ልጥፎች

ምስል
 
ምስል
 

"ከተማ #አፍርሰን እዬገነባን ነው።" (ዶር የትምጌታ አሥራት ከብልጽግና ፓርቲ።) አስደንጋጭ ክስተት ነው።

ምስል
  "ከተማ #አፍርሰን እዬገነባን ነው።" (ዶር የትምጌታ አሥራት ከብልጽግና ፓርቲ።) አስደንጋጭ ክስተት ነው።    ግን ለምን ከተሞች እንዲፈርሱ #ብልፄው ወሰነባቸው????   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       #የምዕራፍ ፲፰ የማጠናቀቂያ ዕድምታ።   https://www.youtube.com/watch?v=j9HL-v6Akjs «ለሚሊየኖች የቤት ጥያቄ ምላሻችሁ ምንድን ነው? ብልጭልጭ ፕሮጀክት ነው? - የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር በፋና መድረክ « #በቅድሚያ ።   ትናንት ላይፍ ላይ የምርጫ ተፎካካሪወች ክርክር ነበራቸው በፋና ቴሌቪዥን። ተጀምሮ እስኪጨረስ በጥሞና ተከታተልኩት። ትናንት የሰማሁት ግድፈት ይሆን ብዬ ደግሜም አዳመጥኩት። ኢዜማ ባደምጥኩት መድረክ ሁሉ ደረጃውን የጠበቀ ማብራሪያ ሰጥቷል። ብልጽግና አሳካሁ የሚላቸው ነገረ የከተማን #ምህንድስናን በሚመለከት በዩንቨርስቲ ደረጃ ጥናቱ በባለሙያ የተሠራ መሆኑን ሹክ ብለውናል የኢዜማው ርትዑ።   በተረፈ ውይይቱ ጥሩ ነበር። በተለይ መደምደሚያው ላይ በአራቱም ፓርቲወች ሴት ፖለቲከኞች የዕለቱን ውይይት ማሳረጊያ ሲያቀርቡ ትንሽ ኩራት ኩራት ብሎኛል። ሁለቱ ሥማቸው ትዕግሥት ነው።    የሆነ ሆኖ በህይወት እያለሁ የታገልኩበት፤ የሞገትኩበትን ፍሬ ነገር ስላዬሁ እግዚአብሄር አመስግኛለሁኝ። የኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሄ ሴት ጠቅላይ ሚኒስተር ኢትዮጵያ ሲኖራት ነው የሚል ከቀድሞ የቤተ - መጸሐፍት ባልደረባዬ ከወ/ሮ ባርባራ ጋር እንደ ተወያዬሁበትን አስታወስኩት።    ተመድን ጨምሮ ዓለም በሴቶች ብትመራ ገፆዋ ይናፍቀኛል። የሆነ ሆኖ በአራቱም የፖለቲካ ድርጅቶች ሴት የፖለቲካ ሊቃናት እንዲህ በእኩል ...

