የልቅና የቅንነት አሳር።
እንኳን ደህና መጡልኝ። የልቅና የቅንነት አሳር ። „መከራን ያጸኑብሽ ባንቺ ጥፋት ደስ ያላቸው ይጎሳቀላሉ።“ መጽሐፈ ባሮክ ፬ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.01.2019 እመ ዝምታ ሲወዘርላንድ። የእኔ ድንግልዬ ትጠብቃችሁ! አንድ ዜና ተከታተልኩኝ። ለነገሩ እኔም ጠፍተውብኝ ነበር የሰነበትኩት ዶር ለማ መገርሳ። በተደጋጋሚ ታመሙ፤ ለህክማና ሄዱ የሚለው ዜና ሁልጊዜ ይረብሸኛል። ቅን ሰው የማያበረክተው ዕድላችን በምን ዓይነት ሁኔታ ይህን ዘመን ሊያሻግረን እንደሚችል ግራ ይገባል። አንድ ጠንከር ያለ ዘገባ OBN አቅርቧል። ታዩት ዘንድ ከሥር ለጥፌያለሁኝ። ይህን መሰል ተግባር የዛሬ ዓመት በትጋት ይሠራ ነበር ሚዲያው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተመረጡ በኋዋላ ግን አቁሞት ቆይቷል። በዚህ ጉዳይ ቢተጋ ብዙ መንፈሶችን መሰብሰብ ይችል ነበር ሚዲያው። ይህን ዘመን ለመታደግ ይህ ሚዲያ ቁልፍ ድርሻ አለው። ስለዚህ ዘመኑን ሳያቃጥል በትጋት በዚህ መሰል ተግባር ላይ ቢያተኩር መልካም ይሆናል። የሆነ ሆኖ ቅኑ፤ ትሁቱ፤ ለስላሳው የዴሞክራሲ አባት ዶር ለማ መገርሳ በርከት ላሉ ቀናት ከሚዲያ የሉም። መቼም ኦነጋውያን፤ ህወሃታውያን ያህል ጸረ ሰብ ደርጅቶች አስቀምጦ በመዘናገት የተፈጠረ ችግር ከኖረ እጅግ ሚያሳዝን ነው የሚሆነው። ምክንያቱም እኔ እራሴ ከውጥኑ ጀምሮ ይጠነቀቁ ዘንድ በስፋት ጽፌያለሁኝ ህዳር ላይ ከ2017 ጀምሮ። ይህ መሰል ህፃፅ የሥልጣን ሱስ ብቻ...