዱት
የባጁት የፖለቲካ ጫና በራሱ የአማራ የህልውና አብዮት ተፈጥሯዊ ባህሪን በስልት፤
በሴራ ፖለቲካ ለማዳፈን እና የህውሃትን ማንፌስቶ ዳግሚያ ተንሳኤ የማወጅ
ያህል ነው እኔ እማስበው። ሳያውቁት ራሳቸውንም ገዝግዘውታል።
ለዚህም ነው አሁን ወደ ቀደመው ባህላችን እንመለስ የህወሃት አውራ ጥያቄ ሆኖ
የወጣው። ይህኑኑ ሲያበረታቱ ነው የባጁት ጠ/ሚሩ ሆነ ድርጅታቸው ኦዴፓ።
ሌሎችም ቢሆን መሰረታዊ የለውጥ ሞቶውን ትተው ቅርጥምጣሚ ሲለቃቅሙ
እና ያን ሲያክሙ ነበር የባጁት። የተጋሩ ሊሂቃን፤ ህወሃት ሌሎችም ድርጅቶች ግን ጠንቅቀው ያውቁታል። ማን ነቅሎ እንደጣላቸው። ለዚህ ነው አማራ ከአንደበታቸው የማይወጣው። ብአዴን ጡጧቸው የሆነው።
አሁን የኢህዴግ ወደ ወጥ ፓርቲነት የመሸጋገር ሁኔታም አንቲፔን እንጂ ፈዋሽ
መዳህኒት ነው ብዬ አላምንበትም። ስለምን ብትሉኝ የጠ/ሚር አብይ አህመድ
መንፈስ በመሰረታዊ የኢትዮጵያ ችግር ላይ ግልጽ አቋም እሳቸውም
ድርጅታቸውም የላቸውምና።
የህወሃት ማንፌስቶ መሰረታዊ ነፍስ የብሄር ጭቆና አለ፤ ጨቋኙ የሸዋ አማራ ነው።
ህገ መንግሥቱ፤ የቋንቋ ፌድራሊዝም ምንጫቸው የህውሃት ማንፌስቶ ነው።
ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት የህውሃት ማንፌስቶ ደግሞ የብሄር ጭቆና ነበር ጨቋኙም
የሽዋ አማራ ነው ብሎ የሚነሳው። የኢህአዴግ ነፍስ ያለው ከዚህ ላይ ነው።
እነሱ „በቋንቋ ፌድራሊዚም አንደራደርም፤ ለአንድ ሰፈር ተብሎ ህገ መንግሥት አይቀዬርም“ ሲሉ የህወሃት ማንፌስቶ ይግዛን ይንዳን ግን ስልጣኑን በኦሮሞ ይተካ ስለመሆኑ ደጋፊውም፤ አሽቃባጩም አልተረዳውም።
ለዚህ ለነፈዘ ጉዞ ነው አቅም እናዋጣ የሚባለው። ይህን መንፈስ ተሸክሞ ወጥ ፓርቲ መመሰረት አብሶ ለብአዴን ቢሞት ይሻለዋል። ራሱን ጨቋኝ አድርጎ፤ ራሱን ለማጥፋት እንደለመደበት ይኳትናል ማለት ነው። አንዱ አቅሙ ደክሞ ሲሸኝ፤ ሌላው ባለ አቅም በአዲስ ጉልበት ደግሞ በተራው ቼ በለው ይላል ማለት ነው። ሌላው ቀርቶ ገዱንም ደመቀንም ሸኝተው አቶ ታከለን ኡማን የለውጥ ሐዋርያ አድርገው ሲወጡ ግድ አይሰጠውም ብአዴን።
ለውጥ ስለሚበላው ምንድን ነው የሆነው የተጋሩ ባልስልጣናት በኦሮማማ ተተኩ።
በቃ!ይህ ይመቸኛል ነው የሚለው ማለት ነው ብአዴን በኦደፓ አውራነት ስለሚመሰረተው ወጥ ፓርቲ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ አቋም ሳይሰናዳ በመንፈስ
እንኳን ኢትዮጵያዊነትን የሚመራው አካል ሳያምንበት የዳማ ጨዋታ ነው
ለእኔ ውህደቱ ሆነ ወጥ ፓርቲ ጥንስሱ።
