እኔን።
እኔን። እባካችሁ ግፍን ፍሩ። እባካችሁን በቀል ይብቃችሁ። ስንት ዘመን ልትኖሩ ይሆን ? ይህ ግፍ ኢትዮጵያን ስንት እርግማን ያመጣባት ይሆን ?? " ፃድቅን መቅጣት፤ ጨዋ ሰውንም በፃድቅነቱ መምታት፦ መልካም አይደለም። " ጠቅላይ ሚር አብይ ፓስተር ናቸው ይባላል። ወሮ ዝናሽ ታያቸው ቀዳማዊ እመቤቷም ዘማሪ ናቸው። በዚህ ግፍ ውስጥ ዘማሪነትስ ሆነ ፓስተርነት በፈጣሪ ዘንድ አገልግሎቱ ተቀባይነት ይኖረው ይሆን ? ሁልጊዜ በተቋማት ግንባታ በትቤት የሚተጉት ቀዳማዊት እመቤት ይህን ግፍ እና ግፍ ህሊናቸው ችሎ ያራምዳቸው ይሆን ? ከቤተሰብስ በዚህ ዕድሜ ያለ አጎት አይኖር ይሆን ? አዛውንቷ ኢትዮጵያስ እንደምን ይከፋት ? ዛሬ ነገ ስንብታችን አናውቀውም። ለፀፀት ይቅርታ ለመጠዬቅ ቀጠሮ አያስፈልገውም። ዛሬውኑ ባለ ዕድል እኒህ አዛውንት አባት ከእስር ተፈተው በክብር ተከብረው እንዲኖሩ ያለስጋት ሊደረግ ይገባል። ውቦች እንዴት አደራችሁልኝ። ደህና ናችሁን ? ኑሩልኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/20 ጊዜ ራዲዮ ነው።