#ትዕግሥትን ፈታኙ ከመንግሥት ኮምንኬሽን የተሰጠ መግለጫ ትዝብቴ።

ምስል
  #ትዕግሥትን ፈታኙ ከመንግሥት ኮምንኬሽን የተሰጠ መግለጫ ትዝብቴ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።                      #ጠብታ ።   ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ሃሳቤን በምዕራፍ ከፋፍዬ ሳቀርብ ቆይቻለሁኝ። እሳቸው ድፍን ፰ ዓመታትን አሳለፋ፤ እኔ ደግሞ ፲፰ ምዕራፎችን አጠናቀቅኩኝ።   አንድ ሃሳብ ይቀረኛል። ዛሬ ምዕራፍ ፲፰ አጠናቅቃለሁኝ። መጪው ህማማት ነው። ማድመጥ። መጠሞን ያስፈልጋል። ከትንሳኤ በኋላ እንደ አማኑኤል ፈቃድ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አገዛዝ አብይዝም ፱ ዓመቱን አህዱ እንዳለው ሁሉ እኔም ፲፱ ምዕራፌን እጀምራለሁኝ።   ምዕራፍ ፲፰ የጨመተ፤ ያስተዋለ፤ ዘለግ ያሉ ዕይታወቼን ያጋራሁበት። በብሎጌም ከጠበቅኩት በላይ መነበብ የቻለ ጊዜ ነበረው። እርግጥ ነው በህይወት ውስጥ ያሉ ገጠመኞችን ትኩረት ለመስጠት አስቤ፤ ፖለቲካው ጊዜውን እየተሻማ በዛ ዘርፍ ብዙም አልሰራሁም።    ፖለቲካም የህይወት አካል ነውና በአገር ጉዳይ ያገባኛል ብሎ፤ ጉልበቱን፤ ሃሳቡን የሚያጋራ ሰብ የዜግነት ግዴታውን የፈቀደ፤ በመብቱም ያልቀለደ ነው ብዬ አስባለሁኝ።   ዝምታ ውበት ቢሆንም ከዘመኑ ሥጦታ ጋር ሳይገናኙ ዳር መቆም ህይወትን ሞናትነስ ያደርጋል እና ዘመናችን በሰጠን፤ እጅግ በተደራጄ፤ ቀልጣፋ እና ስልጡን ዘመን ሰጥ የሚዲያ ፎርማት ተጠቃሚ መሆን በእጅጉ አልፈላጊ ነው። እያንዳንዱ ሰውም ሰብዕናውን የሚገነባበት፤ የራሱን አሻራ የሚያስቀምጥ ነፃ እና ለታረመ አንደበት ብቁ የሆነ ዕድል ስለሆነ ተጠቃሚነቴ ይቀጥላል። ...

የፖለቲካል ፓርቲን የመረጠ ሰብዕ #የእኔ የሚለው የፖለቲካ ዕይታ ሊኖረው አይችልም።

ምስል
  የፖለቲካል ፓርቲን የመረጠ ሰብዕ #የእኔ የሚለው የፖለቲካ ዕይታ ሊኖረው አይችልም ።       "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     #ምዕራፍ ፲፰።       ፎቶው የፖለቲካ ድርጅት ቋሚ ሠራተኛ ሳለሁ የነበረ የሥራ መታወቂያ ካርዴ ላይ ያለ፤ እንደ ልጄ የማዬው፤ አብሮኝም የተሰደደ፤ እጅግ እምሳሳለት የፓርቲዬ የኢሰፓ ቅርሴ ነው። ፓርቲዬን ኢሠፓ እወደዋለሁኝ። በህይወቴ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ፓርቲዬ ኢሠፓ ነው።   ከኢሠፓ ጋር እስከ መጨረሻው ታግያለሁኝ። እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ለፓርቲዬ ደንብ፤ ፕሮግራም #በድንግል ነው ያለሁት። ከፓርቲዬ ኢሠፓ መራራ ስንብት በኋላ አይደለም የፖለቲካ ድርጅት፤ ማህበር እንኳን በአባልነት ተመዝግቤ፤ ተሳታፊ ሆኜ፤ መዋጮ አዋጥቼ አላውቅም። ወደፊትም ፈጽሞ አይታሰብም። ይበቃል።    እንደ ዕድል ሆኖ እኔ አገር ለመምራት ሙሉ ልቅና፤ ሙሉዑ ልዕልና፤ ሙሉ ብቃት በነበራቸው ታላላቅ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቀ - ሊቃውንት ነበር የመለመሉኝ። #የሠሩኝ ልበል። እነ ጓድ ገብረመድህን በርጋ፤ እነ ጓድ ወንድወሰን ኃይሉ ወዘተ…   የማይናወጽ ጽናት፤ #የማይበረግግ ሰብዕና፤ እጥፍ ዘርጋ የማይል ዕይታ፤ ገባ ወጣ የማይል የፖለቲካ አቋም ብቻ ሳይሆን አጥርቶ የመስራት ሚስጢር፤ የፖለቲካ ፓርቲ ጽንሰ ሃሳብ፤ ዲስፕሊን ተልዕኮ በተለያዩ የኮርስ፤ የሰሚናር፤ የጉባኤ ዕድሎች እንድሳተፍ በማድረግ ብቻም ሳይሆን ህይወቱ እኖረው ዘንድ በቅርብ እየተከታተሉ አዕምሮዬን አነጹት።    የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ቢመጣ - ቢሄድ፤ ሚሊዮኖች የእኛ ቢሉት፤ ስልጣን ቢይዝ ቢለቅ ከቶውንም #አይናፍቀኝም እስከ ህይወቴ ፍፃሜ። በዛ በተደራጄ፤ ምራቁን...