በቃ!ይህ ይመቸኛል ነው የሚለው ማለት ነው ብአዴን በኦደፓ አውራነት ስለሚመሰረተው ወጥ ፓርቲ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ አቋም ሳይሰናዳ በመንፈስ
እንኳን ኢትዮጵያዊነትን የሚመራው አካል ሳያምንበት የዳማ ጨዋታ ነው
ለእኔ ውህደቱ ሆነ ወጥ ፓርቲ ጥንስሱ።
የአማራ፤ ኦሮሞ፤ ጋንቤላ፤ ቤንሻንጉል፤ ሱማሌ፤ ድሬ፤ ትግሬ፤ አፋር ክልል
እያልክ የአማራ፤ የኦሮሞ፤ የአፋር፤ የትግሬ፤ የሱማሌ፤ ድሬ፤ ጋንቤላ ጉምዝ ፓርቲ
ብሎ ድርጅት የለም ከእንግዲህ ማለት አይቻልም።
ማረፊያ የለውም ሎጅኩ። ስሜት እኮ ድርጅት አይሆንም ወይንም ስኬት
አይሆንም። በመፈለግ እና በማግኘት ውስጥ የሂደትም፤ የአቅምም፤
የማህበራዊ ንቃተ ህሊናም አቅም ያስፈልጋል።
27 ዓመት ሙሉ ያልነበርክበትን ዜግነት በምሽት ድለቃ እና በኮክቴል መሰናዶ
መውለድ አይቻልም። አንድ ሙሉ ትውልድ እድሜ አሳልፏልና።
በነገራችን ከሰሞኑ ደግሞ የወላይታ ድርጅት ተመስርቷል። ግንቦት 7 አገር ከገባ
ሦስተኛው መሆኑ ነው። የጉራጌ፤ የጋሞ፤ የወላይታ። ወንድ ከሆኑ አብን በጥርሳቸው
የያዙት የግንቦት 7 ጋዜጠኞች አቶ ወንድም ልጅ ፋሲል የኔአለም እና እና አቶ ካሳሁን
ይልማ እስኪ ይህን ይሞግቱት እና ይርቱት። ያስቁሙትም አቅሙ ካላቸው።
ሌላው በዚህ የወጥ ፓርቲ ደንብ፤ ፕሮግራም፤ ፖሊሲም የአንድ ድርጅት ለዛውም
የኦነግን መንፈስ ያነገበው ያረቀዋል ስለሚባለው መንፈስ ሳስብ ጭጋግ ነው
የሚታዬኝ።
አንድ የአገር መሪ ድርጅት ሲመሰርት ወይንም ሲፈጥር የሚዘልቅ መሆን አለበት።
ቤት በተለቀቀ ቁጥር እቃ አዲስ ገዝቶ ዲኮ ማሟላት ነው የሆነው። ድርጅት እኮ
ሰው ነው። ሰው እንደ ጭቃ ተጠፍጥፎ ሸክላ አይሆንም። ሰው ፈጣሪ / አላህ
ባምሳሉ የፈጠረው የእዮር ዜጋ ነው።
የፖለቲካ ፓርቲ የሰው ሰው የሚበጀበት ነው። የነቁት፤ የበሰሉት፤ ሃሳብ ያላቸው፤
ራሳቸውን ለመስጠት የቆረጡ ጀግኖች ነፍስ ውህደት እንጂ የእቁብ እድር ተልዕኮ
የለውም። ከሁሉም እኔ ሊሂቅ ከሚበለው ዘመኑን የመጠነ የፖለቲካ አቋም ያዬሁት ከ21ኛው ምዕተ ዓመት ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ እናም የኢትዮጵያ ችግር "አማራ ጨቋኝ" ትርክትን መልክ የያዘው የጠራ እና የጸዳ አቋም ያዬሁት በአቶ ሙስጦፋ ኡመር መንፈስ ውስጥ ነው። ብቻ ለድህንነታቸው ይጨንቀኛል። የህወሃትን ትርክት የኦነግን ትርክት ተሸክመህ ወጥ ፓርቲ ተረት ነው … ውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት።
