ቤልጀም ብራዚልን አንገት አስደፋ።
ቤልጄም ብራዚልን አንገት አስደፋ። ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „የሚለምኑትን ሰዎች ልመናቸውን ይሰማል።“ (መጸሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፯) ዛሬ ቤልጀሞች ማልዶ ነው የቀናቸው። ጨዋታው ግን የሞት የሽረት ያህል ነበር። ኳስዬ ተደልቃም አሽካክታም ተወቃቅታም የሰናይ መሰረት ናት። ኳስ ፍቅር ነው። ኳስ መሻት ነው። ኳስ ደስታ ነው። ኳስ ሰላም ነው። ኳስ ኪዳን ነው ኮስ ጥበብ ነው። ኳስ መቻቻል ነው። ኳስ መከባባር ነው። ኳስ ዕውቅና መስጠት - መቀበል - ማግኘትም ነው። ኳስ ተስፋ ነው። ኳስ ድል ነው። ኳስ ትጋት ነው። ኳስ የድካም ሥራ፤ የልፋት ውጤት ነው። ኳስ የማሰብ ችሎታ ነው። ኳስ የእግር ሥራ ሳይሆን የጭንቅላትም ነው። ኳስ ልዩ መክሊትም ነው። ኳስ ህግ -ዳኝነት - ችሎትም ነው። ኳስ ትውልድ ነው። ኳስ የፈጠራ ሥራ ቤተሰብ ነው። ኳስ ሳቅ ነው። ኳስ ማስተዋል ነው፤ ኳስ መልካም ነገርን መመኘት ነው ተስፋን። ኳስ ጊዜ ነው። ኳስ ክውን ያለ ንጡህ መንፈስ ነው። ኳስ ምጥን ያለ ዕቅድ እና ግብ ያለው የመሆን ሁነኛ ነው። ኳስ ነገ ነው። ኳስ ሃብትነቱ ለማህበረሰቡ የማህበረሰቡ አንጡራ ሃብት ነው። ኳስ ዘመናይ ኢንደስትሪ ነው። ኳስ ሲታስብ ዓለም ደንበር ወስን የ...