#እነማንን ይሆን የሚል ጥያቄ ያስነሳል።
" #ሆደ ሰፊ እንሁ -----" #ን "። " ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። #ምዕራፍ ፲፱። "አሁን ግን #እንሰሶችን ጠይቅ፥ ያስተምሩኃልም፥ የሰማይ #ወፎችንም ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። ወይንም #ለምድር ተናገር፥ እርሷም #ታስተምርኃለች ፤ የባህር #አሳወችም ይነግሩሃል።" (መጸሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ከ ፯ - ፰።) እንዴት ዋላችሁልኝ ክብሮቼ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የፓርላማው መደምደሚያ ቀን በንግግራቸው ማጠናቀቂያ ይህን ተናግረዋል። እርዕስ ያደረኩትን። ሃሳቡ ጥሩ ነው። ሃሳቡ ጥራት እና ብቃት ያለው ትውልድን ከዘመን ወደ ዘመን በተፈጥሮ ድልድይ ሊያሸጋገር የሚችል ነው። "ሆደ ሰፊ እንሁን።" የወል ጉዳይ ነው --- አገላለጹ። #እነማንን ይሆን የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ከሳቸው በተጨማሪ ማን እነማንን ይመለከታል። እነማንንስ ያካትታል? ሌላው #ከመቼ ጀምሮ የሚል ተከታይ ጥያቄም ያስነሳል። የውሳኔው ተፈፃሚነት፤ የሳቸው ቃል ከተነገረበት ቅጽበት ጀምሮ፤ ወይንስ በቀጠሮ? በአሳቻ ቀንና ወር ይሆን? የሚልም ሌላ ጥያቄ ያስነሳል። በሌላ በኩል አስበውበት መጥተዋል ለማለትም የማያስደፍር ዕውነት አለ። አንድ የፓርላማ አባል ጥያቄ ሲያቀርቡ በቀደመው የመከፋት ድባብ ውስጥ ሆነው ሲያዳምጡ አይቻለሁኝ። ጥያቄ አቅራቢውን ማየት አልፈቀዱም። በልቤ ዛሬ በመሰነባበቻ ቀን እንኳን ያለውን ነገር ቻል አድርጉ ለማሳለፍ ስለምን አቃታቸው። እያልኩ ይህን ሳስብ መጨረሻ መልሶች ከሰጡ በኋላ፤ አስቀጥለው " ጀግና፤ አብረን እንስራ፤ #ሆደ ሰፊ እንሁን" ሌላም አለ እምጽፍበት የሚሉ ኃይለ ሐረጋት ወይንም ሥንኛ...