ለሳቸውም ነፍስ እሳሳለሁኝ ስል ቆሞስ ስመኘው በቀለ፤ ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው የተገበሩበት ይህ የሃቅ እትብት ነውና። አንድ ጥርት ያለ ነገር አሁን ከሆነ እኔ
የታዘብኩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ዴሞክራት ነኝ ይበሉ እንጂ ጠረኑ የላቸውም። የሚበልጣቸውን ሰው፤ የሚሞግታቸውን ነፍስ አይሹም። እሺታን ነው ሁልጊዜ የሚፈልጉት እንጂ አይ የሚላቸው አንጡራ ጠላታቸው ነው። ያሳድዱታልም።
በዚህ ውስጥ ዴሞክራሲ ኢትዮጵያን እኔ አላስባትም … ፈተናውን ወድቀዋልና።
አንድ መሪ ከእኔ የሚሻል፤ የሚበልጥ አቅም አለ እኔ አጋጣሚ ነው የሰጠኝ
ብሎ ማመን አለበት እንጂ ከሰማዬ ሰማያት የወርድኩኝ ባለክንፍ ነኝ ካለ
ዶከከ ራዕዩ …
በሌላ በኩል ድርጅት እንዲህ በሳቢያዎች፤ በገጠመኞች፤ በወጀብ፤ ወይንም በገፊ ምክንያቶች ብቻ ተንጠልጥሎ ከሆነ ትውልድ ከማባከን ውጪ ትርፍ የለውም።
በመጀመሪያ የለውጡ መሪ ሆነው አሁን ላይ የወጡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን አሸቀንጠረው አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶር አብይ አህመድ፤ ኢንጂነር ታከለ ኡማ
ሆነው እያዬን ነው። ይህን እንኳን ለሚያስተውለው ነገ ክው ብሎ ደርቆ ስለመምጣቱ ነጋሪት ይጎስማል መለከት ይነፋል …
መጀመሪያ እነሱ ከዞጋዊ በሽታ ይዳኑ። ለዞገኝነት ቢክተም ናቸው። የአንቦ
ፕሮጀክት በዝግ ስብሰባ ሲካሄድ በምን ሁኔታ እንደተከወነ ስለምን እንደሆነ
እንዴትና እንዴት እንደነበረ የውሽማ ሞት ነው። በዚህ መንፈስ ውስጥ
ብሄራዊነትን ለማስብ ዳገት ነው።
የአንድ አገር ርዕሰ መዲና የህዝብ ስብጥር ብዋዛዊ ለውጥ ለማድረግ
እዬተጋህ ወጥ አገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለማምጣትም ዳገት ነው። ረግረግ ነው።
ጨቀጨቅ ነው።
„የጌዴኦ እናት እውን እኛ ኢትዮጵያዊ ነን“ ብላ ስትጠይቅ አውራው ድርጅት
ኦዴፓ ዜግነትህ ምንድነው? አንተ ማነህ? ስለማን ነው የምትሠራው? ስለማንስ
ነው የነገስከው እያለች ስለመሆኑ ለወጡ ፓርቲ ምሰረታ ሃሳብ ታላቅ መልዕክት
ነው።
ስለምንፈልገው ነገር መሆን በምንችለው ልክ መሆን አለበት። በመፈለግ ውስጥ የሌለ እኔነት እኛነትን አዋላጅ ሊሆን
አይችልም።
