ልጥፎች

የደብርዬ¡ ምሾ ይሁን፤ የአስተዛዛኞች ዓላማ እና ግብ ግን አልገብቶም!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝብር ቅር ቅ። „አቤቱ እጅህ ከፍ ከፍ አለች፤ አላዩምም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላላች“  ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፲፩  ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15.01.2019 ከእመ ብዙሃን። ·        ማ ሟሻ … ውዶች ክብሮቼ እነ ናፍቆት የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? ደህን ናችሁ ወይ? ውይ ዛሬ ፏ ፍንተው ብሏለኝ አዬሩ፤ እትጌ ልዕልተይ ጠሐይ መጥታ ትፍነሸነሻለች - ታፍነሸንሻለች፤ ለነገሩ የዚህ ዓመት ክረምት ቀለል ያለ ነው። ምን ትፈሪያለሽ ብባል ክረምትን ነው የምላችሁ፤ አገር ቤት እያለሁ አብሶ አዲስ አባባ ኗሪ በነበርኩበት ጊዜ ክረምት እህቶቼ በፈረቃ ይመጡልኝ ነበር፤ ሆዴ ርብሽብሽ ነው የሚለው፤ በተለይ ነጎድጓድ አልወድም። በዬአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ እንዲህ የያዝነው ዘመን ዓይነት ሲመጣ ደግሞ ሳንክ አይጠፋም። ብቻ ጠሐይ ካለች ተስፋ ነው። ተስፋ ደግሞ ያጀግናል። ·          ተዚህ ላይ ዕለቱንስ አብረን ብናዘክር። ዛሬ ጥር ሥላሴ ነው። የጎንደሪት የልጅነት ጊዜ ታወሰኝ፤ የዋሾ ሜዳ፤ የማርገጃው ወይራ…  ዓይኔ ዕንባ አቀረረ። አያቶቼ ነዳይን ፍሪዳ አርዳው በቁርጥ የገና ጾምን እንዲፈቱ የሚያደርጉበት ዕለት ነበር ዛሬ - ትውፊቱ እንደዛ ነበር። ሸንበቆው ተሰንጥቆ፤ እንደ ካራ ይዘጋጃል፤ ጤፍ እንጀራው ዘንጠፍ ብሎ ታጥፎ በአዋዜ ቁርጥ ለሚፈልግ ቁርጥ፤ ጥብስ ለሚፈልግ ጥብስ አደግድገው መላከብርሃናቱ አያቴ እና ታናሽ ወንድማቸውም መላከብ...

የአካዳሚ ነፃነት የትውልድ አውንታዊ ብቅል ነው!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  መ ሠ ረት። „የፃድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ የፃድቅናንን መንገድ ታቃናለህ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ Seregute©Selassie 14.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። ·        እ ፍታ። እንዴት አመሻችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ይህቺ እንደነፍሴ የምወዳት አገር እምዝምታ ሲዊዝሻ ጸጥታውን እዬመገበችኝ ነፍሴን ታፍነሽንሸኛለች። እኔ ግርግር ጩኽት - ሁካታ-  የአገር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አልፈቅደውም /ሰላማዊ ስልፉ/። ድምጽ የባዘበት ቦታ ይጨንቀኛል። አንድም ከቤቴ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማ ነገር የለም። እቃ ሲታጠብ በጸጥታ፤ በር ሲከፈትም ሲዘጋም በዝግታ ነው። ራሱ ጎረቤቶቼ ስለመኖሬ ወይንም ስላለመኖሬ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም። ጸጥ ረጭ። እናላችሁ ሲዊዚሻን ሳስባት ለእኔ ተብላ የተፈጠረች ይመስለኛል። አብሶ እኔ ያለሁበት ቪኒቲ። ቪንቲ የቁልምጥ ስሙ ነው። ከዚህ ከተማ የተፈጠሩትም የገጠሙኝ ሁሉ ቤተሰብዐው ስብዕና ያላቸው ናቸው። ይህችን እንደ ወግ ቢጤ ካደርኩኝ ስለዛሬው ቁም ነገር ልንገራችሁ … ትውልድ። ·        ትውልድ። ትንተና የለውም እንዲሁ በመደዴው ስሄድበት ግን ትውልድ በመኖር ውስጥ ያለ የአገር መኖር ማለት ነው። አገር ለማኖር ደግሞ የትውልድ መኖር ብቻውን በቂ ነው ሲባል ጥማድ በሬ ገዝቶ ማሳ የሌለው ገበሬ ይሆናል። እና የትውልዱ መኖር መበራከት ብቻውን አገርን የማስቀጥል አቅም ሊኖረው አይችለም። ማሳው በበጎ በፈቃደኝነት፤ በባለቤትንት፤ በታማኝነት፤ በምክንያታዊነት መታ...

እንደ ሴት እንደ እህትም እንደ እናት እንደ ዜጋም ምን ይሰማችኋል?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።    እንደ ሴት እንደ እህትም እንደ እናት እንደ ዜጋም ምን ይሰማችኋል ? „ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፣   ጠማማውን እባብ ሌዋታንን በጠንካራ በታላቅም   በብርቱም ሰይፍ ይቀጠዋል በባህርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል። “ ትንቢተ ኢሳያስ ፳፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie  14.01.2019 ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? የኢትዮጵያ እናቶች መቼ ይሆን ዎህ የሚሉት ይሆን? መቼ ይሆን የሚያርፉት - ከሰቀቀን? መቼ ይሆን ከሞት በመለስ ባሉ የልጆቻቸው የመኖር ውጤታማ፤ ስኬታማ ትርጎሞች እያዩ እፎይ የሚሉት? ከቶ መቼ ይሆን ያቺ ምስኪን የኢትዮጵያ እናት ከጉንጯ አልፎ ደረቷን በሚያርሰው የህሊና ወራጅ የዕንባ ቋት ተላቃ የልጆቿን ቁም ነገር አይታ ነገን በመልካምነት የምታስበው? መቼ ይሆን የኢትዮጵያ እናቶች ከስጋት የሚወጡት? የኢትዮጵያ መንግሥት አንድ ሰው በቁም እስር ማስቀመጥ ተስኖት አሁንም የወለጋ እናቶች ያለቅሳሉ። የወ/ሮ ታደሉ እንባ በቃህ እንዳይባል አንድ የዘመን እሾኽ ተፈጥሮበት አሁንም ዋይታ በረከተ።  አሁን ያን ሁሉ የሬቻ ዘግናኝ መከራ ያዬ፤ ያን ሁሉ የካቴና ዘመን ያሳለፈ፤ ያን ሁሉ መገፋት እና የስላቅ ዘመን በቃህ የተባለ ነፍስ እንደገና በትግሉ ባመጣው ነፃነት መጠቀም ሲገባው በአውሮፕላን ጥቃት ተፈጸመበት መባል ሲሰማ እኔን ሥርጉተን እንደ ሴት፤ እንደ እህት፤ እንደ እናት፤ እንደ ዜጋም ከሬቻው ጭፍጫፋ ባለነስ  ውስጤ እርር ኩምትር ብሏል።   ደግሞም ከጅምሩ „ትጥቅ አልፈታም አላለም ተብሎ በ...