አንድ እውነት አለ ተዚህ ላይ የብሄር ጭቆና አልነበረም ማለቱ ኦህዴድ እና ኢትዮጵያዊነትን የአይዲኦሎጂው አስኳል ለማድረግ የሄደበት ጉዞ ክብር፤ ፍቅር፤ ተቀባይነትን አሸልሟል። ያ ግን ላስተዋለው ሰው የትውስት ነበር። „የተውሶ ይሄዳል ተመልሶ“ ነው የሆነው አሁን።
ሆን ያሉትን ቀበቶ ሲያወልቁት የተዋሱትን የቅቡልነት
ክብርንም አጡ።
ማስተባባያው አሁን የፕሮፖጋንዳ ስንቅ ነው። እነሱን በሚዲያ ተቀስቅሶላቸው
አልነበረም፤ ያከበርናቸው ለዛውም ህወሃት ከነግርማው በነበረበት ወቅት ነው
ያን አስፈሪ ድርጅት ተደፍሮ የእነሱ ሰብዕናን በድፈረት የገነባነው።
ያን ያደረገላቸው ያልሆኑት ሆን ብለው ስላባጨሉን ነበር። ስለዋሹን። ክንብንቡ
ሲወልቅ ደግሞ ወደ ነበረበት ሙቀቱ ተመለሰ ሁለመናው። የተሰጠው ክብር፤
ፍቅር፤ ልቅና ጸድቆ ሰክኖ ሊሰርጽ አልቻለም። የሰጠውን መልሶ ወሰደው ቅኑ
የኢትዮጵያ ህዝብ እኔንም ጨምሮ።
አሁን ያሉት ሦስቱም በሚዲያ ጉልበት ነው። የሰሞናቱን የአስኮባ ሰርግና መልስ
ሳይ እስቅ ነበር። ሞጋች የሆኑት ነፍሶች ብዕሮች፤ ሚዲያዎች አማላጅ እዬተለከ፤ እዬተገፉም አቁሙ እዬተባለ መሆኑን እናስተውላለን። እልፍኝ አስከልካዩ ዛሬ
ላይ ግንቦት 7 ነው …
... እንጂ ነፍሱ የለችም ያ የምዕልእት ንጹሁ፤ ፃድቅ ፍቅር … ደግሞም አትገኘም …
ህወሃትን የሚደቃ ይፈለጋል፤ አብይወለማን የሚነካ ደግሞ እንደተለመደው የማርያም
ጠላት ነው። ብልህነት ብስለት ተዚህ አንጻር ነው የሚለካው። ህወሃት የተሞገተበት
አቅም ዛሬ መቅኖው ፈሶ የሰው ሁሉ ትጥቅ ፈቺ ሆኗል። እውነት ጥግ አጥታ ኤሉሄ ትላለች!
አቅም ዛሬ መቅኖው ፈሶ የሰው ሁሉ ትጥቅ ፈቺ ሆኗል። እውነት ጥግ አጥታ ኤሉሄ ትላለች!
መፍትሄ ከችግሩ መነሻ መነሳት አለበት። ኢትዮጵያዊነት በግጥምጥሞሽ በወጀብ
በአውሎ በጦሮ አስገዳጅነት አይደለም ሊፈጠር ሊመጣ የሚገባው።
ኢትዮጵያዊነት ስክነት ነው። በዘር አባዜ እዬዘለሉ፤ እዬፈረጡ ኢትዮጵያዊነት
ለማምጣት ማስብ ባይታሰብ ይሻላል። ቁጭ ብሎ የፊደል ገበታ ገዝቶ መማር
ያስፈልጋል ኢትዮጵያዊነትን። ኢትዮጵያዊነት የነጠረ ረቂቅ ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያዊነት ሳይንስን የፈጠረ ማንነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከሚኒሊክ በመለስ አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ጠፈርንም
ያካታል። የዛሬው የሊቀ ሊቃውንታት መሰረት የሆኑ የህውሃ ሳይንስ መሰረቱ ኢትዮጵያዊነት ነው። ናሳን መጎብኝት ነው።
በኢትዮጵያዊነት ልክ፣ መጠን፣ ይዘት፣ ውስጥ፣ ቀለም ውስጥ ሆኖ ነው ኢትዮጵያዊ
ድርጅት የሚፈጠረው። ታሪክ ሽሚያ ላይ የሚገኘው ኦዴፓ ጅሉን ብአዴንን
አዴፓ ብሎ ቅጥል ስም ሸልሞ እንደ ቀለደበት ሌሎችንም ኢዴፓ ብሎ ታሪክ
ሠራሁ፤ ኢትዮጵያን ሠራሁዋት ለማለት ደፋር ስለሆነ የሚጠበቅ ነው።
ታሪክ እንዲህ በግፋፎ ቅርጥምጣሚ አይገነባም። እርጋታን ይጠይቃል።
ማድመጥን ይጠይቃል። ልክን ማወቅን ይጠይቃል። ታሪክ ጥድፊያ አይደለም።
ማስተዋልን ይጠቃል። ሴራ ታሪክን አይሰራም። ቢሰራም አይበረክትም። ታሪክ
ራሱን የመሥራት አቅም አለው። ያ ደግሞ ለተሰጠው ብቻ ነው …
ተፈጥሮን ፈጣሪ ፈጠረው ማለት፤ ሰውን ፈጣሪ ፈጠረው ማለት፤ ፍጥረታትን
ፈጣሪ ፈጠራቸው ብሎ ዘፍጥረትን መቀበል በዛም ውስጥ ለመኖር መቁረጥ
እና መወሰንን ይጠይቃል። ግን አቶ ለማ መገርሳ ይሁኑ ዶር አብይ አህመድ
በዚህ ውስጥ ናቸውን? ዘር ቆጠራ ነው የተባጀው። ክብር ልዕልና ቦታ ሹመት
ሽልማት እውቅና ላይ ነበር የባጁት ለዘራቸው ደም ቅዳ እና ደም መልስ ሆነው።
በዚህ ስሌት ኢትዮጵያን ያህል ገናና አገር ለመምራት ሆነ በወጥ ፓርቲ ለማደራጃት
እኔ ከጣሊያኑ የህውሃት እና የደርግ ድርድር ቅጽበታዊነት ውጭ አላዬውም። ታሪክ ተንደርዳሪ አይደለም።
ታሪክ በራሱ ተፈጥሮ ሰክኖ የቆመ የአመክንዮ ቋት ነው። ፍቅርን ለመያዝ አቅቶ፤
ፍቅርን ማኔጅ ለማድረግ አቅቶ ስንት ወጣ ገባ ጉዳይ እንደተፈጠረ እያስተዋልን
ነው፤ እንኳንስ አንድ ግዙፍ አገራዊ ብሄራዊ ድርጅት ለመመሰረት።
ጨርቅ፤ ሸሚዝ፤ ቀሚስ፤ ሱሪ በአንድ ሻንጣ ይቻል ይሆናል። አንድ ዝብርቅርቁ
የወጣ ግንባርን ግን ሌላውንም አክሎ ለማዋዋጥ ጥናት ጥንቃቄ አስተውሎት
ይጠይቃል። እስኪ ኦዴፓ ራሱን መሆን ይቻል መጀመሪያ። ድርጅቱን ኢትዮጵያዊ
አደርጎ ይቅረጸው። ቤት ሳይጸዳ መቼም ግቢ አይጸዳም እና።
ድርጅት ሲፈጠር የራሱ ህግ፤ መርህ፤ አስተውሎት፤ ጥናት ይጠይቃል ወቅት እና ሁኔታ ይጠይቃል። እራሱ አሁን ተረቀቁ፤ ተሻሻሉ ስለሚባሉት ህግጋት እኔ እምነት የለኝም። የሚኒሊክ ቤተመንግሥት እድሳትን ጨምሮ። ቅቡል የሆነ መንግሥት እስኪፈጠር ተግ
ማለት ያስፈልጋል። ሽሚያም ጥድፊያም አያስፈልግም፤ ብአዴን ተግ በለ አትሰገር
ሊለው ይገባል ታሪኩንም ልቡንም አውልቆ ለሸለመው ለባልንጀራው ድርጅት
ለኦዴፓ።
ይልቅ የሰባዕዊ መብት ረገጣ የለም ቢለን አቃቢ ህግም የሥነ - ልቦና ወራራው ብቻ
ሳይሆን ሰብዕዊ እርዳታ የሚያደርጉ ነፍሶች ራሱ ችግር ውስጥ እንዳሉ እናውቃለን።
ይህ መንግስት መጀመሪያ ሰው ለመሆን ሰብዕዊነትን ያክብር። ድርጅት የሰዎች
ስብስብ እንጂ የሸቀጦች፤ ወይንም የፕሮፖጋንዳ ማህበር አይደለምና።
ጥድፊያው ለምን እንደሆነ እኔ አውቃለሁኝ። ፈርሰናል፤ የለንም፤ ደግሞ እንደገና
አለን፤ ደግሞ ከሌሎች አጋሮቻችን ጋር ውህደት ለመፈጸም መንገድ ጀምረናል
የሚሉ ሀሳበ ቢስ ድርጅቶችን አካታች አድርጎ ለመዝለቅ ነው። ያው ግንቦት 7
የተጠጋው ነገር ሁሉ በረከት የለውም። አማካሪው እሱ ስለመሆኑ ተነግሮናል።
አሁን ላይ ሃሳቡ ድጋፍ ሊያስገኝለት ይችል ይሆናል መቋጠሪያ አልቦሽ ለሆነው
ድርጅት ጃንጥላ ስለሚሆን። ግን ዳጥ እና ምጥ ነው። ለዛውም ገርባባ …
ይህን መሰል የድንገቴ እቃ እቃ ጨዋታ ትውልድን አባክኗል፤ አክስሏል። ለአንድ
ስኬት እርሙ ለሆነ መንፈስ ብሎ የግብር ይውጣ ተግባር ለመከወን ከመትጋት
ስክነትን መዋጥ ያስፈልጋል። "ዓዋጅ! ዓዋጅ! የዞግ ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ ቀርቷል"
ቢባል ህሊና በቅጡ በጭብጥ እውነታዊ የእኩልነት አመክንዮ ካልተዋዋጠ ነጥሮ
ነው የሚመለሰው። በተወሰኑ ጊዚያት ያው የድብሽት ቤት ተረኝነቱ አይቀሬ ይሆናል።
በተነቃነቀ ቁጥር የሚናድ፤ የሚፍረከረክ፤ ፈርሶ የሚገጣጠም ተገጣጥሞ
የሚተረተር ወዘተ … ነው ታሪኩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት። አንድ ናሙና
ሰው ማግኘት አይቻልም። ያልተገላበጠ አክሮባት ያልሰራ።
ንፋስ በመጣ ቁጥር እንደ ድመት አራስ ቦታ ሲመደምድ የሚውል የፓርቲ
መሰራች ሊሂቅ ነው ያለው … የሰው ልጅ መለኪያ ስኬት ነው። ኢትዮጵያም
በዬዘመኑ እንደ ጥንቸል መሞከሪያ ጣቢያ ባትሆን መልካም ነው።
ከትናንት ስህተትም መማር ያስፈልጋል። ስኬት እርሙ አማካሪም አወያይም
ሊሆን አይገባም። ስለምን? አብነት ሊሆን ስለማይችል። ይህ የራስፈረስ
እንደራሴነት ኢትዮጵያን ያህል የወዘተረፈ ችግር ቁልል መፍቻ መንገድ ሊሆንም
አይገባም።
ያልፈረሰ፤ ያልተናደ፤ ያልተነቃነቀ፤ የልተሰነጣጠረ፤ ያልተገለባባጠ፤ መልሶ
ያልገጠም፤ አንድም ለአብነት የሚሆን የፖለቲካ ድርጅት ልምድ ኢትዮጵያ
የላትም። ስለምን? ወጀብ ከተል ስለሆነ …
የዞግ አጅንዳህን ተሸክመህ አይዲኦሎጂያዊ አንድነት አይመጣም … ተፈጥሮው አይፈቅድም፤ ባገኘኸው ሁሉ አማራን እያሳደድክም አይሆንም። ኢትዮጵያዊነትን መሸከም የተሳናቸው አቶ ለማ መገርሳ ሆኖ ዶር አብይ አህመድ ችግሩ ይኸው ነው።
ቀን ይሆኑበታል ማታ ሲክዱት ያመሻሉ …
እንዴት ነው ሰሞኑን ደግሞ የሜጫ ሱናሜ ውጭ ጉዳይን ሊያጥለቀልቀው እንደሆን ተደምጧል። እነ ዶር ብርሃነመሰቀል አበበ ደግሞ ... እንጠብቃለን።
የሆነ ሆኖ ያ የሚሊዮን ደጋፊው አንድ ዓመት በዝልቀት ሊቀጥል ያልቻለው
ስግረቱ እውነት አልባ ስለነበር ነው። የፈለገ የሴራ ፖለቲካ ቢኖርበትም መዝለቅ የሚቻለው በመሆን ውስጥ ባለ እውነት ብቻ ነው። እውነትን ሸፍጠህ እውነት
መሆን ከቶም አያቻልም።
ለእኔ አሁን የታሰበው የጥድፊያ ውህደት ሃሳብ የለሽ የሆኑ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/
ተቃዋሚ ድርጅቶችን አካታች አድርጎ እፎይታ ለማግኘት ነው ጥድፊያው። አይበረክትምም። ፍቅር በፍቅርነቱን አንድ ሆቴል ተከራይቶ ሃኒሙኑን ማስነካት
እንጂ ሚሊዮንን የመሞከሪያ ጣቢያ ማድረግ የተገባ አይደለም።
እንጂ ሚሊዮንን የመሞከሪያ ጣቢያ ማድረግ የተገባ አይደለም።
አይጥ እና ድመት ሆነህ እዬተጠባበቅህ ውህደት ማላገጥ ነው …
ለመሆኑ አንዱ አሰናድቶት የቆዬውን ምግብ ይሁን መጠጥ ሌላው አምኖ
ይጠጣዋልን? ይመገባዋልን? ከትንሹ እንነሳ ብዬ ነው። መተማመን የለም።
የጓዳው ነገር ይባዛል ከይፋዊው ቲም ወርክ።
ድርጅት ቲም ወርክ ነው።
ከሁሉ በላይ ቅንነት ይፍልጋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅን ሆኖ አያውቅም።
ቅንነት ከሌለ ቲም ወርክ የለም። ቲም ወርክ አልባ ደግሞ ድርጅት የለም።
ዲልታም ድልም ቅንትን ይሻል። በእውነት ውስጥ ለመኖር መፍቀድን ይለምናል።
ድግግሞሽ የአፍ ወለምታ ለማህበርተኛ እንጅ ለመሪነት እእ … መሪ ማለት እኮ
ሊቅ ልሁቅ ከሁሉም የሚበልጥ ሥልጡን አድማጭ ታጋሽ ማለት ነው …
ሌላው ስሜትም መግራትም ሆነ ተጠያቂነትን መቀበል የሙሴነት ምልክት ናቸው።
ህዝብን ከቀስት የማዳን ክህሎት ነው መሪነት። ሞት ላይ ቁጭ ብለህ ድል መቁጠር
ወይንም ስለድል መወደስን ማስነካት በቅኔ ዘጉባኤ ክሰረት ነው። ሰው ዜጋ ነህ
ይባል። ሰው መኖር ትችላለህ የሚለውን ነጻነት ያግኝ። መለኪያ የሰው የሰላም
ልክ ነው።
ራስን መገምገም ይገባል እኔ የወሉ አይደለም የሚመስጠኝ። እያንዳንዱ ቤቱን ዘግቶ ገማናውን ይመርምረው። ንሰሃ ይግባ! ከርባት አስሮ ገበርዲኑን ከሚያስመርቅ ነጋ
ጠባ። ስለ አገር ጉዳይ ከሆነ ውዳሴ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው። ዝቅ ያሉትን
የሚያነሳቸው አምላካቸው ነው። ፕሮፖጋንዲሰት አያሻቸውም ዝቅ ለሚሉት።
ዝቅ ያሉት አጀንዳቸውን ከፍክፍ ብሎ መንበር ላይ ጉልላት የሚያደርግላቸው አምላካቸው ብቻ ነው እንጂ እኔ „ማንም ተራ አክቲቢስት ጋር አልወዳደርም
ተብሎ ታብዮ ያለልክ ተወጣጥሮ፤ ከፍታን ከፈጣሪ ዘንድ ማግኘት አይቻልም።
ወይንም እልፍ እዕላፍ ጠ/ሚኒስተሬ እያለ ያን ከግንባራችሁ ለጥፋችሁ ዙሩልኝ
ማለትም አይሆንም፤ ወይንም "እናንተም መንግሥት ለመሆን ታስባላችሁ" ስላቅ
አለበት፤ "አታስቡት" ስላቅ በሽርዳዳ ቀምመህ ይህም አያስኬድም። "ቤተ መንግሥቱን እንሟሟትበታልን" ብለህ አይሆንም።
አንዲት ቅንጣት ተግባር ሳያይ ራሱን የሰጠህን ነፍስ ክደህ የራስህን አጀንዳ ስትከውን ባጅተህ አትናገሩኝ የሹም ዶሮ ነኝም አይገባም። ወንጀል ለከፍታም ለዝቅታም
ተጠያቂነቱ እኩል ነው። የዲሞግራፊ አጸያፊ ምህንድስና በአለም አቀፍ ህግ
ያስከስሳል … ያስፈርዳል፤ እንደ ክፉ በሸታ ነገር የተከለከለ ገመና ነው። ያን
ዝልቦ መንፈስ መልሰህ ጉልላት አድርገው ራሱ ያሳፍራል። የሰሞኑ መንጎባለል
እና እዩኝ እዬኝ ወይ መዳህኔአለም አባቴ አሰኝቶኛል እኔን።
እኔ አሁን እንደ ጎንደሬነቴ የአማራ እና የቅማንት ገማና እንዴት ውስጤን አቁስሎ
አንገቴን እንዳስደፋኝ ራሴ ነው እማውቀው። አቅደህ ከውነህ ድሌ ብለህ እዬፎከርክ
ድልህ ለአንተ በ21ኛውም ምዕተ ዓመት በሰብዕዊ መብት ጥሰት ህግ ይጠይቃሃል
ሲባል ማስተባበያ ማለገጥ ነው ለእኔ፡፤ ጸጸቱም፤ ሱባኤውም አይችለውምና
ወንጀሉን። ድርቅ ያለ ግረት ይሰበራል። እውነቱን ብናገር ያ እናሻግራችሁአለን
መንፈስ አከርካሪው ተሰብሯል በመንፈስ ደረጃ።
ከረባቱም ገበረዲኑም ንጹህ ፍቅርን በቀጣይነት የማልማት የመሸከም አቅም
የለውም። ነገ ከመምጣቱ በፊት ፍርሃት ላይ ነው። ማግስት ከመምጣቱ በፊት
ራድ ላይ ነው። ይህን ተሸክምህ በዚህ መንፈስ የተቃኜ፤ በዚህ መንፈስ ንጠረ ነገሩ
የሆነ ወጥ ፓርቲ ለእኔ እርግማን ነው። እርምም ነው። ብክል ስለሆነ።
መንፈሱ ጤነኛ አይደለምና።
መብዛትም የሚገኘው ራስን ባሳነሱት ውስጥ ግን በተባው የተግባር ብርሃን
ውስጥ ነው። በማውቅ ውስጥ አለማወቅ፤ በአይ ውስጥ ክብር እንዳለ ማሰብ
ይገባል።
ይገባል።
አይ No“ ልዩ አቅም ነው።
04.03.2018
አይ ትልቅ ጉልበት አቅም ሃይልና ብርታት ነው ላወቀበት። አይን አልቀበልም
ስትል አንተ ከተፈጥሮ አፍንግጠህ ያለህ ጣዖት ነህ ማለት ነው። ጣዖት ደግሞ
ሙት መሬት ላይ ያለ ድውይ ድንጋያማ መንፈስ ነው። ለዲልም ለድልም የማያበቃ ከንቱነት …
ውዶቼ በፅናት ፌስ ቡካችሁ ላይ ትለጥፉልኝ ዘንድ በዘንካታ አክብሮት እና ትህትና እጠይቃችሁ አለሁኝ። አላዛሯ ኢትዮጵያ ዬዘመኑ ዝልቦ የሙከራ ጣቢያ መሆን ስሌለባት።
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ፡፤
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